TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዛሬው የክልል መንግስታት መግለጫ !

ዛሬ የክልል መንግስታት #ተመሳሳይ_አይነት ይዘት ያላቸው መግለጫዎችን አውጥተዋል።

እስካሁን ድረስ መግለጫቸውን ለህዝብ ያሰራጩት ፦

- የሶማሌ ክልል
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል
- የደቡብ ክልል
- የሐረሪ ክልል
- የጋምቤላ ክልል መንግስታት ሲሆኑ በመግለጫቸው " በተገቢው አካል ያልተፈቀደ እና የደህንነት ስጋት የሚፈጥር ሰላማዊ ሰልፍ " የተከለከለ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

የየክልሉ መንግስታት ባወጡት ተመሳሳይ አይነት ይዘት ባለው መግለጫ ፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተከሰተው ችግር የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖና መሰረት ባደረገ ውስጠ ደንብ / ውስጣዊ አሰራር ሊፈታ ይገባል የሚል አቋማቸውን ገልጸዋል።

" በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ከሃይማኖት ጉዳይነት አልፎ እየተወሳሰበና በርካታ እኩይ ዓላማ ያላቸው የሀገር ውስጥና የውጭ የፓለቲካ ኃይሎች ተቀናጅተው ኢትዮጵያን ለማዳከም ርብርብ እያደረጉ ናቸው " ያሉት የየክልሉ መንግስታት " ይህንንም በመረጃና በማስረጃ አረጋግጠናል ብለዋል።

በዚህም " ሐይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሀገርና የህዝብ ደህንነትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ማናቸውንም እንቅሳቃሴ እንቃወማለን " ሲሉ ገልጸዋል።

በተገቢው አካል ያልተፈቀደና የደህንነት ስጋት የሚፈጥር የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ማድረግም ተገቢነት ያለው ጉዳይ አይደለም ሲሉም አክለዋል።

የየክልሉ መንግስታት ባወጡት ተመሳሳይ አይነት ይዘት ባለው መግለጫቸው ፤ ህገ መንግስቱንና የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ውሳኔን መሰረት በማድረግ ማንኛውንም ሕገወጥ እንቅስቃሴ በመከላከልና በመቆጣጠር ህግ የማስከበር ኃላፊነታችንን እንወጣለን ሲሉ አስገንዝበዋል።

(መግለጫቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia