TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amahra

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም " ማንነታቸው አልታወቀም " የተባሉ #ታጣቂዎች አንድ መነኩሴ ሲገድሉ የገዳማት ንብረት ተዘርፏል።

በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በሚገኙ ሁለት ገዳማት " ማንነታቸው ያልታወቀ  ታጣቂዎች " ባደረሱት ጥቃት አንድ መነኩሴ ሲገደሉ የገዳማቱ ንብረቶች እንደተመዘበሩ ተገለጸ።

ሀገረ ስብከቱ ስለጉዳዩ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ ምን አለ ?

- በሀገሪቱ ላይ የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር እንደ ትልቅ አጋጣሚ በመጠቀም በሀ/ስብከቱ በሚገኙት በተለያዩ ወረዳዎች ሥር በሚተዳደሩ አድባራትና ገዳማት በተካሄደው ጦርነትና እየተፈጠረ ባለው ግጭት ብዙ ጉዳት ደርሷል።

- በማቻክል ወረ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በዋሻ አምባ አቡነ ተ/ሃይማት አንድነት ገዳም ታህሳስ 27 / 2016 ዓ.ም ሌሊት ማንነታቸው ያልታወቁ 8 ግለሰቦች ከገዳሙ ውስጥ በመግባት፡-

1ኛ. የገዳሙን አመሰራረትና የገዳሙን ሙሉ ታሪክ የያዘ የፊልም ዶክሜንት

2ኛ. የገዳሙ መጠበቂያ የሆኑ 2 ዘመናዊ ክላሾች ከእነ ሙሉ ተተኳሹ፤

3ኛ. በጥሬ ገንዘብ ከ100,000 /ከአንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ፤

4ኛ. ወርቅ በግራም 20 ግራም የሚመዝን

5ኛ. ለመነኮሳቱ በየጊዜው የሚሰፋላቸውን ሙሉ ጣቃ ልብስ

6ኛ. ዘመናዊ ተች የእጅ ስልኮች ብዛት 5

7ኛ. አምስት ጠገራ ብርና የአንገት ጌጣ ጌጦች

8ኛ. የጥበቃ ክፍሉን መጽሐፍና ብር 2000.00 በአጠቃላይ የተዘረዘሩትን የገዳሙን ንብረቶች ከመዘረፋቸውም በላይ ገዳማውያኑን በማንገላታትና የገዳሙን አበምኔት እማሆይ ወለተ ማርያም ገላውን አፍነው /አግተው/ በመውሰድ ከፍተኛ እንግልት አድርሰውባቸዋል።

- በአዋባል ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በመካነ ቅዱሳን ጣቢያ ቅ/ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም የተፈጠረ ችግር ጥር 27 ለ28 አጥባህ ከሌሊቱ በ6፡00 ሰዓት ማንነታቸው ያልታወቁ በቁጥር 5 የሆኑ ታጣቂዎች ገዳሙ ውስጥ ገብተዋል።

2 ክላሽ ጠበንጃ ፣ 1 ገጀራ ፣ 1 ሽጉጥ ፣ 1 አለንጋ የያዙ ታጣቂዎች የገዳሙን አበምኔት ቤት እንዲያሳዩአቸው ዘበኞችን በማፈን ይዘው መ/ሃይማኖት ቆ/አባ ሊባኖስን ፀበልተኛ እንደታመመ አስመስለው " ክፈቱ " ሲሏቸው " እኔ አልከፍትም " ወደ አባ ገ/ሕይወት ሂዱ ሲሉ ይነግሯቸዋል።

አባ ገ/ሕይወትም ጋር ሄደው በመሳሪያ አስገድደው ወደ ገዳሙ አባት መጋቢ ሃይማኖት ቆሞስ አባ ሊባኖስ አስታጥቄ በድጋሚ ሄደው " ክፈቱ " ሲሏቸው " ያለ ሰዓት አይከፈትም " የሚል ምላሽ ሲመልሱ የቤቱን በር በ5 ጥይት ደብድበዋል።

በድጋሚ የካቲት 20 ለ21 አጥቢያ ከምሽቱ በግምት 3፡00 ሰዓት ሲሆን ከገዳሙ ገብተው የእቃ ቤቱን በማንኳኳት የእናቶችንና የአባቶች7 ገዳም ቤቶችን በር ሲመቱ ቆይተው፦

👉  አባ ገ/ሥላሴ ታመነ የተባሉትን በገጀራ መተው #ገድለዋቸዋል

👉 ዲ/ን ዮሐንስ እና አብርሃም አያና ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰውባቸዋል።

👉 15 የሞባይል ስልክ ከፀበልተኛው ወስደዋል።

በቁጥር ያልታወቀ ገንዘብና ንብረት ወስደዋል።

በዚህም በ2ቱም ገዳማት ላይ ከፍተኛ የግድያ ፣ የድብደባና የንብረት ዝርፊያ እየተፈጸመ ስለሆነ ለወደፊቱም በቤተ ክርስቲያኗ፣ በገዳማት ላይ ከፍተኛ ችግር እየገጠመን ስለሆነ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia