TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
553 ኢትዮጵያውያን ወደሀገራቸው ተመለሱ!

አምስት መቶ 53 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረብያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡ በሳኡዲ አረብያ ጂዛን ግዛት ኢዋ እና ሲጂንነዓም በተሰኙ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 280 ኢትዮጵያውያን ትናንት ከሌሊቱ በ8፡30 ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ኢትዮጵያዊያኑ ከ5 ዓመት እስከ 30 ዓመት ድረስ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ጅዳ በሚገኘው የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት በኩል የሳኡዲ መንግስት ምህረት እንዲያደርግላቸው በተደረሰው ስምምነት መሰረት ከአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

ኢትዮጵያዊያኑ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኮንሱላር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ዮሃንስ ሾዴ እና ሌሎች አካላት በተገኙበተ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በተመሳሳይ በጅዳ እና ጂዛን ግዛት ያለ ህጋዊ የጉዞ ሰነድ ይኖሩ የነበሩ 273 ኢትዮጵያውን ረቡዕ ማታ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።ከነዚህ ተመላሾች ውስጥ 75ቱ ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወንዶች ናቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በተለያዩ ሀገራት በእስር ላይ የሚገኙ ኢትጵያውያንን በማስፈታት በህገወጥ መንገድ የሚኖሩም በፈቃደኝነት ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘነው መረጃ ያሳያል።

Via #AddisTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ECX

#የኢትዮጵያ_ምርት_ገበያ በ2011 በጀት አመት 681 ሺህ ቶን ምርት በመጠቀም በ33̇̇.8 ቢልዮን ብር #ማገበያየት መቻሉን አስታወቀ፡፡ ተቋሙ በ2011 በጀት አመት 681 ሺህ ቶን ምርት በመጠቀም በ33̇̇.8 ቢልዮን ብር ማገበያየት እንደቻለ አስታዉቋል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2011 በጀት አመት ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተደራሽነቱን በማሳደግና ዘመናዊ የግብይት ስርአትን በመከተል ሃገራዊ ተልእኮዉን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ ተደራሽነቱን ለማስፋት በክልሎች ኤሌክትሮኒክስ የግብእት ስርአትን ተግባራዊ ማድረጉን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድምአገኘሁ ነገራ ገልፀዋል፡፡ ተቋሙ ከግብይት ስራዉ ባሻገር በተለያዩ የቡና አብቃይ አካባቢዎች የሚመረቱ የቡና ምርቶች በሚመረቱባቸዉ አካባቢዎች እንዲጠሩ ተደርጓልም ብለዋል፡፡ በበጀት አመቱ ተቋሙ አጠቃላይ በ33.8 ቢልዮን ብር የተለያዩ ምርቶችን ሲያገበያይ መቆየቱን ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ተደራሽነቱን በሃገር ዉስጥ ለማስፋት የሚያከናዉናቸዉን ተግባራት አጠናክሮ በመቀጠል ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ጋር ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁሟል፡፡

Via #AddisTv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ

በአዲስ አበባ ከተማ #በ2012 የተመደበው #በጀት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚደረግ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 6ተኛ አመት የስራ ዘመን 3ተኛ መደበኛ ማጠቃለያ ጉባኤውን የከተማ አስተዳደሩን የ2012 በጀት በማጽደቅ አጠናቋል፡፡

ምክር ቤቱ በ2012 በጀት አመት ከ48 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መድቧል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ያሉባትን ችግሮች ለሚቀርፉ ፤ነዋሪዎቿን በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ለተባሉ እንዲሁም አንገብጋቢ ለተባሉ የልማት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ መስጠት ለሚችሉ ዘርፎች ልዩ ትኩረት የሰጠ በጀት ምደባ ነው ተብሏል፡፡

በጀት ከመመደብ ባለፈ አጠቃቀሙ ላይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጀቱን አዋጪ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የአስፈፃሚ ተቋማትን አቅምና አደረጃጃት የማስተካከል ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የተመደበው በጀት በአግባቡ ለታለመለት አላማ እንዲውል የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡

Via #AddisTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰራተኞች አለመሟላት፣ በሰዓት አለመገኘትና ፈጣን ምላሽ አለመስጠት ተገቢዉን አግልግሎት እንዳያገኙና በየጊዜዉ እንደሚላለሱ እያደረጋቸዉ መሆኑን የጽ/ቤቱ ተገልጋዮች ተናገሩ፡፡ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማስተካከልና የተገልጋዩን ቅሬታ በመመሪያ የተደገፈ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ አገልግሎት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

Via #AddisTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደብረ ታቦር (ቡሄ) በአል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በተገኙበት እየተከበረ ነው። #ETHIOPIA #AddisTV

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisTV_Live

የአ/አ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በህገወጥ የመሬት ወረራ ፣ ባለቤት አልባ ህንፃዎች እና የጋራ መኖሪያ ቤት እና የቀበሌ ቤቶች ዙሪያ የማጥራት ስራ ውጤት ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ምክትል ከንቲባዋ እየሰጡ የሚገኙትን ማብራሪያ በ "አዲስ ቴሌቪዥን ጣቢያ" በቀጥታ መከታትል ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot