TIKVAH-ETHIOPIA via @like
የዕለቱ መልዕክት፦
ውድ ኢትዮጵያዊያን ሃገራችንን ምንወደው የራሳችን የሆኑ ነገሮችን ስንወድ፤ እርስ በእርሳችን ስንከባበርና ስንፋቀር ነው። እኛ ብዙ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት ያለን ኩሩ ህዝቦች ነን። ኢትዮጵያዊነት #ሱስ የሚሆንብን ስለራሳችን ህዝብ፤ ስለምንወዳት ሀገራች ጠንቅቀን ስናውቅ ነው። ሁሉም ቋንቋ እና ባህል #የኛ የኢትዮጵያዊያን ነው፤ ልንኮራባቸው ለንከበከባቸው ይገባል።
@tsegabwolde @tikvahethedu

" ቲክቶክ " ኪርጊስታን ውስጥ እንዲታገድ ተወሰነ።
ኪርጊስታን " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው በሚል ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ወስናለች።
ውሳኔውን ያሳለፈው የሀገሪቱ የባህል ፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ነው።
ሚኒስቴሩ ባደረገው ግምገማ መሰረት " ቲክቶክ " ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ መቆጣጠሪያ እንደሌለው ገልጿል።
በተጨማሪም መተግበሪያው ለተጠቃሚዎቹ ትክክለኛ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎች እንደሌሉት ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ " ተጠቃሚዎችን በአጫጭር የቪዲዮ ክሊፖች ወደ ምናባዊ ግዛት ይስባል እናም እነዚህን ክሊፖች ከተመለከቱ በኋላ አንዳንድ ሰዎች ለሕይወት አስጊ የሆኑ አደጋዎችን የሚያስከትሉ ቪዲዮዎችን ለመኮረጅ ይሞክራሉ ሲል አክሏል።
እንዲህ ያለው #ሱስ የሚያስይዝ ይዘት በወጣቱ ትውልድ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በአጠቃላይም ለትውልዱ ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ የገለፀው ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ "ን ከሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ወስኗል።
ቲክቶክ ለሀገሪቱ እገዳ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።
" ቲክቶክ " በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ ሀገራት የሚደረግበት እገዳ እና ገደብ እየጨመረ መሆኑ ተነግሯል።
" ቲክቶክ " ከዚህ ቀደም በምስራቅ አፍሪካዋ ሀገር #ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ መቅረቡ ይታወሳል። በወቅቱም የፓርላማው አፈጉባኤ " ቲክቶክ በኬንያውያን በወጣቶች ዘንድ ተዘውታሪ በመሆኑ ፦ ግጭቶችን በማባባስ፣ ልቅ ወሲብን በማስፋፋት፣ የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት፣ የብልግና ቃላትን በማስፋፋት፣ አደገኛ ባሕሪያትን በማስፋፋት ለአገሪቱ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጠንቅ እየሆነ ነው " ብለው ተናግረው ነበር።
የእግዱ ጥያቄ ከቀረበ በኃላ ግን የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ከ " ቲክቶክ " ስራ አስፈፃሚ ጋር በመነጋገር በኬንያ ቲክቶክ ላይ የሚወጡ ቪዲዮች ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ስምምነት ላይ ሊደርሱ ችለዋል።
ከኬንያ በተጨማሪ ሶማሊያ የአሸባሪዎች መፈንጫ ሆኗል ፣ አሰቃቂ ቪድዮዎች ያለገደብ ይሰራጩበታል፣ ህዝቡንም አሳሳች መልዕክቶች ይዘዋወሩበታል በሚል እንዲታገድ መወሰኗ ይታወቃል።
የ " ቲክቶክ " መተግበሪያ በተለይ ፦
- ህፃናት ፣ ወጣቶች እንዲያዩትና እንዲሰሙት የማይመከሩ ቪድዮዎችን፤
- ልቅ የሆኑ የብልግና ስድቦችን ፤
- የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን፤
- ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን . . . የመሳሰሉትን በፍጥነት እንዲሁም እጅግ በቀላሉ ወደ ብዙሃን ያደርሳል ፤ ይህንን የሚቆጣጠርበት ስርዓት የለውም በሚል ይተቻል።
መተግበሪያው ለአጠቃቀም ቀላልና ማንኛውም ሰው የሚሰራው ቪድዮ በቀላሉ ለብዙሃን የሚደርስበት መንገድ ችግሩን እንዳባሰው የሚገልጹም አልጠፉም።
ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ " ቲክቶክ " በተለያዩ ሀገራት በርካታ ወጣቶች ተሠጥኦቸውን አውጥተው በቀላሉ ተደራሽ እንዳሆኑ ፣ በሚሰሯቸው ስራዎችም ክፍያዎችን እያገኙ እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲደግፉ ፣ ሀሳብ ያላቸውም ሀሳባቸውን በቀላሉ ለብዙሃን እንዲያደርሱ የሚያደርግ መተግበሪያ ነው በሚል የሚያወድሱት አሉ።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኪርጊስታን ውስጥ እንዲታገድ ተወሰነ። ኪርጊስታን " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው በሚል ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ወስናለች። ውሳኔውን ያሳለፈው የሀገሪቱ የባህል ፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ነው። ሚኒስቴሩ ባደረገው ግምገማ መሰረት " ቲክቶክ " ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ መቆጣጠሪያ…
#Update
የ " ቲክቶክ " እገዳ በኪርጊስታን ተግባራዊ ሆነ።
ኪርጊስታን " ቲክቶክ " በመላ ሀገሪቱ እንዲታገድ ውሳኔ ማስለፏ ይታወሳል በዚሁ ውሳኔ መሰረት የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ትዕዛዙን ወደ መፈጸም #እርምጃ ገብተዋል።
በሀገሪቱ " ቲክቶክ " መስራት እንዳቆመም ተነግሯል።
ሰዎች መተግበሪያውን ሲከፍቱን የሚያገኙት መልዕክት " Unable to load, please try again." የሚል ነው።
ውሳኔው በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት መ/ቤት የተላለፈ ነው።
የኪርጊስታን ዲጂታል ሚኒስቴር ቲክቶክን የሚያስተዳድረው ' ባይት ዳንስ ' ኩባንያ ፥ " #የልጆችን ፦
- አእምሯዊ፣
- አካላዊ፣
- መንፈሳዊ እና #ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም " ብሏል።
በዚህም ምክንያት " ቲክቶክ " በሀገሪቱ እንዳይሰራ ተደርጓል።
ውሳኔው የተቃወሙ አካላት ይህ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ገደቡ እንዲነሳ ጠይቀዋል። ከገደብ ይልቅ ቁጥጥር ይደረግበት ብለዋል።
ከዚህ ቀደም የኪርጊስታን የባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ፥ " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው " ማለቱ ይታወሳል።
መተግበሪያው #ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ #መቆጣጠሪያ እንደሌለው ነበር የገለጸው።
በተጨማሪም ለተጠቃሚዎቹ ትክክለኛ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎች እንደለለው እና ተጠቃሚዎችን በአጫጭር የቪዲዮ ክሊፖች ወደ ምናባዊ ግዛት በመሳብ #ሱስ የሚያስይዝ ይዘት እንዳለው አስረድቶ ነበር።
ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ " በወጣቱ ትውልድ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በአጠቃላይም ለትውልዱ ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ አሳውቆ ነበር።
በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ውስጥ ከመረጃ ደህንነት ጋር በተያያዘ መተግበሪያው እንዲታገድ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገ ሲሆን " ቲክቶክ " ከቻይናው ኩባንያ ካልተፋታ / አሜሪካ የምትቆጣጠረው አይነት ካልሆነ በመላ ሀገሪቱ መታገድ ዕጣ ፋንታ ሊገጥመው ይችላል ተብሏል።