TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና! የደቡብ ሱዳኑ የአማፂ ቡድን መሪ #ሪክ_ማቻር  የሀገሪቱን ሰላም  ለመመለስ የሚያስችለውን የተሻሻለውን ስምምነት #ለመፈረም ፍቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

📌የአማፂ ቡድን መሪው ሀገሪቱ ሊኖራት በሚገባው የክልል #መጠንና #የደንበር ጉዳይ በነበራቸው ቅሬታ ማሻሻያ የተደረገበትን ሁለተኛ ስምምነት ለመፈረም ፍላጎት አልነበራቸውም።

▪️ሆኖም #ከሱዳን መንግስት ጋር በተደረገ ከፍተኛ #ድርድር ሪክ ማቻር የመጨረሻውን የሰላም ስምምነት ለመፈረም መዘጋጀታቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አል ዲርዲር መሀመድ ተናግረዋል።

©CGTN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

የኦነግ መሪዎች እና የኢፌዴሪ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት #ድርድር እና #ውይይት እያካሄዱ ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ የተፈጠረው ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ #መፍትሔ እንደሚያገኝ ሁለቱም ወገኖች ቃል ገብተዋል። ውይይቱ የሚካሄደው በዝግ ስብሰባ ሲሆን ከውይይቱ ማብቃት በኋላ ለህብረተሰቡ #መግለጫ ይሰጣል ተብሏል።

ምንጭ፦ Afendi Muteki
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE ቻይና ከአሜሪካ ጋር የገባችውን የንግድ ጦርነት #በሰላም ለመፍታት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች። የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ዋንግ ቂሻን በንግድ ጦርነት አሸናፊ አለመኖሩን ገልፀው ቻይና ከዋሽንግተን ጋር የገባችውን የንግድ ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል #ድርድር ለማካሄድ ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የፀደቀው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ማሻሻያዎች ተደረገበት ? የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚ አዋጅ በዛሬው ዕለት በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል። የኮሚሽኑን መሪዎች በመሰየሙ ሂደት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ በሙሉ እጃቸው እንዳይገባ ሆኖ ነው የኮሚሽኑ የማቋቋሚያ አዋጅ የፀደቀው። አገራዊ መግባባትን ለማምጣት ተከታታይ ምክክሮችን በማዘጋጀት እንዲሰራ ስልጣን የተሰጠውን ኮሚሽን…
" የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ ይመረጣሉ " - የህግ ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ እንደሚመረጡና ሹመታቸውም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደሚጸድቅ የህግ ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ናቸው።

በጋዜጣዊ መግለጫው ምን ምን ነጥቦች ተነሱ ?

• የኮሚሽነሮች ጥቆማ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያካተተ ነው። ከተጠቆሙት 14 እጩዎች መካከል 11 ተመልምለው በአፈ ጉባኤው አቅራቢነት በም/ቤቱ ይሾማሉ።

• ኮሚሽነሮቹ በም/ቤቱ ከተሰየሙበት እለት ጀምሮ ለ3 ዓመታት የሚቆይ የስራ ጊዜ ይኖራቸዋል። እንደ አስፈላጊነቱ ቆይታቸው ሊራዘም ይችላል።

• በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ስለ #ድርድር የሚገልጽ ምንም አይነት ይዘት አልተካተተም፤ የአዋጁ ዋና አላማ እስካሁን መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸውና የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተኑ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያካተተ ውይይት በማድረግ ችግሮችን መፍታት ነው።

• የሚቋቋመው ኮሚሽን ከምክክር መድረኮቹ የሚያገኘውን ምክረ ሀሳብ በመቀመር ተግባራዊ እንዲደረጉ ይሰራል። ም/ቤቱን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት ወስደው እንደሚያስፈጽሙና ለስኬታማነቱም ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል።

#HPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OFC የኦሮሞ ፊዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሁለተኛው መደበኛ ጉባዔ ተሳታፊዎች ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል። በዚህ መግለጫ ላይ ፤ ባለፉት 3 ዓመታት በሀገራችን የተከሰቱ ለአያሌ ንፁሃን ህይወት መቀጠፍ፣ ለከፍተኛ ንብረት ውድመትና ፣ ለዜጎች ክብር ውርደት የዳረጉ የርስ በርስ ጦርነቶች ማዘናቸውን ገልፀዋል። ከጥቂት ወራት ወዲህ ለእርስ በእርስ ጦርነቶቹ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ መንግስት…
' ብሄራዊ ምክክር '

የኦሮሞ ፊዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ተሳታፊዎች ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያላካከተና ገልልተኛ እና ተዓማኒነት በሌላቸው አካላት የሚመራ ብሄራዊ ምክክር የሀገሪቱን ችግር ይፈታል ብለን አናምን ብለዋል።

ጉባኤተኞቹ የተሳካ የሆነ ብሄራዊ ምክክር እንዲደረግ ያስችላሉ ያሏቸውን ምክረ ሃሳቦችን በዝርዝር አቅርበዋል ፦

👉 በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ግጭት እንዲቆም በማድረግ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ፤

👉 ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች በተለይም ባአሁን ጊዜ በተለያዩ እስር ቤቶች ግፍ እየተፈፀመባቸው ያሉ የኦፌኮ እና ኦነግ አመራር አባላት ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፤

👉 መንግስት የእርስ በእርስ ጦርነቱ ላይ እየተሳተፉ ካሉ የታጠቁ ኃይሎች ጋር #ድርድር በመጀመር እና ግጭቶች እንዲቆሙ በማድረግ ፣ ያሉትን የህግ ማነቆዎችንም ሙሉ በሙሉ በማንሳት ብሄራዊ ምክክር ላይ እንዲሳተፉ ሊጋብዛቸው ይገባል፤

👉 የብሄራዊ ምክክሩ አዋጅ ሊዘጋጅ የሚገባው በጋራ ስምምነት ሆኖ ኮሚሽነሮችም ምክክሩ ላይ በሚሳተፉ አካላት ሊመረጡ ይገባል ብለዋል።

(የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ)

@tikvahethiopia
#PressBriefing

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር ፤ በመግለጫቸው ያነሷቸው ነጥቦች እና ተጠይቀው ከመለሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ጥቂቶቹ ፦

- በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፈጸሙ በተባሉ ጥሰቶች ላይ ተመድ [UN] ሊያደርገው ያቀደው ተጨማሪ ምርመራ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። በኢሰማኮ እና በተመድ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የጋራ ሪፖርት ላይ የተመላከቱ ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር መንግስት ዝግጁ ነው ብለዋል። ነገር ግን በተመድ በኩል ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የሚደረገው አካሄድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

- ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነት ተጠናክሮ መቀጠሉን፣ አገራዊ ምክክሩ በሂደት ላይ መሆኑ እና ሰላምን የማስፈን ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠላቸውንም ተናግረዋል።

- ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ 19 በመቶ ድርሻዋን እንዳጣች በሚመለከት ይፋ የሆነውን መረጃ በተመለከተ መንግስት መረጃውን እያጣራ ይገኛል ብለዋል።

- መንግስት ሱዳን የያዘችው የኢትዮጰያ መሬት በሌሎች የኢትዮጰያን መረጋጋት በማይፈልጉ አገራት ግፊት የወሰነችው ውሳኔ አድርጎ እንደሚወስደው ገልፀዋል። አሁንም ቢሆን መንግስት ሱዳን ከያዘችው የኢትዮጵያ ግዛት ያለ ግጭት ለቃ እንደምትወጣ ተስፋ አለው ብለዋል።

- ከሰሞኑ ገንዘብ ሚኒስቴር የ2015 ዓ.ም በጀትን ለክልሎች ሲደለድል #የትግራይ_ክልልንም አካቷል ፤ የበጀት ድልድሉ #ድርድር ስለመጀመሩ አመላካች ነው ወይ ? ተብሎ ለተነሳ ጥያቄ አምባዳደር ዲና ሙፍቲ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

Credit ፦ #ኤፍቢሲ #አሀዱሬድዮ #ኢትዮኤፍኤም

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrAbiyAhmed ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከህ/ተ/ም/ቤት አባላት እየተነሳላቸው ላለው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ። በአሁን ሰዓት በፀጥታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ነው። በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በቀጥታ መከታተል ይቻላል። ዋና ዋና ነጥቦችን ተከታትለን እናሳውቃለን። እስካሁን ድረስ ያነሷቸው ጉዳዮች እና ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡባቸው (ከፀጥታ ጉዳዮች…
#ድርድር

ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ መንግስት ከTPLF ጋር ድርድር ሊያደርግ እንደሆነ የተለያዩ ምንጫቸው በግልፅ ያልተገለፁ/ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ሲወጡ ነበር።

ዛሬ ከህ/ተ/ም/ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ድርድርን በተመለከተ መረጃ ሰጥተዋል።

" ከማንም ጋር ሰላም ነው የምንፈልገው። " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " እያንዳንዷ የሰላም ቀን ለእኛ ትርፍ ታስገኝልናለች። ሕዝብ ሳያውቀው የሚደረግ ድርድር የለም። " ብለዋል።

አክለውም ፥ " በይፋ የታወቀ አጥኚ ኮሚቴ ተቋቁሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት እየተመራ ሲሆን፣ እስካሁን ውጤቱን አላሳወቀም። የሚደራደረው ኮሚቴም ይሄ ነው። " ብለዋል።

" ውጊያ ሲመጣ ለሕዝብ አሳውቀን የጀመርን ሰዎች፣ ድርድር ከተጀመረ የሚያስደብቀን ነገር የለም። ነገር ግን፣ የብቻ ጠላት የለም የሀገር ጠላት እንጂ፣ ለብቻም የሚሰራ ሥራ የለም በጋራ እንጂ። " ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

የእኛም የሕዝባችንም ፍላጎት ለጥይት የሚወጣ ውጪ ለልማት እንዲወጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ሰላም እንፈልጋለን ማለታችን የተደበቀ ድርድር እናደርጋለን ማለት አይደለም " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ፦
- በፀጥታ ተቋማት ዝግጅት፣
- በህግ ማስከበር፣
- በ ' ተረኝነት ' ጉዳይ ፣
- በማህበራዊ ሚዲያዎች ጉዳይ ፣
- ሌብነትን በተመለከተ፣
- የብሄራዊ ምክክሩን በተመለከተ የሰጧቸው ምላሽ እና ማብራሪያዎች በዚህ ታገኛላችሁ https://telegra.ph/PM-Abiy-Ahmed-06-14-2 (#PMOEthiopia)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ድርድር ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ መንግስት ከTPLF ጋር ድርድር ሊያደርግ እንደሆነ የተለያዩ ምንጫቸው በግልፅ ያልተገለፁ/ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ሲወጡ ነበር። ዛሬ ከህ/ተ/ም/ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ድርድርን በተመለከተ መረጃ ሰጥተዋል። " ከማንም ጋር ሰላም ነው የምንፈልገው። " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " እያንዳንዷ የሰላም ቀን ለእኛ ትርፍ ታስገኝልናለች።…
#ድርድር

የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በሰላም መቋጫ ያገኝ ዘንድ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም አንዳንድ የውጭ ሀገር ሚዲያዎች ድርድርን በተመለከተ በግልፅ ምንጫቸው የማይታወቁ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ከርመዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ንግግር አለመጀመሩን ነገር ግን ለዚሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁሟል።

ትላንት ፓርላማ የቀረቡት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋ የታወቀ አጥኚ ኮሚቴ ተቋቁሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት እየተመራ መሆኑን፤ እስካሁን ውጤቱን አለማሳወቁን እና የሚደራደረው ኮሚቴም ይሄ መሆኑን ጠቁመው ነበር። ድርድር ሲጀመር መንግስት የሚደብቀው ነገር እንደሌለም ገልፀው ነበር።

ይህ የጠቅላይ ሚስትሩ ንግግር ከተሰማ ብዙም ሳይቆይ በህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የተፃፈ ደብዳቤ ተሰራጭቷል።

ይኸው ደብዳቤ ህወሓት በኬንያ መንግስት በተጠራ ድርድር የሚሳተፍ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለመላክ መዘጋጀቱን ይገልጻል።

ደብዳቤው በኬንያ መንግስት የተጠራ ድርድር #በናይሮቢ ስለመኖሩ ፍንጭ የሰጠ ነው።

ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሰላም ድርድሮችን በማስመልከት የትግራይ ክልልን አቋምን ለማሳወቅ ደብዳቤውን የፃፉት ለአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀ መንበርና የሴናጋሉ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል፣ ለኬንያው ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ፣ ለተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አልናህያን እና ለታንዛኒያዋ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን እንዲሁም የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ነው።

ያንብቡ ; https://telegra.ph/Dr-Debretsion-GMicahel-06-15

@tikvahethiopia
#እናት_ፓርቲ #ድርድር

እናት ፓርቲ የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ ለማድረግ የታሰበውን ድርድር እንደሚገፍ ገልጾ ነገር ግን በሁለቱ ፓርቲዎች (ብልፅግና እና ህወሓት) መካከል የሚደረግ እንዳይሆን ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብሏል።

ፓርቲው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በላከልን መግለጫው ነው ይህን ያለው።

እናት ፓርቲ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውና ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀረው ጦርነት ምን አልባት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከጋጠሟት ጥፋቶችና ውድመቶች ሁሉ ከቀዳሚዎቹ ሊቆጠር የሚችል ነው ብሏል።

ጦርነቱ ሰዋዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ ልቡናዊና ድፕሎማሲያዊ ጉዞን ለብዙ አሥርት ዓመታት ወደኋላ መልሷል ያለ ሲሆን ይህ ጦርነት ሊያመጣ የሚችለው ምስቅልቅልና ዳፋ አሳስቦት በእርቅና ሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሽምግሌዎችን ከማፈላለግ ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሷሳ።

አሁንም ያ ውድመትና ውረድ እንውረድ ዳግም እንዳይከሰት ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት የታየው መነሳሳት በደስታ የሚመለከተው ኩነት መሆኑን ገልጿል።

በመጀመሪያ ችግሩ እንዳይከሰት ብንከላከለው ጥሩ ነበር ከተከሰተ በኋላ የውጭ አካል ገብቶ በድርድር መልክ ከሚፈታ ይልቅ በሀገሬው ባህል በእርቅና ይቅርታ ቢፈታ መልካም ነበር ሲል ገልጿል።

ይህ ድርድር ብዙ ውስብስብ ጉዳዮችን ተሸክሞ የሚደረግ ነው ያለው ፓርቲድ ስለሆነም ሂደቱ ከቅድመ ድርድር ጀምሮ ዘለቄታዊ መፍትሔ በሚያመጣ መልኩ ታቅዶ ካልተፈጸመ እና የውጭ ኃይሎችን "አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት መከላከል ካልተቻለ ጅብ ፈርቶ ዛፍ ብወጣ፣ ነብር ቆየኝ” ዓይነት መሆኑ አይቀሬ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ፓርቲው ለድርድሩ ውጤታማነት ወሣኝ ናቸው ያላቸውን ነጥቦችን አንድ በአንድ ዘርዝሮ በመግለጫው አስቀምጧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ድርድር

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሸኔ ወይም እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ገልጸዋል።

ይህንን ያሳወቁት ፥ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ግጭት በሰላም ስምምት እንዲቋጭ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት በተካሄደበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ የወለጋ ሕዝብ እፎይ እንዲል ሁሉም ወገን የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል በቀጣዩ ሣምንት በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራ ልዑክ ወደ መቐለ እንደሚያቀና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሳውቀዋል።

ልዑኩ የሁሉንም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ያካተተ እንደሚሆን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

ፎቶ፦ ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ድርድር የኢትዮጵያ መንግሥት ከሸኔ ወይም እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ገልጸዋል። ይህንን ያሳወቁት ፥ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ግጭት በሰላም ስምምት እንዲቋጭ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት በተካሄደበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ…
#ድርድር

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ #ድርድር ምንድነው ያሉት ?

" ከኦነግ ሸኔ ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ ይጀመራል።

ይህንን ድርድር የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝብ አብዝቶ ይፈልገዋል።

በዚህ ድርድር የሚሳተፉ ወገኖች ሁሉ የዛሬዋን ቀን እያሰቡ ፣ ከግጭት፣  ከጦርነት እንደማናተርፍ አውቀው ህግ እና ስርዓት ተከትለን ይቅር ተባብለን ሀገራችንን በጋራ ማነፅ እና መገንባት እንድንችል ፤ የወለጋ ህዝብ አሁን ካለበት ስቃይ እፎይ ማለት እንዲችል ሁሉም ወገን የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ከወዲሁ ጥሪዬን አቀርባለሁ። "

ይህንን ድርድር በተመለከተ ከታጠቀው ቡድን (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት/ መንግሥት ኦነግ ሸኔ ከሚለው ቡድን) በኩል የሚሰጥ መግለጫ ሆነ መረጃ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ድርድር

መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ መሮ ዲሪባ ፥ የታጠቂ ቡድኑን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሚያደራድር ሦስተኛ አካል መኖሩን ለቢቢሲ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

ጃል መሮ አደራዳሪዎቹ እነማን እንደሆኑ በስም ከጥቀስ ተቆጥበዋል።

መሮ ዲሪባ ታጣቂ ቡድኑን ወክለው ከመንግሥት ጋር የሚደራደሩ የልዑክ ቡድን አባላት ወደ #ታንዛኒያ ጉዞ እያደረጉ ስለመሆኑ አሳውቀዋል።

መሮ ዲሪባ ይህ ንግግር በታንዛኒያዋ ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው #ዛንዚባር ደሴት ላይ እንደሚከናወን ገልጸው፤ " የጥይት ድምጽ ሳይሰማ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ መልስ የሚያገኝ ከሆነ በራችን ሁሌም ክፍት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

መሮ ፥ በቅርቡ ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና መንግሥት ሦስተኛ ወገን ባለበት በኬንያ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘው የታጣቂ ቡድኑ ተወካዮች በቦታው ቢገኙም የመንግሥት ተወካዮች ግን ሳይገኙ ቀርተዋል ብለዋል።

" በሌሎች አገራት ግብዣ በኬንያ ለመገናኘት ቀጠሮ ነበር። ነገር ግን መንግሥት ሳይገኝ ቀረ "  ያሉት መሮ " በአሁኑ ድርድር ስኬት ላይ ጥርጣሬዎች ቢኖረንም የንግግር ሂደቱ ሰላም ሊያመጣ ይችላል የሚል ተስፋ አለኝ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ንግግር መጀመሩ ጥሩ ነው። መነጋገር እና መፍታት ያለብን ብዙ ነገሮች ስላሉ ጉዳዩ በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ አይሆንም " ሲሉ አክለዋል።

ከዚሁ ድርድር ጋር በተያያዘ ቢቢሲ የኢትዮጵያ መንግሥት ከታጣቂ ቡድኑ ጋር በሚደረገው ንግግር ፦
- የስዊድን፣
- የኖርዌይ፣
- የኬንያ፣
- የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች እንደሚገኙ ሁለት ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ምንጮች እንደገለፁለት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" አሁንም ያለው ችግር በውይይት እና በድርድር የሚፈታበት መንገድ ዝግ ባለመሆኑ ተከታታይ ጥረቶች ይደረጋሉ " - የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዛሬ ምሽት መግለጫ አውጥቶ ነበር።

በዚሁ መግለጫው በአማራ ክልል ያለው ችግር አሁንም በ #ውይይት እና በ #ድርድር የሚፈታበት መንገድ ዝግ እንዳልሆነ ጠቁሟል።

መ/ቤቱ በመግለጫው ፤ " ከድርድር እና ውይይት ይልቅ መንግሥታዊ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝ የሚጥሩ እንዲሁም አጋጣሚዎችን በማቀነባበር ዝርፊያ ለመፈጸም የሚፈልጉ የታጠቁ ቡድኖች፣ ፅንፈኛና አክራሪ ኃይሎች ከውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ሀገራዊ የጸጥታ ሥጋት ለመደቀን ሙከራ እያደረጉ ነው " ብሏል።

በአማራ ክልልም እየታየ ያለው ሁኔታ ይኸው ነው ሲል ገልጿል።

" ከኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ጋር በተያያዘ የተከሰቱ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥረቶች ቢደረጉም ችግሩ በሚፈለገው ልክ አልተፈታም " ያለ ሲሆን ፤ " ለዘረፋ የተደራጁ ጥቂት ኃይሎች አሁን ላይ መንግሥታዊ መዋቅሮች እንዲፈርሱ፤ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት እንዲቋርጡ፤ አንዳንድ ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚያገናኙ የመንገድ መሠረት ልማቶች እንዲዘጉ በማድረግ፤ ሕዝቡ ላይ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ " ብሏል።

ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ፤ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅመው የጠቅላይ መምሪያ ዕዝን በማስተባበር የክልሉን ሰላምና ደኅንነትን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ የሚያግዝ ስምሪት ወስዶ እየሠራ መሆኑን ገልጾ " በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ " ሲል አሳስቧል።

አሁንም በአማራ ክልል ያለው ችግር #በውይይትና #በድርድር የሚፈታበት መንገድ ዝግ ባለመሆኑ ተከታታይ ጥረቶች ይደረጋሉ ሲል አሳውቋል።

" ለዝርፊያ ከተደራጁ ቡድኖች ጋር የሚንቀሳቀሱ አካላት ካሉ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ እና ሕግ የማስከበር ሂደቱ ተጠናክሮ ይቀጣላል " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia