TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የወላይታ ዞን ምክር ቤት‼️

የወላይታ ዞን ምክር ቤት በሁለተኛው ቀን ውሎ አቶ #ዳጋቶ_ኩምቤን የወላይታ ዞን ተጠባባቂ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ የሾመ። የዞኑ ተጠባባቂ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ቃለ መሃል ፈጽመዋል፡፡

የወላይታ ዞን ምክር ቤት በሁለተኛው ቀን ውሎ ያፀደቃቸው የዞን አመራሮች ዝርዝር፦

1. አቶ ዳጋቶ ኩምቤ የዞኑ ተጠባባቂ ዋና አስተዳዳሪ

2. አቶ ፍሬው ሞገስ ምክትል አስተዳዳሪና የወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ

3. አቶ ሙሉቀን ታደሰ የፍትህ መምሪያ ኃላፊ

4. አቶ ፃዲቁ ፈለቀ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ

5. አቶ ደሳለኝ ፋንታ የጤና መምሪያ ኃላፊ

6. አቶ ተፈሪ ላቢሶ የትምህርት መምሪያ ኃላፊ

7. አቶ ተከተል ጎአ የፋይናንስና ኢኮኖሚ መምሪያ ኃላፊ

8. ሐምሳ አለቃ ተሰማ ኡታላ የፀጥታና አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ

9. ወ/ሮ እቴነሽ ኤልያስ የሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ

10. አቶ አሞና ቶልካ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ ኃላፊ

11. ዶ/ር ኤፍረም ዳመነ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት መምሪያ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

በሌላ በኩል....

የወላይታ ዞን ምክር ቤት የብሔሩን #በክልል የመደራጀት ጥያቄን አፅድቆ ለአስፈጻሚ አካላት ውክልና ሰጥቷል፡፡

አጀንዳው በቀጣይ ወደ ታችኛው መዋቅር እስከ ቀበሌ ድረስ በአስፈጻሚ አማካይነት ወርዶ የህዝብ ውሳኔ ካለቀ በኋላ ወደ ክልል ምክር ቤት እንዲቀርብ ከስምምነት ተደርሷል፡፡

ከወላይታ ብሔር ጋር አብሮ እንደ ክልል ለመደራጀት የሚፈልግ ብሔርና ህዝብ ካለ በፍላጎቱ መደራጀት እንደሚችልም ምክር ቤቱ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ተማሪዎች ከጥቅምት 9 ጀምሮ ትምህርት ቤት በመገኘት ዝግጅት ማድረግ አለባቸው" - አቶ ማሄ ቦዳ (የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ)

የደቡብ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን የ8ኛ ክፍል ፈተና #በክልል ደረጃ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

የቢሮ ኃላፊው የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ. ም እንደሚሰጥ፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ አስታውሰዋል።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል መሠረት ባደረገ መልክ በኦንላይ ስለሚሆን ከኩረጃ የፀዳ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ማሄ ቦዳ ተማሪዎች ከጥቅምት 9/2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት ቤት በመገኘት ዝግጅታቸውን ማድረግ አለባቸው ሲሉ ማሳስበባቸውን ከቢሮው የ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Update

ዛሬ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ 4 ወረዳዎች እና 1 ከተማ አስተዳደር የ "ክላስተር" አደረጃጀትን በየም/ቤቶቻቸው ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባኤ አፅድቀዋል።

የመስቃን እና ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እና የቡታጅራ ከተማ ማዕከሉን ቡታጅራ ያደረገ አዲስ ዞን ለመመስረት በተጨማሪነት የወሰኑ ሲሆን የማረቆ እና ቀቤና ወረዳዎች ደግሞ ወደ ልዩ ወረዳነት ለማደግ ውሳኔ አሳልፈዋል።

የማረቆ፣ ቀቤና፣ የመስቃን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እንዲሁም የቡታጅራ ከተማ ም/ ቤቶች፤ በ" ክላስተር" የሚደራጀውን አዲስ ክልል የመቀላቀል ውሳኔን ያጸደቁት በሙሉ ድምጽ መሆኑን ተነግሯራ።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን የሚል ስያሜ ያለው አዲስ ዞን ለመመስረት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብም በተመሳሳይ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን ተነግሯል።

የ4ቱ ወረዳዎች ም/ቤቶች ዛሬ የወሰኗቸውን ውሳኔዎች ለፌደሬሽን ም/ቤት ያስገባሉ ተብሏል።

የፌዴሬሽን ም/ቤት ወረዳዎች እንደዚህ አይነት ውሳኔዎች የማሳለፍ ስልጣን አላቸው ወይ ? በሚል ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል።

የም/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ " ምክር ቤቶቹ ስለ ህዝብ ጥያቄ የመወያየት፤ ተወያይተውም ውሳኔ የማሳለፍ ስልጣን አላቸው፤ ሆኖም ጥያቄው የሚቀርበው #በዞን እና #በክልል ምክር ቤቶች አልፎ ነው " ሲሉ ማስረዳታቸውን #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር ዘግቧል።

ከቀናት በፊት የጉራጌ ዞን ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ዞኑን ከአጎራባች ዞኖች እና ልዩ ወረዳ ጋር አንድ ላይ በክልል እንዲደራጅ በመንግስት የቀረበውን ምክረ ሀሳብ በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አድርጎ ነበር።

በምክር ቤቱ ከተገኙ 92 አባላት ውስጥ 40ዎቹ የ " ክላስተር " አደረጃጀት ምክረ ሃሳብ የደገፉ ቢሆንም 52 አባላት ክላስተርን በመቃወማቸው ነው ምክረ ሀሳቡ ውድቅ የተደረገው።

@tikvahethiopia