" በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን " - ፕ/ር መስፍን አርአያ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት ወደ ምክክር መድረኩ እንዲገቡ ጥሪ አቀረበ።
ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።
አሁንም " ወደ ምክክር መድረኩ ኑ " ያለው ኮሚሽኑ ፤ ለታጠቁ አካላት ተገቢውን የጥበቃ ዋስትና በኮሚሽኑ እንደሚያመቻች ገልጿል።
ይህ የተሰማው በምክክር ጉባዔው የሚሳተፉ የኦሮሚያ ክልል ማህበረሰብ ተወካዮች የማጠቃለያ ልየታ መድረክ በሻሸመኔ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።
" በትጥቅ ትግል ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ #ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን " ያሉት ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ " የሚያዋጣን ይሄ ነው ፤ በየታች ድረስ ሄደን ያገኘነው ህዝባችን ሰላምን እንደሚፈልግ ነው የገለጸለን " ብለዋል።
ምክትል ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ሒሩት ገብረስላሴ በበኩላቸው ፥ እንዲህ አይነት ምክክር ትልቅ ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰዋል።
" ይህን አጋጣሚ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ሊጠቀሙበት ይገባል " ብለዋል።
" በተለይ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ አካላት ወደ መድረኩ ሊመጡና ሀሳባቸውን ሊገልጹ ይገባል ፤ እነሱ መጥተው በሚሳተፉበት ጊዜ ኮሚሽኑ ተገቢውን #የዋስትና_ጥበቃ /safe space/ የሚያመቻች ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከዶቼቨለ ሬድዮ ማግኘቱን ይገልጻል።
@tikvahethiopia