TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኩታበር⬆️ከደሴ ኩታበር ወደ ደላንታ /ወገል ጤና ሲጓዝ የነበረ FSR አይሱዙ ቅጥቅጥ የህዘብ ማመላለሻ መኪና ዛሬ ነሐሴ 30 2010 ዓ/ም ከጧቱ 1፡30 አካባቢ ከኩታበር ከተማ ወጣ ብሎ በግምት 10 ኪ/ሜ እንደተጓዘ #አደጋ ደርሶበታል፡፡ በአደጋው በተሳፋሪዎች ላይ #ቀላልና #ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡

©የኩታበር ወረዳ የኮሚኒኬሽን ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ⬇️

በአዲስ ዓመት ዋዜማ በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ #አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ6 ሰዎች ላይ ደግሞ #ከባድ እና #ቀላል የመቁሰል አደጋ መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ በተለይ ለኢቲቪ በስልክ እንደገለፁት አደጋዎቹ የደረሱት በአቃቂ፣ ቦሌ እና የካ ክፍለ ከተሞች ነው፡፡

አደጋዎቹ የደረሱት እግረኞች መንገድ በማቋረጥ ላይ ባሉበት ወቅት መሆኑን የገለፁት ባለሙያው የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ባለሥልጣን በዋዜማውም ሆነ በዛሬው ዕለት ምንም አይነት የእሳት አደጋ #አለመከሰቱን ገልጿል፡፡

በአዲሱ ዓመት ሕብረተሰቡ ከተለያዩ አደጋዎች እራሱን እንዲጠብቅና ጥንቃቄ እንዲያደርግ መስሪያ ቤቶቹ አሳስበዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከትላንት በስቲያ ማምሻው አዲስ አበባ ከተማ የጣለው #ከባድ_ዝናብ የአንድ ሰው ሕይወት አጥፍቷል፤ በተለያዩ አካባቢዎችም የንብረት ጉዳት አድርሷል ተብሏል።

Via #ሸገር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 9 ደርሰዋል!

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ሁኔታን አስመልክቶ በጤና ሚንስቴር በተሰጠ መግለጫ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9 ደርሰዋል።

መጋቢት 10 ከተያዙት ውስጥ ፡-

- የ44 ዓመት ጃፓናዊ (ከዚህ ቀደም ከተያዙት ጃፓናዊ ጋር ንክኪ የነበራቸው)

- የ85 ዓመት እድሜ ያላቸው ኢትዮጵያዊ (ከውጪ ከመጡበት ከየካቲት 23/2012 ዓ/ም ጀምሮ ራሳቸውን ለይተው ሲከታተሉ የነበሩ)

- ሶስተኛው የ39 ዓመት አውስትራሊያዊ ዜጋ ሲሆን በመጋቢት 6/2012 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ ተገቡ ናቸው።

ሁለቱ ታማሚዎች በጥሩ ጤንነት ላይ ሲሆኑ የ85 ዓመት ዕድሜ ታማሚ ግን #ከባድ የሚባል ህመም ቢኖራቸውም አስፈላገው ክትትል እየተደረገላቸው ነው

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

መንገዱ ተከፍቷል።

በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዛሬ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝን ጠቅሶ ፋና ብሮድካስት ዘግቧል።

በኢንተርፕራይዙ የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ ዘሃራ መሃመድ ፤ ኢንተርፕራይዙ በታሪኩ #የመጀመሪያ ሊባል የሚችል #ከባድ የትራፊክ አደጋ ነው ባሳለፍነው ጥር 8 ቀን ያስተናገደው ብለዋል።

ይህን ተከትሎ የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዝግ ተደርጎ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱን ወደ ቦታው ለመመለስና መንገዱን ለተጠቃሚዎች ክፍት ለማድረግ ከጽዳት ሰራተኞች ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ባለሞያዎች ርብርብ ሲደረግ መቆየቱንም ጠቁመዋል፡፡

በዛሬው ዕለት 3፡30 ጀምሮም የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US አሜሪካ በአስከፊው ጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት አስራው የነበረችውን አልጄሪያዊ ወደ ሀገሩ መለሰች። አሜሪካ በሀገሯ ውስጥ የ "ቦምብ ጥቃት ለማድረስ አቅደሃል" ብላ ለ20 ዓመታት ገደማ ያሰረችውን ሱፊያን ቡርሃሚ የተባለ አልጄሪያው ወደ ሀገሩ እንዲመለስ አድርጌዋለሁ ብላለች። በአስከፊው ጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት አሜሪካ አስራ ያቆየችው እና አሁን መልሸዋለሁ ያለችው አልጄሪያዊ በፈረንጆቹ 2002 ፓኪስታን…
#አሜሪካ

አሜሪካ ያለ አንዳች ፍርድ ለ20 ዓመታት በ " ጓንታናሞ ቤይ " በሚገኘው እስር ቤት አስራ የቆየቻቸውን ሁለት ፓኪስታናውያን ወንድማማቾችን ከእስር ስለመልቀቋ ተነግሯል።

ጓንታናሞ ቤይ ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ወታደራዊ እርስ ቤት ውስጥ ለ20 ዓመታት ያህል ታስረው የቆዩት ሁለቱ ፓኪስታናውያን ወንድማማቾች ምንም ክስ ሳይቀርብባቸው ነው የተለቀቁት።

አብዱል እና ሞሐመድ አህመድ ራባኒ ፓኪስታን " ካራቺ " ውስጥ ተይዘው ከአገራቸው የተወሰዱት በአውሮፓውያኑ በ2002 ነበር።

የአሜሪካ መከላከያ መ/ቤት አብዱል ራባኒ የተባለው ግለሰብ የ " አልቃኢዳን የመደበቂያ ቤት ያስተዳድራል " እንዲሁም ወንድሙ " የቡድኑ መሪዎችን ጉዞ እና ገንዘብን ይመራል " ብሎ ነበር።

ወንድማማቾቹ ወደ ጓንታናሞ ከመሸጋገራቸው በፊት ከአገራቸው ውጪ በሲአይኤ (CIA) መኮንኖች #ማሰቃየት እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል።

ሁለቱ ፓኪስታናውያን ከአስፈሪው ወታደራዊው እስር ቤት ከተለቀቁ በኋላ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል ተብሏል።

ጓንታናሞ ኩባ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የአሜሪካ ባሕር ኃይል ሰፈር ከመስከረም 11 የሽብር ጥቃት በኋላ ተጠርጣሪዎችን ለማቆያነት በቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ የተቋቋመው ነው።

ካምፑ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት አሜሪካ ካካሄደችው " ፀረ ሽብር ጦርነት " ጋር በያያዘ ከተፈጸሙ መጥፎ ድርጊቶች ጋር ስሙ ይነሳል።

በተለይ ተጠርጣሪዎች በምርመራ ጊዜ #ከባድ_ሰቆቃ እንደተፈጸመባቸው እና ያለፍርድ ለረጅም ጊዜ በእስር እንዲቆዩ መደረጋቸው ይነገራል።

ከ20 ዓመት በፊት በጓንታናሞ ውስጥ 680 አስረኞች የነበሩት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ግን 32 እስረኞች ብቻ የሚገኙበታል።

#BBC

@tikvahethiopia
#ቁልቢ

ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር ወደ ስፍራው የሚመጡ ምዕመናንና እንግዶችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅት ማድረጉን ፖሊስ አሳውቋል።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ እና የበዓሉ የጸጥታ ኮማንድ በመጪው ረቡዕ በሚከበረው ዓመታዊ የቁልቢ ንግስ በዓል ላይ ከተለያየ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ብዛት ያላቸው ምዕመናን፣ ቱሪስቶችና ሌሎችም እንግዶች ወደ ስፍራው እንደሚመጡ ይጠበቃል ብለዋል።

የምዕመናኑን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅም ከምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፣ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ ከሐረሪ ክልል እና ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከመከላከያ ሠራዊት፣ ብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ጋር በመቀናጀት ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

የበዓሉ ታዳሚዎች የግል ንብረቶቻቸውን እንዳይሰረቅ በጥንቃቄ በመያዝና የወንጀል ድርጊት ሲመለከቱ በማጋለጥ የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ተብሏል።

በንግስ በዓሉ ላይ ሶስት ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያና ተጠርጣሪ ወንጀለኞችም ሲያዙ ውሳኔ ለመሰጠት ዐቃቤ ህግና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ተቋቁሟል።

ወደ ስፍራው በሚያመራው መንገድ አልፎ አልፎ ያለው አካባቢ የመሬቱ አቀማመጥ ዳገታማ፣ ቁልቁለታማና ጠመዝማዛ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግና ደንብ በማክበር አደጋን ለመከላከል የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል።

ከዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ባለው ዋናው የተሸከርካሪ መንገድ ላይ #ከባድ_መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑንም ተገልጿል።

ምዕመናን ወደ ንግስ ስፍራው በሚመጡበት ወቅት ተገቢነት የሌላቸው አርማና ምልክቶችን ይዘው መገኘት እንደሌለባቸውም ፖሊስ አሳስቧል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia
#AmanuelMentalHospital

ወደ አማኑኤል ሆስፒታል የሚገቡ የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው።

ሆስፒታሉ አዳዲስ ታካሚዎች እየጨመሩ መጥተዋል ብሏል።

አማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምን አለ ?

- ከሚመጡ ታካሚዎች ከሴቶች በበለጠ ወንዶች ትልቁን ቦታ ይይዛሉ።

- ከሆስፒታሉ ደህና ሆነው ወጥተው ከወጡም በኋላ ያለው ሁኔታ የተስተካከለ ስለማይሆንላቸው ተመልሶ የማገርሸት እና ተመልሶ የመምጣት ነገር እየጨመረ ይገኛል።

- አንድ ክፍተት እየፈጠረ ያለው የተጠኑ ጥናቶች ባለመኖራቸው መንግስትም ትኩረት እየሰጠው ባለመሆኑ ነው።

- ወደ ሆስፒታል የሚመጡ አብዛኞቹ ታካሚዎች ፦
° #ድባቴ
° #ባይፖላር
° #ከባድ_የአእምሮ_ህመም
° #በአደንዛዥ_እፅ_ሱስ ሳቢያ የሚመጣ የአዕምሮ ህመም የተጠቁ ናቸው።

- በሆስፒታሉ ከሚታከሙ ታካሚዎቸ ውስጥ በብዛት ከ20-40 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ቁጥራቸው ከፍ ይላል።

- የሆስፒታሉ ግንባታ በጣም የቆየና ደረጃውን የጠበቀ ባለመሆኑ በተደጋጋሚ የአልጋ እጥረቶች እየገጠሙ ነው።

- ለሚፈጠሩት ክፍተቶች እንደማስተንፈሻ እንዲሆን በጤና ሚኒስቴር አማካኝነት በሆስፒታሉ ግቢ ሌላ ህንፃ ለመገንባት መሰረተ ድንጋይ ተጥሏል። በአንድ አመት ግዜ ውስጥ ያልቃል ተብሎ እቅድ ተይዟል።

- የአእምሮ ህመም ታክሞ መዳን የሚችል በመሆኑ ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል።

የዚህ መረጃ ባለቤት ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia