የኢትዮ ቴሌኮም የምስጋና ስጦታ !
ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹ ከዛሬ ነሃሴ 21 እስከ 23 ለሶስት ቀን በተከታታይ ከጥዋቱ 12:00 እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ፦
- የ1 ጊጋ ባይት (በቀን 341 ሜ.ባ)
- የ40 ደቂቃ የሀገር ውስጥ ድምፅ ጥሪ (በቀን 13 ደቂቃ)
- የ100 የሀገር ውስጥ SMS (በቀን 33 መልዕክት) ስጦታ እንዳበረከተ መግለፁ ይታወቃል።
ነገር ግን በርካታ ሰዎች የ1 ጊጋ ባይት ኢንተርኔት ስጦታው እንዳልደረሳቸው/እንዳልሰራላቸው/ እስካሁንም ከሞሉት ካርድ ላይ ሲቆርጥ እንደነበር አሳውቀዋል፣ አሁንም እያሳወቁ ይገኛሉ።
ውድ ቲክቫህ አባላት በዚህ ጉዳይ ከኢትዮ ቴሌኮም ማብራሪ ጠይቀን ለጊዜው ምላሽ አላገኘንም፤ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የሚሰጥ ማብራሪያ ስናገኝ እናሳውቃችኃለን።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የትምህርት ቤት ክፍያ የተጨመረባቸውና የአከፋፈል ስርዓቱ የተቀየረባቸው የተማሪ ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵየ ቅሬታቸውን አሰምተዋል!
ትላንት ነሃሴ 20/2012 ጀምሮ የ2013 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መጀመሩን ተከትሎ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የወራዊ ክፍያ ጭማሪ እንዲሁም የአከፋፈል ሥርዓቱ እንደተቀየረ ቅሬታቸውን አድርሰውናል፡፡
እኛም ይህንን የወላጆች ቅሬታ ለትምህርት ሚኒስቴር አቅርበናል፡፡ ድርጊቱ ተገቢነት የሌለውና አስፈላጊው ክትትል የሚደረግበት እንደሆነ የነገሩን በሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሯ ወይዘሮ ሀረጓ ማሞ ናቸው፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ ትምህርት ቤቶች ከዚህ ቀደም ሲያስከፍሉበት በነበረው መሰረት( የወር ሲያስከፍሉ የነበሩ የወር፣ የተርም ሲያስከፍሉ የነበሩ የተርም) የክፍያ ሥርዓታቸውን ሳይቀይሩ ምዝገባውን ማካሄድ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘም በ2012 ከነበረው ክፍያ ላይ ጭማሪ ማድረግ እንዳልተፈቀደ የገለጹ ሲሆን ወላጆች እንዲህ አይነት ችግር ካጋጠማቸውም በአከባቢው ወዳለ ትምህርት ቢሮ ማመልከት ይችላሉም ብለዋል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም መግለጫ እንደሚሰጡም ነግረውናል፡፡
ጉዳዩን ወደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም አቅርበን ነበር፡፡ የቢሮው የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አበበ ቸርነት በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠ አቅጣጫ መኖሩን የገለጹ ሲሆን ቅሬታ ያላቸው ሰዎች ቅሬታቸውን ከወረዳ ጀምሮ ባሉ መዋቅሮች ማቅረብ ይችላሉ ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ባሉ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ በወላጆች በተነሱት ቅሬታዎች ላይ በቢሮው የተያዘ አቅጣጫ እንዳለ የጠየቅናቸው አቶ አበበ 'ቅሬታ ያላቸው አካላት መዋቅሩን ተከትሎ ቢያቀርቡ መፍትሔ ያገኛሉ' ሲሉ ነው ምላሻቸውን የሰጡን፡፡

ነሃሴ 21/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦
#Somali
በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 524 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 44 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።
#Oromia
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 4,124 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 134 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 29 ከጉጂ
- 22 ከፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን
- 12 ከአሰላ ከተማ
- 12 ከምዕራብ ሀረርጌ
- 11 ከምስራቅ ሸዋ
- 11 ከምስረቅ ሀረርጌ
- 5 ከቢሾፍቱ ከተማ
- 5 ከነቀምቴ ከተማ ይገኙበታል።
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 348 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 36 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት መካከል ፦
- 17 ከማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ
- 5 ከአሶሳ ከተማ
- 5 ከባንቢስ ወረዳ
- 3 ከጉባ ወረዳ
- 3 ከዛይ (ያሶ) ወረዳ ይገኙበታል።
#DireDawa
ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 341 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 28 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Harari
በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 805 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 28 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Amhara
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 3,630 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 50 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 21 ከምዕ/ጎንደር ዞን
- 14 ከጎንደር ከተማ
- 5 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 4 ከደሴ ከተማ ይገኙበታል።
@tikvahethiopiaBot

ባለፉት 24 ሰዓት የ20 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ 1,186 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,060 የላብራቶሪ ምርመራ 1,186 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 518 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 46,407 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 745 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 16,829 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,060 የላብራቶሪ ምርመራ 1,186 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 518 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 46,407 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 745 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 16,829 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 21/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦
#SNNPRS
በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1,681 የላብራቶሪ ምርመራ 88 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት ፦
- ከጎፋ 26 (መለኮዛ ወረዳ 16፣ ሳውላ ከተማ 6፣ ኡባ ደብረጸሀይ 4)፣
- ከጌዴኦ 21 (ዲላ 12፣ ወናጎ ወረዳ 5፣ ይረጋጨፌ 2፣ ገደብ 1 እና ቡሌ 1)፣
- ከአማሮ 10፣
- ከወላይታ 9 (ዳሞት ጋሌ 4፣ ኪንዶ ኮይሻ 2፣ ሻንቶ 2 እና ከቢጠና 1)፣
- ከጋሞ 6 (ቁጫ አልፋ 3፣ አርባምንጭ 2 እና ገረሴ 1)፣
- ከጉራጌ 6 (አበሸጌ 3 እና እንደጋኝ 3) ፣
- ከሸካ 6 (6ቱም ከማሻ ከተማ) ፣
- ከኮንሶ 2 (2ቱም ከካራት ከተማ)
- ከስልጤ 1(ሁልባረግ) ፣
- ከባስኬቶ 1 ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ናቸው፡፡
አጠቃላይ በደቡብ ፦
- 1,046 በቫይረሱ የተያዙ
- 9 ሞት
- 406 ያገገሙ
#Sidama
በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 405 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 36 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 28 ከሀዋሳ ከተማ
- 4 ከማልጋ ይገኙበታል።
አጠቃላይ በሲዳማ ፦
- 1,327 በቫይረሱ የተያዙ
- 15 ሞት
- 460 ያገገሙ
#Afar
በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 462 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 41 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
አጠቃላይ በአፋር ፦
- 883 በቫይረሱ የተያዙ
- 231 ያገገሙ
@tikvahethiopiaBOT

የ4 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው አሳዛኙ አደጋ!
የኦሞ ወንዝ ሞልቶ ዉኃ ከከባቸዉ መንደሮች ለማምለጥ የሞከሩ አራት የደቡብ ክልል ፤ የዳሰነች ወረዳ ነዋሪዎች ሞቱ።
የአካባቢዉ ባለስልጣናት ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ እንዳሳወቁት አራቱ ሰዎች በዉኃ የተበሉት ዉኃ ከከበባት ቶል-ታሌ ቀበሌ ወደ ደረቅ መሬት በጀልባ ለመሻገር ሲሞክሩ ጀልባቸዉ ተገልብጣ ነዉ።
ከሟቾቹ ሁለቱ እናት እና ልጅ ሁለቱ ደግሞ አዛዉንቶች ነበሩ።
በውኃ ተከበው የነበሩ ሌሎች 200 ነዋሪዎች ግን ከክልሉ በተላኩ ጀልባዎች ርዳታ ሙሉ በሙሉ ወደ ደረቅ አካባቢ መሻገራቸዉን ተሰምቷል።
የኦሞ ወንዝ ሙላት ከዳሳች ወረዳ አርባ (40) ቀበሌዎች መካከል 28ቱን አጥለቅልቋል። ከ15 ሺሕ በላይ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸዉ አፈናቅሏል።
የዉኃ ሙላቱ ከ30 ዓመት ወዲሕ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ ያሁኑ የመጀመሪያዉ መሆኑን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
PHOTO : FILE

'ፎሬይን ፖሊሲ' የተሰኘው መፅሄት ትላንት ምሽት እንደዘገበው የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ በከፊል እንድታቆም ፍቃዳቸውን ሰጥተዋል ብሏል።
ይህም የትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ እና ሱዳንን በህዳሴ ግድብ ዙርያ ለማወያየት የጀመረው እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ተቃውሞ ገጥሞት መቆሙን ተከትሎ የመጣ ነው ብሏል።
ፖምፔዎ ፍቃዳቸውን ያኖሩበት ይህ ውሳኔ በዚህ ሳምንት እንደተወሰነ መፅሄቱ ገልፆ በዚህም አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምታደርገው ድጋፍ ውስጥ 130 ሚልዮን ዶላሩን ልትቆርጥ አስባለች ብሏል።
ለፀጥታ እና ደህንነት ፣ ለፀረ-ሽብር እንቅስቃሴ ፣ ለወታደራዊ ስልጠና ፣ ለሰዎች ዝውውር ቁጥጥር እና ሌሎች ልማት ስራዎች የሚውሉ ድጋፎች ሊቋረጡ ከሚችሉት ውስጥ ተካተዋል ተብሏል።
በሌላ በኩል ዘገባው አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፎች እንዲሁም የጤና እርዳታዎች አይቋረጡም ብሎ የኮንግረስ ምንጮቹን ጠቅሶ ፅፏል።
https://foreignpolicy.com/2020/08/27/trump-africa-gerd-dam-us-halts-foreign-assistance-funding-ethiopia-over-dam-dispute-egypt-sudan/
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት (AP)

#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በበይነ መረብ (Virtual) ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ ያስቻላቸው የድህረ ምረቃ (ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ) ተማሪዎቹን ፣ እንዲሁም ከኮሮና ወረርሽኝ መከሰት በፊት ትምህርታቸውን አጠናቀው ምረቃቸው በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ በወረርሽኙ ምክንያት የምረቃ ስነ-ስርዓቱ ሳይካሄድ የቆዩትን በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛና መደበኛ ያልሆኑ መርሃ-ግብሮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ነገ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም በበይነ መረብ (Virtual) ስነ-ስርዓት ያስመርቃል፡፡

የአሜሪካ የሥራ ሚኒስቴር እንደገለፀው ባለፈው ሳምንት 1ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች፣ የሥራ እጥነት ድጎማ ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።
ይህም የአሜሪካ አሰሪዎች ፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ፣ ሰራተኞችን ማስወጣት እንደቀጠሉ ያመለክተል ተብሏል።
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፣ በየሳምንቱ የሥራ አጥነት ማመልከቻ የሚያስቡት ሰዎች ብዛት፣ አንድ ሚሊዮን ገደማ ይሆናል።
የቫይረሱ ወረርሽኝ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ከማዳከሙ በፊት ከነበረው፣ በ200,000 ከሚገመት የሥራ አጥነት ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ግን፣ የበዛ እንደሆነ ተገልጿል።
Via VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ይህም የአሜሪካ አሰሪዎች ፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ፣ ሰራተኞችን ማስወጣት እንደቀጠሉ ያመለክተል ተብሏል።
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፣ በየሳምንቱ የሥራ አጥነት ማመልከቻ የሚያስቡት ሰዎች ብዛት፣ አንድ ሚሊዮን ገደማ ይሆናል።
የቫይረሱ ወረርሽኝ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ከማዳከሙ በፊት ከነበረው፣ በ200,000 ከሚገመት የሥራ አጥነት ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ግን፣ የበዛ እንደሆነ ተገልጿል።
Via VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ ዳይክተሮች እና የስራ ክፍሎች ተወካዮች በተገኙበት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2012 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2013 ዓ.ም እቅድ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#Tigray #AddisAbaba #COVID19
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የነሃሴ 21 ሪፖርት እንደሚያሳየው በከተማው 640 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ህይወታቸው ካለፈው 17 ሰዎች መካከል 10 ሰዎች በአስክሬን ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን 7 ሰዎች ከጤና ተቋም ናቸው።
በሌላ መረጃ፦
የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የነሃሴ 21/2012 ሪፖርት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም ከ706 የላብራቶሪ ምርመራ 56 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ 101 ሰዎች አገግመዋል።
ከነዚህ 56 ሰዎች መካከል 22 ለይቶ ማቆያ ማዕከል የነበሩ ፣ 5 በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ፣ 29 የጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው።
እስከሁን ድረስ በትግራይ ክልል 44,600 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 3,552 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ ከነዚህ መካከል የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል ፣ 2,184 ሰዎች አገግመዋል።

ችሎት!
ፍርድ ቤት አርቲስትሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል በተጠረጠሩት ከበደ ገመቹ እና አብዲ ዓለማየሁ ላይ አቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰርት የ15 ቀን ጊዜ ሰጠ።
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ ምርመራዬን አጠናቅቂያለሁ ብሎ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ አስረክቧል።
በችሌቱ አንደኛው ተጠርጣሪ አብዲ ዓለማየሁ ሃጫሉ ሁንዴሳ በተገደለበት ወቅት በቦታው አልነበርኩም ያለ ሲሆን ሌላኛው ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚ በበኩሉ አርቲስቱ ሲገደል ከበደ ገመቹና አብዲ ዓለማየሁ አብረውት እንደነበሩ አስረድቷል።
በዚሁ መሰረትም ፍርድ ቤቱ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የክስ መመስረቻ አስራ አምስት (15) ቀን ጊዜ መጠቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ከነሃሴ 26/2012 ዓ/ም ጀምሮ በኳታር የግል የትምህርት ተቋማት እና ስልጠና ማዕከላት እስከ 50 በመቶ አቅማቸው መንቀሳቀስ ይጀምራሉ።
የኳታር መንግስት የኮሮና ቫይረስ የአራተኛ ደረጃ (Phase Four) ማሻሻያዎች በሁለት ዙር ተግባራዊ እንደሚደረጉ ማሳወቁ ይታወቃል።
የመጀመሪያው ዙር ከነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም (01 September 2020) የሚጀምር ይሆናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኳታር መንግስት የኮሮና ቫይረስ የአራተኛ ደረጃ (Phase Four) ማሻሻያዎች በሁለት ዙር ተግባራዊ እንደሚደረጉ ማሳወቁ ይታወቃል።
የመጀመሪያው ዙር ከነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም (01 September 2020) የሚጀምር ይሆናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ ከአራተኛ እስከ 14ኛ የተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎላቸው ነፃ መሆናቸውን የሚገልፅ ውጤት ለፍርድ ቤቱ ቀርቧል።
ከዚህ በፊት አቶ ጃዋር መሀመድና አቶ በቀለ ገርባ ከጓደኞቻቸው ጋር መገናኘት አልቻልንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ፍርድ ቤቱ በጓደኛ የመጠየቅ መብት ቢኖራቸውም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚከለክል በመሆኑ አልተቀበለም።
አንደኛ ተጠርጣሪ የሆኑት አቶ ጃዋር መሃመድ ከልጄ እና ከባለቤቴ ጋር በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንድገናኝ ይፈቀድልኝ ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ በሳምንት ሁለት ጊዜ በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንዲገናኙ አዟል።
12ኛ ተጠርጣሪ የሆኑት አቶ ሸምሰዲን ጣሃ ጆሮዬን ታምሚያለሁ የተሻለ ሆስፒታል ልታከም ብለው አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤት በመረጡት ሆስፒታል እንዲታከሙ እንዲመቻችላቸው አዟል።
ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ ቀሪ ምስክሮችን ለማድመጥ ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Via Tarik Adugna (ኤፍ ቢ ሲ)

#EZEMA
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ነሐሴ 22/2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሔዱ የመሬት ወረራዎችን እና ኢ-ፍትሀዊ የሆነ የመኖሪያ ቤቶችን ክፍፍል በሚመለከት በራስ ሆቴል ሊሰጥ የነበረው መግለጫ በፖሊስ መበተኑን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል።
የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ናትናኤል ፈለቀ እንደተናገሩት ከቀናት በፊት ስለስብሰባው ለሰላም ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው ሁሉ በደብዳቤ ያሳወቁ ቢሆንም ዛሬ ነሐሴ 22/2012 በራስ ሆቴል ሊሰጥ ነበረው መግለጫ ግን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስለ መግለጫው መረጃ የለኝም በሚል መግለጫው እንዳይካሔድ መከልከሉ ታውቋል።
Via Addis Maleda

በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደር በወንዝ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ የባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በጎርፍ በመውደቁ ምክንያት ከትናንት እኩለ ቀን ጀምሮ የተቋረጠውን ኃይል ለመቀጠል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
የአካባቢው መስመር ከኮተቤ ከሚወጣ መስመር ጋር በጊዜያዊነት በማገናኘት እስከ ማምሻው ድረስ ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።