TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዩኤኢ (UAE) ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ለመምህራኖቿ የኮሮና ምርመራ እያደረገች ነው!

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶች ከመመለሳቸው አስቀድማ የግል ትምህርት ቤት መምህራንን እየመረመረች ነው፡፡

205 የግል ትምህርት ቤቶች በሚገኙባት አቡዳቢ ከ15 ሺ የሚበልጡ መምህራን ተመርምረዋል፡፡

ምርመራው ሁሉንም የትምህርት ተቋማቱን መምህራን እና የስታፍ አባላት እስኪያዳርስ ድረስ እንደሚቀጥልም ነው ዘ ናሽናልን ዋቢ አድርጎ አል አይን የዘገበው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 22/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 725 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 34 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በሱማሌ፦
- 1,128 በቫይረሱ የተያዙ
- 23 ሞት
- 693 ያገገሙ

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,642 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 255 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 58 ከምዕራብ ሀረርጌ
- 54 ከምዕራብ አርሲ
- 23 ከሰሜን ሸዋ
- 17 ከለገጣፎ ከተማ
- 16 ከአዳማ ከተማ
- 15 ከሞጆ ከተማ
- 14 ከጉጂ ይገኙበታል

አጠቃላይ በኦሮሚያ ፦
- 5,843 በቫይረሱ የተያዙ
- 42 ሞት
- 1,762 ያገገሙ

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 266 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 19 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት መካከል ፦
- 1 ከቡለን ወረዳ
- 3 ከአሶሳ ከተማ
- 10 ከማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ
- 3 ከባንቢስ ወረዳ ይገኙበታል።

አጠቃላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፦
- 546 በቫይረሱ የተያዙ
- 274 ያገገሙ

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 376 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 97 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 3,972 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 143 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 42 ከሰ/ወሎ ዞን
- 31 ከዋግ ኽምራ ብ/ሰብ ዞን
- 19 ከጎንደር ከተማ
- 12 ከባህር ዳር ከተማ
- 9 ከደሴ ከተማ ይገኙበታል።

@tikvahethiopiaBot
ባለፉት 24 ሰዓት 1,733 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,766 የላብራቶሪ ምርመራ 1,733 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 586 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 48,140 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 758 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 17,415 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 22/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,604 የላብራቶሪ ምርመራ ሃምሳ አራት (54) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት ፦

- ከጌዴኦ 12 (ዲላ 7፣ ይርጋጨፌ 3፣ ወናጎ 2) ፣
- ከደቡብ ኦሞ 11 (ጂንካ 5፣ በናፀማይ 4፣ ሀመር 1፣ ማሌ 1)፣
- ከወላይታ 10 (ዳሞት ወይዴ 9 ፣ ሶዶ 1)፣
- ከከምባታ ጠምባሮ 8 (ዱራሜ 5፣ አዲሎ ዙሪያ ወረዳ 2 እና ዳንቦያ 1)፣
- ከጉራጌ 5፣ ከጋሞ 2 (1 ቦረዳ 1 አርባምንጭ) ፣
- ከምዕራብ ኦሞ 2 (2ቱም ከሜኒት ጎልዲያ)
- ከደራሼ 2 ፣
- ከጎፋ 1 (ዛላ) እና ሃላባ 1 ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ናቸው፡፡

አጠቃላይ በደቡብ ፦
- 1,100 በቫይረሱ የተያዙ
- 9 ሞት
- 453 ያገገሙ

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 523 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 32 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት ሁሉም (32) ከሀዋሳ ከተማ ናቸው።

አጠቃላይ በሲዳማ ፦
- 1,359 በቫይረሱ የተያዙ
- 15 ሞት
- 502 ያገገሙ

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 294 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 6 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በድሬዳዋ ፦
- 911 በቫይረሱ የተያዙ
- 20 ሞት
- 751 ያገገሙ

@tikvahethiopiaBOT
በትላንትናው ዕለት (ነሃሴ 21/2012 ዓ/ም) በተለያዩ ሚዲያዎች "በችግር ውስጥ የሚገኙ ከ25 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያና ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ወደ አገራቸው ሊመለሱ ነው" በሚል የተሰራጨው መረጃ ስህተት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቆናል።

በውጭ ያሉ ዜጎችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ፣ የረድኤት ድርጅቶች እንዲሁም የሚኖሩባቸው ሀገራት መንግስታት እየደገፉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም ከየሀገራቱ መንግስታት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

'ከ25 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ሊመለሱ ነው' የሚለው መረጃ ከኢዜአ የተወሰደ ሲሆን መረጃው ትላንት (በፌስቡክ ገፃቸው እና ድረ ገፃቸው) ተስተካክሏል።

@tikvahethmagazine ላይ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ምንጭ አድርገን የተለዋወጥነው መረጃም ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ አድርገናል። ሌሎች የሚዲያ ተቋማትም የኢዜአን መረጃ ዳግም ተመልክታችሁ መረጃችሁን ማስተካከል ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን የእስረኞች አስተዳደር ኃላፊ በፖሊስ ተይዘው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ትዕዛዝ መስጠቱን #BBC አስነብቧል። ፍርድ ቤቱ ኃላፊው በ24 ሰዓት ተይዘው እንዲቀርቡ ነው ትዕዛዝ የሰጠው።

ይህ ትዕዛዝ የተሰጠው በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ ውስጥ ያሉ የOMN ጋዜጠኛ መለሰ ድሪብሳና ሌሎች አራት (4) ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤት እንዲያመጡ የተሰጠው ተደጋጋሚ ትዕዛዝ ተፈፃሚ ባለመሆኑ ነው።

ፍርድ ቤቱ ነሐሴ 20/2012 ዓ/ም በነበረው ችሎት ላይ ተጠርጣሪዎቹ ለምን የኮቪድ-19 ምርመራ እንዳልተደረገላቸው ኃላፊው ፍርድ ቤት መጥተው ያስረዱ ቢልም አስተዳዳሪው ዛሬ በነበረው ችሎት ላይ ሳይቀረቡ ቀርተዋል፣ ተወካይም አላኩም ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 በሽታ ህክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችሉ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. በቤት ሆኖ የኮቪድ-19 ህክምና ለማግኘት ፍቃደኛ የሆነ፣

2. ቀላል ወይም ምንም አይነት የኮቪድ-19 ምልክት የሌለበት፣

3. በቤት ውስጥ የቆይታ ጊዜ አጋዥ ወይም ረዳት ያለው እንዲሁም እራሱን መርዳት የሚችል፣

4. የምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማግኘት ወይም ማሟላት የሚችል፣

5. በተመሳሳይ ቤት ውስጥ የሚኖር ሌላ ሰው የግል ንፅህና መጠበቂያዎችን እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ ማሸፈኛ ጭንብሎችን ማግኘት የሚችል እንደሆነ፣

6. ኮቪድ-19 የተገኘበት ሰው ከሌሎች ተዷጋኝ በሽታዎች ማለትም የልብና የደም ቧንቧ በሽታ ፣ የስኳር በሽታ፣ አስም፣ ኤች አይቪ፣ ቲቢ፣ ካንሰርና የመሳሰሉት በሽታዎች ካሉባቸው ሰዎች ጋር አብሮ የማይኖር ከሆነ፣

7. የኮቪድ-19 የተገኘበት ሰው ከቤት ላለመውጣት ወይም ማናቸውም ጠያቂ ወደቤት እንዳይመጣ ለማድረግ ማረጋገጫ የሚሰጥ ከሆነ፣

8. እራሱን ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ለይቶ ማቆየት የሚያስችል ክፍል ወይም ከቤተሰብ አባላት በ2 ሜትር ርቀት ላይ መቆየት የሚያስችል ክፍል ያለው እንደሆነ፣

9. በጤና ቡድን በቋሚነት ለመደገፍ ፈቃደኛ የሆነ፣

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Tigray #COVID19

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የነሃሴ 22/2012 ሪፖርት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም ከ418 የላብራቶሪ ምርመራ 63 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል፤ ተጨማሪ 139 ሰዎች አገግመዋል።

በቫይረሱ ከተያዙት 63 ሰዎች መካከል 15 ለይቶ ማቆያ ማዕከል የነበሩ ፣ 7 በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ፣ 41 የጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው።

እስከሁን ድረስ በትግራይ ክልል 45,018 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 3,615 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ ከነዚህ መካከል የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል ፣ 2,323 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትላንት (ነሃሴ 22/2012 ዓ/ም) ስብሰባ አካሂደዋል።

በስብሰባ ሂደቱ ታዛቢ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ፣ አውሮፓ ህብረት እና የአሜሪካ ተወካዮች እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት የወከላቸው ባለሞያዎች ተገኝተው ነበር።

በስብሰባው ላለፈው አንድ ሳምንት በሃገራቱ ባለሙያዎች በትላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሞላል እና ውሃ አለቃቀቅ ደንብ ላይ ሲከናወን የነበረው የባለሙያዎች ድርድር ሪፖርት ቀርቧል። የሃገራቱ ባለሙያዎች ከነሃሴ 15 ጀምሮ በበይነ መረብ ስብሰባቸውን አካሂደዋል።

በቀጣይ በሚኖረው ሂደት በሚመለከት ሃገራቱ የድርድሩ ሂደት የሚገልጥ ደብዳቤ ለደቡብ አፍሪካዋ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ናዴሊ ፓንዶር ለመላክ ተስማምተዋል።

በዚህ መሰረት ሱዳን የምትሰጠው ማረጋገጫ የሚጠበቅ ሆኖ የሶስትዮሽ ስብሰባው መስከረም 4 እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
CONGRATULATIONS!

ዛሬ ባህር ዳር እና ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ መርሃ ግብር ያሰለጠኗቸውን 12 ሺህ 300 ተማሪዎችን አስመርቀዋል።

ከዚህ ውስጥ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 780 ተማሪዎችን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አስመርቋል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 520 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

PHOTO : FANA BROADCASTING
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ መንደር እና አካባቢው የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ማምሻውን እንዲያገኝ መስመሩን ለመቀጠል ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ሃይል ለኢዜአ አስታውቋል።

ኃይል የተቋረጠው የክረምቱ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ መንደር አካባቢ አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በመውደቁ መሆኑ ትላንት ተገልጿል።

የወደቀውን የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶ በሌላ የመተካት ስራው ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ የአካባቢውን መስመር ከኮተቤ ከሚወጣው መስመር ጋር በጊዜያዊነት በማገናኘት ዛሬ ማምሻውን ኃይል እንዲያገኝ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

መስመሩን አገናኝቶ ሃይል ለመልቀቅ የሚከናወናው ስራ ትናንት ማምሻውን ለማጠናቀቅ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ በጣለው ከባድ ዝናብ ማጠናቀቅ ሳይቻል ቀርቷል።

በዛሬው እለት መስመሩ ተስተካክሎ አካባቢው የኤሌክትሪክ ሃይል እንደሚያገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጳጉሜ 5/2012 ዓ.ም ሥራ ይጀምራል የተባለውን የአዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታልን ምክትል ጠቅለይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር በመሆን መጎብኘታቸውን የጤና ሚስቴር አስታውቋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለኮቪድ 19 ሕክምና አገልግሎት እየተዘጋጀ ያለው የአዲስ አበባ ኮቪድ 19 ፊልድ ሆስፒታል በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስር በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት በዓለም ምግብ ፕሮግራም እና በዓለም ጤና ድርጅት ድጋፍ የተሠራ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብሱን ሊቀይር ነው! የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ እንደሚቀየርና ጉዳዩን አስመልክቶ በመጪው ቅዳሜ ሰፊ ማብራሪያ በኮሚሽኑ እንደሚሰጥ ለኢዜአ ገለፁ። ለደንብ ልብሱ መቀየር አሁን ያለው የደንብ ልብስ በቀላሉ የሚገኝ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነ ምግባር ችግር የተባበሩ ፖሊሶች ልብሱን ለብሰው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በምክንያትነት…
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዲሱን የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል!

አዲሱ የደንብ ልብስ ይፋ በተደረገበት ሥነ-ሥርዓት ላይ በእንግድነት የተገኙት የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል የፖሊስ የደንብ ልብስን መቀየር እንደ ሀገር የተጀመረው ሪፎርም አካል መሆኑን ገልፀዋል።

PHOTO : EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FederalPoliceCommission

በጉለሌ ክፍለከተማ ከመሬት ጋር በተያያዘ አገልግሎት ለማግኘት ወደ መስሪያ ቤቱ የሄዱ ተገልጋዮችን ጉዳይ እናስፈጽማለን በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ ከተዘረጋው ሰንሰለት በተጨማሪ ደላሎችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ከተገልጋዮቹ ጋር በመሆን ባደረገው ተከታታይ ክትትል በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት እንዲከፈላቸው የጠየቁትን ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ህብረተሰቡም በህጋዊ መንገድ ማግኘት የሚችለውን አገልግሎት ገንዘብ በመቀበል በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት አካላትን በማጋለጥ ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

የወንጀል ድርጊቱን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎች በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በኩል ለህዝብ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል ተብሏል።

ምንጭ፦ #MayorofficeAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia