TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የነባርና አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ከነገ ነሐሴ 20/2012 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

ሁሉም ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን እና ነባር ተማሪዎችን በማስመዝገብ ሂደት ወላጆች ኃላፊነታቸው እንዲወጡ ተጠይቋል።

ትምህርት ቤቶች ለመመዝገብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ምዝገባውን ሊያካሂዱ እንደሚገባም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከግምት ውስጥ በማስገባት ምዝገባው ሲካሄድ ተማሪዎች በ2 ሜትር ርቀት ላይ ሆነው እንዲመዘገቡ ፣ ተማሪዎች እና ወላጆች የፊት ማስክ ማድረጋቸውን ትምህርት ቤቶች በመከታተል ምዘገባውን ማካሄድ አለባቸው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶክተር ደብረፅዮን የምርጫ ካርድ ወሰዱ!

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በዛሬው እለት በአደዋ ከተማ በመገኘት የምርጫ ካርድ ተመዝግበው ወስደዋል።

በትግራይ ክልል በሚካሔደው ስድሰተኛው ክልላዊ ምርጫ መራጮች ከነሐሴ 15 ጀምሮ እየተመዘገቡ የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ነው።

የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ትላንት እንዳስታወቀው ከነሐሴ 15 እስከ ነሐሴ18 ባሉት ቀናት ብቻ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበው ካርድ ወስደዋል።

በክልሉ ለሚደረገው ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የሚጠናቀቀው ነሐሴ 22/2012 ዓ.ም ሲሆን ህብረተሰቡ በተቀመጠው ህግና መመሪያ መሰረት በከፍተኛ ተነሳሽነት ተመዝግቦ የምርጫ ካርድ እየወሰደ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል በምርጫው የሚሳተፉ ፓርቲዎች በክልሉ መገናኛ ብዙሃንና ሌሎች የመቀስቀሻ መንገዶች የምረጡኝ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።

ምንጭ፦ አውሎ ሚዲያ
PHOTO : Tigray Mass Media Agency
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaB
በ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ለኢቲቪ ገልጸዋል።

የቀጣዩ ዓመት ትምህርት ምዝገባ ከነገ ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት እና በግል ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ምዝገባ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል ብለዋል።

የበሽታው ሁኔታ እየተስፈፋ ቢሆንም የትምህርት ዝግጅት እና እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ ሆኑ መገኘቱን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ወደ መማር ማስተማር ተግባር በሚገባበት ወቅት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሚሠራ ገልጸው፣ ማስክ፣ የእጅ ማፅጃ እና መሰል አቅርቦቶችን ከባላድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በግልም ሆነ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እንዳይከሰት ተማሪዎች ማስክ በማድረግ፣ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና እጅን በመታጠብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች በ2012 የትምህርት ዘመን በ2ኛ ሴሚስተር ያለፋቸውን ትምህርቶች ማካካሻ ለመስጠት መታሰቡንም ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል #etv

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 19/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 606 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 20 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,578 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 211 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 47 ከምዕራብ ወለጋ
- 33 ከዱከም ከተማ
- 28 ከምስራቅ ሸዋ
- 15 ከፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን
- 11 ከአዳማ ከተማ
- 11 ከምስራቅ ሀረርጌ ይገኙበታል።

አጠቃላይ በኦሮሚያ ፦
- 5,071 በቫይረሱ የተያዙ
- 41 ሞት
- 1,521 ያገገሙ

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 832 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 1 ከምዥጋ (በሎጂጋንፎይ) ወረዳ
- 2 ከሸርቆሌ ወረዳ
- 2 ከማንዱራ ወረዳ
- 1 ከግልገል በለስ ከተማ
- 9 ከባምቢስ ወረዳ
- 3 ከፓዌ ወረዳ
- 1 ከአሶሳ ከተማ ይገኙበታል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 2,101 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 29 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 6 ከሰ/ወሎ ዞን
- 5 ከጎንደር ከተማ
- 4 ከባህር ዳር ከተማ
- 4 ሰ/ሸዋ ዞን ይገኙበታል።

አጠቃላይ በአማራ፦

- 1946 በቫይረሱ የተያዙ
- 21 ሞት
- 828 ያገገሙ

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 212 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 25 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot
የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብሱን ሊቀይር ነው!

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ እንደሚቀየርና ጉዳዩን አስመልክቶ በመጪው ቅዳሜ ሰፊ ማብራሪያ በኮሚሽኑ እንደሚሰጥ ለኢዜአ ገለፁ።

ለደንብ ልብሱ መቀየር አሁን ያለው የደንብ ልብስ በቀላሉ የሚገኝ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነ ምግባር ችግር የተባበሩ ፖሊሶች ልብሱን ለብሰው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በምክንያትነት ጠቅሰዋል።

በዚህም የደንብ ልብሱን በመልበስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችና ዝርፊያዎች መበራከታቸውን ነው ያስታወቁት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ700 አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,778 የላብራቶሪ ምርመራ 1,545 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 534 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 43,688 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 709 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 15,796 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 19/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1,068 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 3 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በሐረሪ ፦
- 877 በቫይረሱ የተያዙ
- 17 ሞት
- 281 ያገገሙ

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,383 የላብራቶሪ ምርመራ 62 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት ፦
- ከጌዴኦ 23 (ዲላ 15፣ ቡሌ 6 እና ገደብ 2)፣
- ከወላይታ 5 (5ቱም ከዳ/ወይዴ)፣
- ከጋሞ 22 ( 5 ከአርባምንጭ፣ 1 ከጨንቻ፣ 16 ምዕራብ አባያ)፣
- ከቤንች ሸኮ 3 (3ቱም ከሚዛን)፣
- ከዳውሮ 1 (ከተርጫ)፣ ከሐድያ 1 ( ከአንሌሞ)፣
- ከኮንሶ 7 (1 ከካራት ከተማና 6 ከካራት ዙሪያ ወረዳ) ዞኖች ናቸው፡፡

አጠቃላይ በደቡብ ፦
- 880 በቫይረሱ የተያዙ
- 9 ሞት
- 360 ያገገሙ

@tikvahethiopiaBOT
#ምክንያትአልሆንም

"ወንዝ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው" --- አንድ (1) ብሎ የጀመረው በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 የሟቾች ቁጥር ዛሬ 709 ደርሷል።

ለራስሽና ለምትወጃቸው ፤ ለራስህ እና ለምትወዳቸው ስትል ይህን አስፈሪ ጊዜ ተሸሽገህ፣ ተጠንቅቀህ ተሻገር / ተሻገሪ!

#ቲክቫህኢትዮጵያ
@TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHIOPIABOT
የዩኒቨርስቲ-ውስጥ-ግጭቶች-2012.pdf
1.8 MB
በዚህ ዓመት በተለያዩ ዩኒቨርሲዎች የተከሰቱ ግጭቶችን አስመልክቶ የመብቶችና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD) ጥቅል ዓመታዊ መግለጫ አዘጋጅቶ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በጥቅምት 30፣ 2012 በወልዲያ ከተከሰተው ግጭት ወዲህ 12 ተማሪዎች ለሞት መዳረጋቸውን፣ ከ58 ተማሪዎች በላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን እና 28 ዩኒቨርሲቲዎች ቀላል እና ከባድ ግጭቶች በማስተናገዳቸው የትምህርት ሒደቱ መስተጓጎሉን በጥንቅሩ ላይ ገልጿል።

ግጭቶቹ የብሔር መልክ ያላቸው ናቸው ያለ ሲሆን፣ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በሐሰተኛ መረጃዎች ግጭቶቹን የማቀጣጠል ሚና እንደተጫወቱም በግምገማው ዳሷል፡፡ ጥንቅሩን ለተጨማሪ ምርመራ እና የመከላከል ሥራ ያግዝ ዘንድ ማዘጋጀቱን ገልጾልናል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነፃ የምርመራ አገልግሎት!

11ኛው የውዳሴ ዳያግኖስቲክ ማዕከል “ጳጉሜን ለጤና” ዘመቻ በይፋ ተጀመረ።

ውዳሴ ዳያግኖስቲክ ማዕከል ባለፉት አስር (10) ዓመታት እንዳደረገው ሁሉ ዘንድሮ ምርመራ እንደሚያስፈልጋቸውና የመክፈል አቅም እንደሌላቸው ታምኖበት በሐኪም ለሚፃፍላቸው ታካሚዎች የነጻ ምርመራ አገልግሎት በጳጉሜ ወር ለመስጠት ዝግጅቱን ጨርሷል።

ይህን አገልግሎት ለማግኘት የምትፈልጉ ሁሉ ወደ ማዕከሉ ስልክ ቁጥሮች 0940050505 ወይም 0940040404 ላይ በመደወል መመዝገብ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Tigray #AddisAbaba #COVID19

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 2 ቀናት ነሃሴ 18 እና ነሃሴ 19 በድምሩ 1,641 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በነዚህ ሁለት ቀናት ሪፖርት መሰረት ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ የ30 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 20 ከአስክሬን ምርመራ ሲሆን 10 ከጤና ተቋም ነው።

በሌላ መረጃ፦

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የነሃሴ 19/2012 ሪፖርት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም ከ602 የላብራቶሪ ምርመራ 62 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከነዚህ 62 ሰዎች መካከል 5 ለይቶ ማቆያ ማዕከል የነበሩ ፣ 11 በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ፣ 46 የጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው።

እስከሁን ድረስ በትግራይ ክልል 43,206 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 3,452 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ ከነዚህ መካከል የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል፣ 1,870 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

በሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ በገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ  አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሲገደል  አብራው የነበረችው ላምሮት ከማል ላይ አቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ፍርድ ቤቱ ፈቀደ።

መርማሪ ፖሊስ ጉዳዩን ለተመለከተው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት  ምርመራ ማጠናቀቁን ገልፆ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ አስረክቧል። አቃቤ ህግም በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ህግ 109 መሰረት 15 ቀን ክስ መመስረቻ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪዋ “አርቲስት ሃጫሉ ጓደኛዬ ነው፣ በወቅቱ አብሬው ነበርኩ ፣ ይህንን አልክድም ፣ ለህይወቴ ሳልሳሳ ወንጀለኞቹን አሳይቻለሁ ፤ ፍርድ ቤቱ የቤተሰቦቼ ማህበራዊ ህይወት እንዳይሰተጓጎል በዋስ ይልቀቀኝ” ብላለች።

ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ 63 መሰረት ጉዳዩ የግድያ ወንጀል የተፈፀመበት በመሆኑና ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ ሲመሰረት ከ15 ዓመት በላይ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ ዋስትና የሚያስከለክል ነው በማለት የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል። ነገር ግን አቃቤ ህግ በ15 ቀን ውስጥ ክስ ካልመሰረተ የዋስትና ጥያቄ አቤቱታን ማቅረብ ይቻላል ብሏል።

Via Tarik Adugna (FBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮ ቴሌኮም ቅናሽ!

'ኢትዮ ቴሌኮም' የኢንተርኔት ጥቅል አገልግሎት ላይ እስከ 35 በመቶ ቅናሽ አደረገ፤ እንዲሁም በቤትዎ ይቆዮ የጥቅል አገልግሎት 59 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል።

የድምፅ ጥቅል አገልግሎት ላይም የ29 በመቶ ቅናሽ ያደረገ ሲሆን አገልግሎቱም ከነገ ነሐሴ 21/2012 ጀምሮ በስራ ላይ ይውላል።

በተጨማሪ እስከ 11 የሚደርሱ ሀገራት ላይ የውጭ ጥሪ አገልግሎት 50 በመቶ ቅናሽ መደረጉ ታውቋል። ከውጭ አለም አቀፍ ጥሪ ለሚቀበሉ ደንበኞች ከኢትዮ ቴሌኮም ስጦታ ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ethiotelecom

ኢትዮቴሌኮም የአደይ አበባ የድምጽ እንዲሁም የዳታ ጥቅል አገልግሎት ላይ እስከ 53 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ ተወስኖ የቆየውን የ4G / LTE አገልግሎት በክልል ከተሞች ለመጀመር ማቀዱን ይፋ አድርጓል፡፡

ምንጭ፦ ካፒታል፣ አዲስ ማለዳ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮ ቴሌኮም የምስጋና ስጦታ!

ኢትዮ ቴሌኮም ከነገ ሐሙስ ነሐሴ 21/2012 ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ የምስጋና ስጦታ ማዘጋጀቱን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

የድርጅቱ ደንበኞች 1 GB የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት ፣ 40 ደቂቃ ድምጽ አገልግሎት ፣ 100 አጭር የጽሁፍ መልዕክት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት በነጻ እንደሚያገኙ መገለፁን ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ትምህርቶች ከወረቀት ነፃ በማድረግ በዲጂታል መልክ መሰጠት በትምህርት ዘርፉ የ10 ዓመት እቅድ ውስጥ ማካተቱን አሳውቋል።

ወደ ዲጂታል ስርዓቱ ለመግባትም ለተማሪዎች ታብሌቶችን ለማሟላት የተለያዩ አማራጮች እየተፈለጉ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እና አመራሮች በየደረጃው በትምህርት ዘርፉ የአስር (10) አመት እቅድ ላይ ውይይት ጀምረዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopiaBot