TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ADP

ግንቦት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በአክሱም ዩኒቨርስቲ የ2ኛው አመት የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ በነበረው ዮሐንስ ማስረሻ ሰይፈ ላይ የተፈፀመውን ግድያ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አጥብቆ ያወግዛል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተማሪ ዮሐንስ ማስረሻ ሞት የተሰማውን መሪር ሃዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞቹና ለዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ አካባቢ የሚገኙ የመስተዳድር እና የጸጥታ አካላት እንዲህ አይነት አስነዋሪ ድርጊቶች ወደፊት እንዳይደገሙ አስቀድሞ በመከላከል ረገድ እንዲሁም የተማሪዎችን ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ይህንን አጸያፊ ድርጊት የፈጸሙ ወንጀለኞች በአስቸኳይ ተለይተው ለፍርድ እንዲቀርቡ ለማድረግ እና ወደፊትም ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ይገልጻል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም.
ባህር ዳር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TPLF/ህወሓት እና #ADP/አዴፓ

"አሁን የአዴፓ ድርጀት የራሱን ትላልቅ ጓዶች የገደለ ሃይል ማውገዝ አቅቶት በአርበኝነት ተረት ለመፍጠር ሲሞክር ስታይ ወይ ተምታትቶበታል ወይም ድርጅቱ የሆነ ነገር ይበል፡፡የራስህ ጓዶች የገደለን ሰው አርበኛ ነው ጀግና ነው ማለት የጀመረ ድረጅት በግሌ አጠገቡ መቀመጥ ይከብደኛል፡፡እና የሄንን በደንብ አጥርቶ ይምጣ ነው ያልነው፡፡አሰላለፍ ማለት እሱ ነው፡፡ስለአሰላለፍ ስታወራ እገሌ ጀግና ነው እገሌ አንዲህ ነበረ ኣይደለም የምትለው፡፡ #አምባቸው_መኮነን ህዝብ የመረጠው የአማራ ክልል መሪ ነው፣ምግባሩ ከበደ በህዝብ የተመረጠ የአማራ ክልል መሪ ነው፣ሌሎቸም እነዚህ ሰዎች በጠራራ ፀሃይ የገደለ ሰው አርበኛ ነው፣አንበሳ ነበረ ማለት ትክክል ኣይደለም ፡፡ አሁን በዚህ ግርግር ውስጥ በኣደባባይ ሰውን የገደለ ላለማውገዝ ተረት የሚፈጥር አመራር ፣እኔ እንደ ጓድ ፣ የሞቱት ጓዶቼ ናቸው የሄን ዓይነት አቋም የሚያሳይ ድርጅትጋር አብረን ለመጓዝ እርግጠኞች መሆን አንቸልም የሚል የአቋም መግለጫ መስጠት ጤነኝነት ነው፡፡ለድርጅቱም ማዘን ንው፡፡" አቶ ጌታቸው ረዳ ከኢሳት ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ

ምንጭ፦ TPLF ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ነገ ሐምሌ 06/2011 በባሕር ዳር ስብሰባውን እንደሚጀምር ታውቋል። #ADP #አዴፓ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አፅህሮተ-ስያሜውን ያካተተው ዓርማ ከላይ የምትመለከቱ ነው፡፡ #ADP #አዴፓ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADP

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ #የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ውህደትን መቀበሉን አስታውቋል። ውህደቱ ኢትዮጵያዊነትን ከማንነት ጋር አስተሳስሮ የሚያስኬድና የእውነተኛ ፌደራሊዝም መተግበሪያ መሆኑን በመገንዘብ የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ በአዲሱ ሀገራዊ ህብረብሄራዊ ፓርቲ ተዋህዶ ለመታከል መወሰኑን የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ መላኩ አለበል በትዊተር ገፃቸው ይፋ አድርገዋል።

(EPA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ODP #ADP #SPEDM

ኦዴፓ (የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) እና አዴፓ (አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ) በቅርቡ ተግባራዊ ሊደረግ ጫፍ ስለደረሰው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ጥምር እና አጋር ፓርቲዎች ውህደት በተመለከተ ለመወያየት አስቸኳይ ጉባኤ መጥራታቸው ተሰምቷል።

ኦዴፓ ዛሬ ኅዳር 16/2012 አስቸኳይ ጉባዔ የጠራ ሲሆን ኦዴፓ ወህደቱን በተመለከተ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። በተመሳሳይ አዴፓ በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ጉባዔ የጠራ ሲሆን በተመሳሳይ ርዕስ ላይ ለሁለት ቀናት እንደሚወያይ ተልጿል። እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ደኢሕዴን) አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ሐሙስ ኀዳር 18/2012 መጥራቱ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia