TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹 ከነገ ግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ቀናት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉን ይጀምራል። ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃን። የስብሰባው ሥርዓቶች ምንድናቸው ? 1. ማንኛውም ተሳታፊ #በነጻነት ሀሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ሆኖም ተሳታፊዎች ከጥላቻ፣ ከአዋራጅ እና ከተንኳሽ ንግግሮችመቆጠብ፤ 2. በምክክሩ ጊዜ መደማመጥን…
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

በአዲስ አበባ የተጀመረው የአጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ምን መልክ አለው?

በአዲስ አበባ የተጀመረው የአጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ከዛሬ ግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል። በሂደቱ ከ2,500 በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፋሉ።

በዋናነት ከዚህ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ምን ይጠበቃል?

- 2,500 ከሚሆኑት ተሳታፊዎች በቀጣይ ለሚደረገው ሀገራዊ ምክክር አዲስ አበባን ወክለው የሚሳተፉ ተወካዮች ይመረጣሉ

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ጉባኤ ይሰየማል

- በአዲስ አበባ ደረጃ በሀገራዊ ምክክሩ ላይ መቅረብ አለባቸው የሚባሉ አጀንዳዎች ይዘጋጃሉ።

በእነዚህ 7 ቀናት ምክክር ኮሚሽኑ ምን ሊያከናውን አቅዷል?

#ቀን_1 እና #ቀን_2

- በመጀመሪያው ቀን በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ የምክክር ምዕራፉ መክፈቻ ሥነ-ስርአት ይካሄዳል። (ይሄ መርሐግብር ዛሬ ጠዋት በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተካሂዷል)

ከመጀመሪያው ቀን የከሰዓቱ መርሐግብር ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ቀን መጨረሻ ድረስ፦

- 11 የሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች  ከ100 በማይበልጥ ቡድን ተከፍለው ይወያያሉ።

- እያንዳንዱ ቡድን ህበረተሰቡን ወክሎ በሚቀጥሉት የምክክር ሂደቶች ሊሳተፉ
የሚችሉ 22 እጩዎችን ይለያሉ።

#ቀን_3

- በቡድን ሲደረግ የነበረው ምክክር ውጤት በየተራ ለቤቱ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይካሄድበታል።

- ከተለዩ እጩዎች ውስጥ 11 የህብረተሰቡ ወኪሎች በሚስጥር ድምጽ አሰጣጥ ይመርጣሉ፡፡

በዚሁ ቀን በተጓዳኝ በከተማ አስተዳደር ደረጃ የተወከሉ ቁጥራቸው 1,220 የሚደርሱ ባለድርሻ አካላት ውይይት ይደረጋል። (ባለድርሻ አካላት የሚባሉት ታዋቂ ሰዎች፤ ፖለቲከኞች ከተቋማትና ማኅበራት የሚሳተፉ አካላት ናቸው።)

#ቀን_4

ዋናው የመክፈቻ  ሥነ-ስርዓት (Launching Ceremony) ይከናወናል

- ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችን ጨምሮ 3,500 ተሳታፊዎች በዋናው የመክፈቻ  ሥነ-ስርዓት ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ።

#ቀን_5

- ተሳታፊዎቹ በ5 ቡድን ( ከወረዳ የተወከሉ (ብዛት 121 )፤ መንግስት፤ የፖለቲካ ፖርቲዎች፤ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት፤ ታዋቂ ሰዎች (ብዛት 1220) ተከፍለው የአጀንዳ ምክክራቸውን ይቀጥላሉ፤ አጀንዳዎቻቸውን ይለያሉ።

በተጨማሪ ከአምስቱ ቡድኖች በተናጠል የምክክር ውጤቶችን የሚያጠናክሩና የሚያዳዳብሩ 5 ተወካዮች በድምሩ 25 ተወካዮች ይመረጣሉ።

#ቀን_6

- ጠዋት 1,340 ተሳታፊዎችን የያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ጉባኤ ይሰየማል፡፡ 

- 5ቱም ቡድኖች ለጉባኤው የምክክራቸውን ውጤት ሪፖርት ያቀርባሉ፤ በሪፖርቱ ላይም ውይይት ይደረጋል።

- ከየቡድኑ የተመረጡ 25ቱ ሰዎች በጋራ የ5ቱን ቡድኖች አጀንዳ አንድ ላይ በማምጣት ኮሚሽኑ ባስቀመጠው መሰፈርት መሰረት ያደራጃሉ፡፡

#ቀን_7

- 25ቱ ወኪሎች ያደራጆቸውን አጀንዳዎች ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርቡና ሙሉ ቀን ውይይት ይደረግበታል፡፡  

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አጀንዳ ግብዓት ተለይቶ ለኮሚሽኑ ይሰጣል፡፡

- 25ቱ ተወካዮች የከተማ አስተዳደሩን የተጠቃለለ እጀንዳ ለማደራጀት ሦስት መስፈርቶች ይጠቀማሉ። እነዚህም አስቸኳይ ፤ አስፈላጊ እና  ከፍተኛ ውክልና ያለው በሚል የሚለዩ ይሆናሉ።

#TIKVAHETHIOPIA

@tikvahethiopia