TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ArbaMinch

በአርባምንጭ ከተማ ለሚገነባው አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዌልነስ ሪዞርት ግንባታ ጅማሮ የሚሆን የቦታ ቅየሳ ስራዎችን ባለሞያዎች ማከናወን ጀምረዋል።

በአርባ ምንጭ ከተማ በአፍሪካ ከሲሼልስ ከሚገኘው ግዙፉ ሆቴልና ሪዞርት በመቀጠል አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴልና ሪዞርት እንደሚገነባ ከዚህ ቀደም ይፋ መደረጉ ይታወቃል፡፡

ግንባታው በሚከናወነበት ስፍራ የኩባንያው ባለቤቶችና የውጪ ሀገር ባለሃብቶች ቦታው ድረስ በመምጣት ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ለሆቴሉና ሪዞርት ግንባታ ስራዎች ዝግጅት የሚረዱ የመረጃ ግብዓቶችን የመሰብሰብ ስራ ሲከናወኑም ቆይተዋል፡፡

ከዚሁ ግንባታ ስራ ጋር በተያያዘ በዚህም ሳምንት ከቀን 25 ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የቦታ ልኬትና ማመቻቸት ስራዎች በአለም-አቀፍ የግንባታ ባለሙያዎች ግንባታው በሚያርፍበት ስፍራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

#BrishZewde #TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia