TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ የስፓርት ውርርድ ( #ቤቲንግ ) ቤቶች እየታሸጉ / እየተዘጉ ይገኛሉ።

ይህ ተከትሎ የስፖርት ውርርድ ቤት ባለቤቶች " እንዴት የንግድ ፈቃድ እያለን ይዘጋብናል ? " ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

እነዚህ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ከወራት በፊት በተለያዩ ምክኒያቶች ተዘግተው የቆዩ ሲሆን በቅርቡ ተከፍተው ነበር።

አሁን ላይ ተመልሰው መዘጋት/መታሸግ መጀመራቸው ግራ እንዳጋባቸውና ልክ እንደባለፈዉ ጊዜ ከስራቸዉ ተስተጓጉለው ቤት መዋል መጀመራቸው እንዳሳዘናቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ቤተሰብ አባል ፥
° ቤቶቹን ለምን ታሸጉ ?
° መፍትሄውስ ምንድን ነው ? ሲል የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለን ጠይቋል።

እሳቸውም ፤ " #በሲዳማ_ክልል_ስር የወጣ አንድም የንግድ ፈቃድ የለም " ብለዋል።

" ከወራት በፊት ከነዚህ አካላት (ቤቲንግ ቤቶች) ጋር በነበረን ውይይት የንግድ ፈቃድ በማውጣት ህጋዊ እንዲሆኑ ተግባብተን ነበር " ሲሉ አስታውሰዋል።

" ይሁንና ከረዥም ጊዜ በኋላ ዳግም ስናጣራ አሁንም ህጋዊ መሆን አልቻሉም " ያሉት ሀላፊው " ከዚህ ባለፈም እነዚህ ቤቶች በትምህርት ቤት ፣ በሀይማኖት ተቋማትና በመኖሪያ ሰፈሮች እንዲሰሩ አይፈቀድም ሌላዉ የመዘጋታቸዉ ምክኒያት ይኸው ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

ለግለሰቦቹ በሰላማዊ መንገድ ምክንያቱ ተነግሯቸው ቤታቸዉ እየተዘጋ መሆኑን የገለጹት አዛዡ ፤ " ከዚህ ዉጭ ' ገንዘብ ተወሰደብኝ ' እንዲሁም ' የአላግባብ ህገወጥ የሆነ ተግባር ተፈጽሞብኛል ' የሚል አካል በማንኛዉም ሰአት ወደ ሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመምጣት ሊያመለክት ይችላል " ብለዋል።

ቤቶቹ ተመልሰው #የመከፈት እድል አላቸዉ ወይ ? ተብለው የተጠየቁት ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ " መጀመሪያ ህጋዊ ይሁኑ ከዛ በኋላ ከፖሊስ በተጨማሪ የሚመለከታቸዉ አካላት የሚመለከቱት ጉዳይ ይሆናል " ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia