TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Fake Video‼️

በማህበራዊ ሚዲያ(በተለይም በfacebook) #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ ንብረት የሆነው #ቦይንግ_737 "ከመከስከሱ በፊት" ተብሎ እየተሰራጨ የሚገኘው #ቪድዮ_ሀሰተኛ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዛሬ ጠዋት በADF ካምፖች ላይ ከኮንጎ አጋሮቻችን ጋር በጋራ የአየርና የመድፍ ጥቃቶችን ፈፅመናል " - የኡጋንዳ ጦር ቃል አቀባይ የኡጋንዳ ጦር ከጎረቤት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) ሃይሎች ጋር በመሆን በAllied Democratic Force (ADF) ታጣቂ ቡድን ላይ በጋራ የአየር ድብደባ እና የመድፍ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ። የኡጋንዳ መከላከያ ሃይል ቃል አቀባይ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ

የኡጋንዳ ጦር ከጎረቤቱ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) ሃይሎች ጋር በመሆን በ Allied Democratic Force (ADF) ታጣቂ ቡድን ላይ በጋራ የአየር ድብደባ እና የመድፍ ጥቃት መፈፀሙን ትላንት አሳውቋል።

ዛሬ ደግሞ ኡጋንዳ ይህን የታጠቀ ቡድን ለማደን እና ለመቅጣት ጦሯን ድንበር አሻግራ ወደ ኮንጎ መላኳ ተሰምቷል።

የኡጋንዳ ባለስልጣናት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በካምፓላ ለደረሰው የአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ADFን ተጠያቂ አድርገዋል።

ይሄ የታጠቀ ቡድን በምስራቃዊ ኮንጎ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ጥቃቶችን ፈጽሟል በሚል ይከሰሳል።

ሁለቱም ሀገራት ADF የተባለው የታጠቀ ቡድን በርካታ ሲቪል ሰዎችን መጨፍጨፉን ይገልፃሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sudan በሱዳን መዲና ካርቱም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ተሰምቷል። የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ያስተላፉት የሱዳን የተቃዋሚዎች እና የፖለቲካ ሀይሎች ኮሚቴ ነው። ሰልፉ በሌተናል ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና በጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ መካከል የተደረሰውን ስምምነት በመቃወም ነው የሚካሄደው። የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ተከትሎ በካርቱም ውስጥ የሚገኘው የደህንነት…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ - #የሱዳን_ተቃውሞ

የሱዳን ጸጥታ ሃይሎች በሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሱ።

ዛሬ በሱዳን መዲና ካርቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ጥቅምት ወር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።

የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ብሄራዊ ቤተ መንግስት አቅራቢያ በነበሩ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸውን ኤኤፍፒ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከካርቱም በተጨማሪ በተለያዩ የሱዳን ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እየተደረገ ነው።

Video Credit : UoKEN

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ - የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ አየር ኃይል ከጥምር ጦሩ ጋር በመሆን በየመን " አል-ጃውፍ " ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ቦታ በተሳካ ሁኔታ ማውደሙን በመግለፅ ከላይ የተያያዘውን ቪድዮ አጋርቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የ40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዥ ስምምነት አልተፈፀመም " - ገንዘብ ሚኒስቴር የተከሰተውን የምግብ ዘይት መጥፋትና የዋጋ መናር ችግሮችን ለመፍታት የ40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዥ ስምምነት #አለመፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ንግድ ቢሮዎች ጋር በመሆን ሰኞ በሰጠው መግለጫ በአገሪቱ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው የምግብ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ : ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ንግድ ቢሮዎች ጋር በመሆን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ላይ የምግብ ዘይት ዋጋ መናር ለመፍታት የሚያግዝ 40 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ የገለፀበት ቪድዮ ይህ ነው።

የገንዘብ ሚኒስቴር የ40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዥ ስምምነት አልተፈፀመም ብሏል።

ሪፖርተር ጋዜጣ ፤ የሚኒስቴሩ አማካሪ አቶ ኤፍሬም ፥" ዘይት ለማቅረብ የተመረጠም ሆነ ከመንግሥት ጋር ስምምነት ያደረገ አቅራቢ የለም ፤ መንግሥት ሊያስገባ ያሰበው የዘይት መጠንን በተመለከተም፣ ውሳኔ ላይ አልተደረሰም፤ ጉዳዩ በጥናት ላይ ያለ ነው " ሲሉ መናገራቸውን ዛሬ አስነብቧል።

ስለጉዳዩ ባለፈው ሰኞ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጠው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚሰጠው ተጨማሪ ማብራሪያ ወይም አስተያየት ካለ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ኤክሳይዝታክስ

ኤክሳይዝ ታክስ ላይ ማሻሻይ ተደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል።

ማሻሻያው ቴሌቪዥን እና ቪድዮ ካሜራ ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ፤ ተሽከርካሪዎች ላይም የኤክሳይዝ ታክስ እንዲቀንስ ያደርጋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ለሁለት ዓመታት እና ከዛ በላይ ሲተገበር የቆየው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ላይ አዳዲስ ማሻሻይ አደርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡ ተሰምቷል።

ማሻሻያ ተድርጎ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የኤክሳይዝ ታክስ የያዛቸው አዳዲስ ጉዳዮች ፦

- በተሽከርካሪ ላይ ይጣል የነበረው የኤክሳይዝ ታክስ መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል ፤

- ከ3000 ሲሲ ባላይ  ጉለበት ባላቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ይጣል የነበረው 240 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ በረቂቅ አዋጁ 120 አካባቢ ዝቅ እንዲል ይላል ፤

- ከ2501 እስከ 3000 ሲሲ 106 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤

- ከ1501 እስከ 2500 ሲሲ 90 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤

- ከ1500 ሲሲ በታች 66 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ፤ እንዲጣልባቸው ይላል ረቂቅ አዋጁ።

የገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ፖሊሲ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሳይ ወልዱ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ " አሁን በጣም ትኩረት የምናደርገው ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ነው። ነዳጅን ለማበረታታ አይደለም (የኤክሳይዝ ታክሱ መቀነሱን ማለታቸው ነው) ግን በጣም ከፍ ያለ ከሚሆን ሌሎች ተያያዥ ነገሮች ስላሉት ሲወጣ ይታያል አሁን ያለውን ከፍተኛ ሁለት መቶ አርባ አካባቢ ያለው ወደ መቶ ሃያ አካባቢ ዝቅ እንዲል ፤ በየደረጃው እንደዛ እንዲስተካከል ነው። " ብለዋል።

ዳይሬክተሩ ፤ አዋጁን ለማሻሻል ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ከፍተኛ የሆነውን የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ በመቀነስ #የኤሌክትሪክ_ተሽከርካሪዎች እና የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ መሳይ ወልዱ ፤ " ታክሱን መቀነስ ብቻ ሳይሆን በተለይ የሀገር ውስጥ ገጣጣሚዎችን በማበረታታት አቅርቦትን ስለሚጨምር ፍላጎትም ይመጣል። አቅርቦትም ስለሚመጣ ዋጋ ተመጣጣኝ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም ፤ ይሄ ወደ ቀረጥና ታክስ ነፃ የሚደረጉ ሩጫ ሁሉ ይቀንሰዋል፤ ይሄ ከፍተኛ መሆኑ ለዛ አንዱ ማበረታቻ ስለሚሰጥ ፤ ዋጋውን ይቀንሰዋል  በተለይ የኦውቶሞቲቭ ኢንድስትሪው የሀገር ውስጡ የራሱን ሚና ይጫወታል በማሳደግ እየተረጋጋ ይሄዳል የሚል ሃስብ ነው ያለው። " ሲሉ ገልፀዋል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ የተካተተው ሌላው ፤ 10 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ይጣልባቸው የነበሩት የቪድዮ ካሜራ እና ቴሌቪዥን ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ እንዲሆኑ ተደርጓል።

አቶ መሳይ " በመጀመሪያው ማሻሻያ እራሱ ቴሌቪዥን ወደ 40 % ነበር የነበረው በጣም ተቀንሶ 10% ነው የተደረገው። የቪድዮ ካሜራም እንደዛው ፤ በጣም አስተያየት ተደርጓል የመጀመሪያው ላይ ግን የገቢ ክፍተት እንዳይፈጠር ቀስ በቀስ መውጣት ስላለብን ከ40 % ወደ 10 % ተደርጓል በተለይ ከስነ ጥበብ ከማሳደግ እና ከመደገፍ አንፃር ታይቶ ፣ ቴሌቪዥንም ህብረተሰቡ መረጃ የሚያገኝበት የመንግስት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ የሚሰማበት ስለሆነ እሱ ላይም ቅናሽ ተደርጓል። በሂደት ስናየው አሁንም ተጨማሪ ማሻሻያ ያስፈልጋል የሚል ነው #ቴሌቪዥንና #ቪድዮ_ካሜራ በተለይ በዛ ውስጥ ባይካተቱ የሚል ሀሳብ ነው የቀረበው " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በ2012 ነበር ለ30 ዓመታት ስትጠቀምበት የነበረውን የኤክሳይዝ ታክስ ያሻሻለችው ፤ አሁን ከ3 ዓመት በኃላ የሚደረገው ማሻሻያ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር  እኩል እንድትራመድ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት መሆኑ ተገልጿል።

መረጃውን ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ድሬዳዋ

" ለከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የምንሰጠው #ክብር ትልቅ ነው " - ድሬዳዋ

በመላው ኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች ለእንግድነትም ሆነ እዛው በከተማዋ እየሰሩ ለመኖር አስተማማኝ የሰላም እና ፀጥታ ደህንነት ካለባቸው ከተሞች አንዷ ድሬዳዋ ናት።

ከተማይቱ በአንድ ወቅት አጋጥሟት ከነበረው የፀጥታ መንገጫገጭ ከወጣች በኃላ ላለፉት ዓመታት እጅግ አስተማማኝ ደህንነቷና ሰላሟን አስጠብቃ ትገኛለች።

በማታም ሆነ በቀን በከተማዋ ውስጥ ለመንቀሳቀስ እንዲሁም ሰርቶ ለመግባት ያማታሰጋ ሆና ተሰርታለች።

ከዚህ ባለፈም ፤ #የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት በሆነው ዋና መንገድ ላይ በመገኘቷ በርካታ አሸክርካሪዎች በየዕለቱ ታስተናግዳለች።

ብዙ ርቀት በአስቸጋሪ የአየር ፀባይ የሚጓዙ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ደህንነታቸው እንዲጠበቅና ፤ በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚስተዋለው የተንዛዛ የትራፊክ ፖሊስ ጭቅጭቅ እንዳይኖርም እያደረገች ትገኛለች።

የድሬዳዋ ከተማ የትራፊክ ፖሊስም ረጅም መንገድ በረሃና አስቸጋሪ የአየር ንብረት በመቋቋም የሀገሪቱን ገቢ እና ወጪ ንግድ ለሚያፋጥኑ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የሚሰጠው #ክብር ትልቅ መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን ማንኛውም አሽከርካሪ በከተማው ውስጥ ሆኖ ችግር ከገጠመው ለማስተካከል ዘውትር ዝግጁ ነኝ ብሏል።

#ቪድዮ፦ ከወር በፊት የከተማይቱ አመራሮች ረጅም ርቀት ተጉዘው ድሬዳዋ ከተማ የደረሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን ለማክበር የታሸገ ውሃ ሲሰጧቸው የሚያሳይ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ : የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የግድያው ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት እሳቸው ቅስቀሳ ከሚያደርጉበት ስፍራ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣሪያ ላይ የነበሩ የ " ሴክሬት ሰርቪስ " የስናይፐር ተኳሾች የግድያ ሙከራውን ባደረገው ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል።

አንድ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪድዮ ሁለት የሴክሬት ሰርቪስ ስናይፐር ተኳሾች በፍጥነት ኢላማ አድርገው የግድያ ሙከራ ባደረገው ግለሰብ ላይ የተኩስ መልስ ሲሰጡ ተስተውሏል።

ግለሰቡ የግድያ ሙከራ ባደረገ በሰከንዶች ውስጥ መተገው ገድለውታል።

የግድያ ሙከራውን ያደረገው ማነው ?

- FBI የግድያ ሙከራውን ያደረገው ቶማስ ማቲው የተባለ #የ20_ዓመት_ወጣት እንደሆነ ገልጿል።

- ነዋሪነቱ ምርጫ ቅስቀሳውና የግድያ ሙከራው ከተደረገበት ስፍራ የአንድ ሰዓት ጉዞ የሚፈጅ ቦታ ነው።

- በ2022 ነው ቤተል ፓርክ ከተባለ ሀይስኩል የተመረቀው።

- ወጣቱ በብሔራዊ የሒሳብ እና ሳይንስ ኢኒሼቲቭ ተሸላሚም ነበር።

- የሪፐብሊካን ደጋፊም ጭምር እንደሆነ ተመዝግቧል (የዶናልድ ትራምፕ ፓርቲ ማለት ነው)።

- ቅስቀሳው ከሚደረግበት ቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣራ ላይ ሆኖ ነው ዶላንድ ትራምፕን ለመግደል የሞከረው።

- ለምን ይህን ለማድረግ እንደፈለገ FBI ምርመራ እያደረገ ነው።

#USElection #FBI

@tikvahEthiopia