TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሩስያ ያቀደችውን ታሳካለች " - ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር 90 ደቂቃ ያህል የፈጀ የስልክ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅት ፑቲን ሞስኮ ዩክሬን ውስጥ በምታካሂደው ዘመቻ ያቀደችውን ታሳካለች ብለዋል። ፑቲን አስተዳደራቸው የኪዬቭን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በማስቆም ለሩሲያ ደኅንት ወታደራዊ ስጋት እንዳትሆን እናደርጋለን ስለማለታቸው…
" ከእኔ ጋር ቁጭ ብለህ ተነጋገር " - ቮልድሚር ዜኔንስኪ

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በቀጥታ ለመነጋገር ጠያቄ አቀረቡ።

ዜሌንስኪ ይህን ጥያቄ ያቀረቡት ዛሬ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ነው።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " ጦርነቱን ለማቆም #ብቸኛው አማራጭ ከፑቲን ጋር በቀጥታ መነጋገር ነው " ብለዋል።

ዜሌንስኪ ለፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት ፥ " ሩሲያን እያጠቃን አይደለም፤ ለማጥቃትም እቅዱ የለንም። ከእኛ ምንድነው የምትፈልገው ? መሬታችንን ትልቀቅ " ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ አክለው ፤ " ከእኔ ጋር ቁጭ ብለህ ተነጋገር። 30 ሜትር ሳይርቅ " በማለት ፑቲን ከፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ጋር በረዥሙ ጠረጴዛቸው ፊት ለፊት ያደረጉትን ንግግር አስታውስዋል።

ዜሌኒስኪ በመግለጫቸው ላይ #ምዕራባውያን ተዋጊ አውሮፕላኖችን እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።

" የአየር ክልሉን መዝጋት የማትችሉ ከሆነ ፤ አውሮፕላኖችን ስጡኝ " ሲሉ ነው ዜሌንስኪ የጠየቁት።

ምዕራባውያን የሩሲያ ተዋጊ አውሮፕላኖችን በዩክሬን ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ የዩክሬንን አየር ክልል እንዲዘጉ ሲጠየቁ ቆይተዋል።

ዜሌንስኪ ፤ " በቀጣይ ሩሲያ ላትቪያ ፣ ሊትዌኒያ እና ኢስቶኒያን ልትወር ትችላለች " ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሌላ መረጃ ፥ የሩስያ እና ዩክሬን ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ዛሬ በቤላሩስ ተጀምሯል።

@tikvahethiopia
" ፕሬዝዳንታችን ከፑቲን ጋር በቀጥታ መገናኘትን ጨምሮ ምንም ነገር አይፈሩም " - የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የዩክሬን ፕሬዜዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ ከሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ቁጭ ብለው እንዲነጋገሩ ይፈልጋሉ።

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ ፥ ዩክሬን በፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እና በሩሲያ ቭላድሚር ፑቲን መካከል ቀጥተኛ ውይይት ትፈልጋለች ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፥ " በዩክሬን ፕሬዝዳንት እና በቭላድሚር ፑቲን መካከል ቀጥተኛ ውይይት ለማድረግ ለረጅም ጊዜ እንፈልግ ነበር። ምክንያቱም በተለይም አሁን ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን የሚወስኑት እሳቸው መሆኑን ሁላችንም እንረዳለን " ብለዋል።

" ፕሬዝዳንታችን ከፑቲን ጋር በቀጥታ መገናኘትን ጨምሮ ምንም ነገር አይፈሩም " ያሉት ኩሌባ " ፑቲንም ካልፈሩ ወደ ስብሰባ ይምጡና ቁጭ ብለው ይነጋገሩ " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም እራሳቸው ፕሬዜዳንት ዜሌንስኪ ጦርነቱን ለማቆም #ብቸኛው አማራጭ ከፑቲን ጋር በቀጥታ መነጋገር መሆኑን ገልፀው " ፑቲን ከእኔ ጋር ቁጭ ብለህ ተነጋገር " የሚል ጥሪ ቢያቀርቡም ፑቲን ምላሽ አልሠጧቸውም።

ጦርነቱ የተጀመረ ሰሞን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መቀመጫው ኬዬቭ ያደረገውን በፕሬዜዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ የሚመራውን አመራር " የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኞች እና የኒዮ ናዚዎች ቡድን " ሲሉ ጠርተው የዩክሬን ጦር ስልጣኑን በቁጥጥሩ ስር እንዲያስገባ ጥሪ አቅርበው ነበር።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ❤️

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድል ያስመዘገበችበት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቋል።

#ከዓለም ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ እንዲሁም #ከአፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ ነው ያጠናቀቀችው።

በዓለም ሻምፒዮናው 4 ወርቆችን ያገኘን ሲሆን የዘንድሮው ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል።

ከተገኙት አራት #ወርቆች 🥇 መካከል ታምራት ቶላ በማራቶን ያገኘው ወርቅ በዓለም ሻምፒዮናው በወንዶች የተገኘው #ብቸኛው ወርቅ ነው።

ለሀገራቸው ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶቻችን እነማን ናቸው ?

ወርቅ 🥇

🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ጎተይቶም ገ/ስላሴ
🇪🇹 ታምራት ቶላ

ብር🥈

🇪🇹 ወርቅውሀ ጌታቸው
🇪🇹 ሞስነት ገረመው
🇪🇹 ለሜቻ ግርማ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ

ነሐስ🥉

🇪🇹 ዳዊት ስዩም
🇪🇹 መቅደስ አበበ

አጠቃላይ ከተገኘው 10 ሜዳሊያ ሰባቱ በሴቶች የተገኘ ነው፤ የቀረው 3 ሜዳሊያ ደግሞ በወንዶች ውድድር የተገኘ ነው።

የዓለም ሻምፒዮናው ምንም እንኳን ከፍተኛው ድል የተመዘገበበት ቢሆንም በወንዶች ውድድሮች ላይ የተሻለ መስራት እንደሚጠይቅ የሚጠቁም ነው።

የአትሌቲክስ ቡድናችን ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጀግና ፣ የክብር አቀባበል እንደሚደረግለት ይጠበቃል።

ውድ አትሌቶቻችን ፤ ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተጋድሎ ላስመዘገባችሁት ድል ፣ የሀገራችሁን ህዝብ ክብር ከፍ ስላደረጋችሁ ምስጋና ይገባችኃል።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጉራጌ ዞን ምክር ቤት #በክላስተር_ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አድርጓል። የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ፤ ዛሬ ሐሙስ ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤ ከሌሎች የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በክላስተር ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አደርጓል። የጉራጌ ዞንን በደቡብ ክልል ስር ከሚገኙ ሌሎች 4 ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ጋር በማዳመር የጋራ ክልል ለመመስረት የቀረበው…
#ተጨማሪ

" መንግስት የዞኑ ህዝብ በም/ቤት ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ ጥያቄ #በድጋሚ ሊያይ ይገባል " - የጉራጌ ዞን ም/ቤት

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር የቀረበውን #በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሐሳብ በአብልጫ ድምፅ #ውድቅ አድርጎታል።

የዞኑ ህዝብ በም/ቤቱ ያፀደቀው ህገመንግስታዊ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ ሊያይ ይገባል በሚል ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ የክላስተር ውሳኔውን ምክረ ሀሳብን ውድቅ ያደረገው።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ህዳር 17/2011 ዓ.ም. ባደረገው ጉባኤ ዞኑ ራሱን ችሎ ክልል ለመሆን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

የደቡብ ክልልን ለሁለት የሚከፍለውን የክልልነት አደረጃጀት በም/ቤቱ ባለማጽደቅ የጉራጌ ዞን #ብቸኛው ሆኗል።

ቀሪዎች የደቡብ ክልል 10 ዞኖች እና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ ላይ ሁለት ክልል የመመስረት ውሳኔን በምክር ቤቶቻቸው ማጽደቃቸው ይታወሳል። 

ፎቶ ፦ የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia