TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድብረ ማርቆስ👆

#በደብረ_ማርቆስ_ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ተማሪ ሞት ምክንያት የሆነውን ድርጊት የከተማው ነዋሪዎች እና የክልሉ መንግስት አወገዙ።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ስለ ችግሩ እና ስለ ቀጣይ የተማሪዎች #ሰላም ተወያይተዋል። ድርጊቱን ያወገዙት ተወያዮቹ ችግር ፈጣሪዎቹን በማጋለጥ ለጸጥታ አካላት እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። እስካሁን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ተማሪዎች #በቁጥጥር _ስር መዋላቸውም ነው በውይይቱ የተገለፀው።

ሌሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጸጥታ ስጋት እንዳይደርስባቸው ከጎናቸዉ እንደሚሆኑ ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እሁድ ግንቦት 18/2011 ዓ.ም የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፋ ሶስት ተማሪዎች ቆስለዉ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። የችግሩ መንስኤ እስካሁን እንዳልታወቀም ነው ማብራሪያ የተሰጠው።

የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና ሕዝብ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ ላይ በደረሰዉ የሕይወት መጥፋት ከልብ ከማዘን ባሻገር ድርጊቱን አጥብቀው እንደሚያወግዙት ገልጿል።

የክልሉ መንግሥት ከሕዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለሕግ እንደሚያቀርብም ነው ያስታወቀው። ለሟች ቤተሰቦች፣ ለጓደኞቹና ለዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብም መጽናናትን ተመኝቷል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia