TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert ኢትዮ ቴሌኮም በኢንተርኔት #መቆራረጥ ምክንያት ብቻ 204 ሚሊዮን ብር ማጣቱን ገለጸ። ኢትዮ ቴሌኮም የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል። የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ፍሬህይወት በዚህ ጊዜ እንዳሉት በኢንተርኔት መቆራረጥ ምክንያት ብቻ 204 ሚሊዮን ብር አጥተናል ብለዋል።

ከዚህ በፊት በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት ኢትዮጵያ በቀን 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች ተብሎ የወጣው ዘገባ ስህተት መሆኑን ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2011 በጀት ዓመት 36 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። የተገኘው ገቢ የእቅዱን 80 በመቶ ያሳካ ሲሆን ገቢው ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በ7 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ወይዘሮ ፍሬህይወት ተናግረዋል።

ድርጅቱ የደንበኞቹን ቁጥር 43 ሚሊዮን ያደረሰ ሲሆን አገራዊ የቴሌኮም ስርጭቱ 44 ነጥብ 5 በመቶ መድረሱም በመግለጫው ወቅት ተገልጿል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአገሪቱ የተወሰኑ አካባቢዎች የጸጥታ ሁኔታ አስጊ በመሆኑ የቴሌኮም አገልግሎቶች የግድ ማቋረጥ አስፈልጓል ይሄ ደግሞ በገቢው ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮብናል ሲሉ ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

Via #ኢትዮ_ቴሌኮም
@tsegabwolde @tikvahethiopia