TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Afar

" በእሳት አደጋው 160 የሚጠጉ ሱቆች እና የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ

በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በድንገት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ በግምት ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው አስተዳድር አሳውቋል።

የሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ አስተዳድር አቶ ሀሰን ሀንዲ ለአፋር ብዙሀን መገናኛ በሰጡት ቃል ፤ " የእሳት ቃጠሎ አደጋው የደረሰው ወደ 10 : 00 ሰዓት አካባቢ በድንገት ከቢንዝል መሸጫ ቤት በተነሳ እሳት ነው " ብለዋል።

በድንገተኛው የእሳት አደጋ ምክንያት የደረሰው ውድመት ወደፊት የሚጣራ ሁኖ በግምት ግን ከ80 በላይ መኖሪያ ቤቶች እንደዚሁም ወደ 80 ሊጠጋ የሚችል የተለያዩ የንግድ ሱቆች ወድመዋል።

በእሳት አደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አሳውቀዋል።

በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ንፋስ መኖሩ እና የውሀ እጥረት በመኖሩ ቃጦሎው በፍጥነት በመባባሱ ምክንያትም እሳቱን ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ከፍተኛ ውድመት መከሰቱን አስተዳዳሪው አስረድተዋል።

ለተጎጂዎቹ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።

በብዛት የቢንዚል ሽያጭ ከሚከናወንበት ቦታም በቀላሉ የእሳት አደጋ እየተፈጠረ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቂ ሊደረግ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

መረጃው የአፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ነው።

@tikvahethiopia
#Afar

ህወሓት ኃይሎቹን ከአፋር ክልል፤ " ኤሬብቲ " ማስወጣቱን በመግለፅ መግለጫ አውጥቷል።

ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ የሚገኘው ህወሓት ኃይሎቹን ከአፋር ክልል ኤሬብቲ ያስወጣው ሰብዓዊ እርዳታ የማድረስ ስራን ለማገዝን ነው ብሏል።

የሰብዓዊ እርዳታ ወደክልሉ እንዲገባና ችግር ላይ ላሉ ዜጎች እንዲደረስ ከዚህ ቀደም ለሰብዓዊነት ተብሎ የተደረሰው ስምምነት ለማክበር ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቋል።

ኃይሎቹን ከኤሬብቲ ማስወጣቱን የገለፀው ህወሓት በሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት ላይ አፋጣኝ ለውጥ እንደሚጠብቅ ገልጿል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲደርስና ሁሉም አስፈላጊ አገልግሎቶች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ለማድረግ የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት በኩል የወጣውን መግለጫ "የተሳሳተ" ብሎታል።

ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል፤ አሁንም አፋር ውስጥ ወረዳዎችን እንደያዙ ነው ብለዋል።

አቶ ከበደ፥ "እንደዚህ አይነት ነገር ሰማን (ወጡ የሚል) ትርጉም ያለው መልቀቅ አይደለም፤ የተያዙ ቦታዎች አሉ ለቀቁ የሚል እምነት የለንም በኛ በኩል። ሰብዓዊ እርዳታው በአግባቡ እንዲደርስ በሚል ነው መንግስት ያለ ቅድመ ሁኔታ ስለፈቀደ ነው እንጂ አልተለቀቁም" ብለዋል።

ከዚህ ቀደ። የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ እርዳታው እንዲሳለጥ የህወሓት ኃይል ከአፋር ክልል ለቆ እንዲወጣ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግስት የህወሓት ኃይሎች በአፋር ክልል ዞን 2 በኃይል ይዘዋቸዋል ካላቸው ወረዳዎች መካከል አብአላ፣ መጋሌ፣ ኤሬብቲና በራህሌ ይገኙባቸዋል።

ለሰብዓዊት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ ከታወጀ በኃላ እስካሁን በአፋር በኩል ወደትግራይ የገባው 26 ተሽከርካሪ ነው።

@tikvahethiopia
#ICRC #Oromia #Afar

ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሀረርጌ ዞን፣ ኩምቢ ለሚገኙ 5000 አባወራዎች የእንስሳት መኖ እያከፋፈለ ይገኛል።

ስርጭቱ በአካባቢው ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ ሲሆን በዚህ ኦፕሬሽን እስከ 150,000 እንስሳት ይመገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ድርጅቱ አስታውቋል።

በሌላ በኩል ድርጅቱ ፤ ባሳለፍነው ሳምንት በአፋር ክልል ሲልሳ ለሚገኙ 9,000 የተፈናቀሉ ሰዎች መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን ማለትም ሶላር የእጅ ባትሪዎችን፣ ጀሪካኖችን፣ የማዕድ ቤት እቃዎችን፣ ምንጣፍ እና መጠለያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Somali #Afar

በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ ቀበሌዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘላቂነት መፍታት እንዲቻል 2ቱ ክልሎች ከስምምነት መድረሳቸውን አስታወቁ።

ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ያስችላል የተባለው መሠረታዊ ስምምነት የታጠቁ ኃይሎች ከግጭት አካባቢዎች እንዲወጡ እና የፌደራል ፀጥታ ኃይሎች ወደነዚህ ቦታዎች እንዲገቡ የሚፈቅድ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን መናገራቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በአዋሳኝ ቀበሌዎች በየቦታው ተኩስ ፣ ስርቆት እና መፈናቀል ይከሰቱ እንደነበር የተናገሩት አቶ ኢብራሂም ዘላቂ ሰላም ለማምጣትም የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደቀያቸው መመለስ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ኢብራሂም « ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ችግር እንዳይከሰት፣… ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲመጣ እና ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ሚና መሆን እንዳለበትም ነው ትናንት ከስምምነት ላይ የደረስነው።» ብለዋል።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ማሣረጊያ እንዲሆን የሁለቱ ክልሎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ኮንፈረንስ እንደሚያካሂዱም ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል መቀመጫ ጅግጅጋ በተካሄደው ውይይት የሰላም ሚንስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ጨምሮ የአፋር እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው እንደነበር ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WFP #Ethiopia የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል። በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል። ኤድሪያብ ቫን ደር…
#Afar

ሰይድ ሞሃመድ (የዓለም አቀፉ ህፃናት አድን ድርጅት የአፋር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ዋና ኃላፊ) ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

" ማህበረሰቡ ድብርብርብ ሸክም ነው የገጠመው ፤ የመጀመሪያው በርካታ የውሃ አቅርቦት እና ሌሎችም መሰረታዊ አገልግሎት ተቋማትን ስራ ያስተጓጎለው ፤ ያቋረጠው ግጭት በዚህ ላይ ድርቅ ሌላው ፈተና ነው።

ላለፉት በርካታ አመታት አፋር በተከታታይ በድርቅ ሲጠቃ ነው የቆየው ፤ ስለሆነም ድርቁ ለአፋር ማህበረሰብ ሌላ ፈተና ነው ማለት ይቻላል ። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ከ8 ወር በላይ ወደ ቄያቸው ያልተመለሱት የገደማይቱ ተፈናቃዮች የመፍትሄ ያለ እያሉ ነው። በገደማይቱ ሀምሌ 17 ቀን በነበረው ግጭት ምክንያት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ በርካታ ዜጎች እስካሁን ወደ ቄያቸው መመለስ አልቻሉም። እነዚህ ዜጎች በየመጠለያው ካምፕ እና በየዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት ተጠልለው ወራት ማለፋቸውን ገልፀውልናል። " ዞር ብሎ የሚያየን እና የሚጠይቀን አጥተናል " ያሉት…
#Afar #Somali

ዛሬ በአዳማ ከተማ የአፋርና የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ የሰላም ውይይት ማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ መሆኑን ለመስማት ተችሏል።

መድረኩ በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማምጣት አላማ ያደረገ ነው ተብሏል።

በውይይቱ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ፣የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ይህን የሰሙ ከ9 ወር በላይ በግጭት ምክንያት ከገደማይቱ የተፈናቀሉ ወገኖች መፍትሄ እንዲያገኙ አቤት በለዋል። ችግር ተፈቶ ወደ ቀደመው ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱም ፣ ፍትህም እንዲያገኙ ጠይቀዋል።

በገደማይቱ ሀምሌ 17 በነበረው ግጭር ከመኖሪያ ቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደቄያቸው አልተመለሱም።

እነዚህ ዜጎች በየመጠለያ ጣቢያ እና ዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት የተጠለሉ ሲሆን ዞሮ ብሎ የሚያያቸው እና የሚጠይቃቸውን እንዳጡ ለ20 እና 30 ዓመታት ከኖሩበት ቄያቸው ተፈናቅለው ያለፍትህ ሜዳ ላይ መቅረታቸውን ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።

ዛሬም ድረስ ችግር ላይ የሚገኙ ወገኖች መፍትሄ እና ፍትህን ይሻሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Somali #Afar #ሰላም #ውይይት

ትላንት የአፋርና የሱማሌ ኢሳ ማህበረሰብ የሰላም ኮንፈረንስ በአዳማ ተካሂዶ ነበር።

የሰላም ኮንፈረንሱ በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማምጣት ዓላማ ያደረገ ነው መሆኑን ሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።

በአካባቢዎቹ የሚታዩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ሰላምን ለማምጣት ወደ ግጭት ለሚያመሩ ጉዳዮችም መፍትሔዎች ተለይተው የተቀመጡበት መድረክ ነው ተብሏል።

የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ ማድረግ፤ በግጭት ምክንያት ከኖሩበት ቀዬአቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት ተጠልለው እየኖሩ ችግሮችን እየተጋፈጡ ያሉ ወገኖች ወደ ቀደመው ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱ ሊደረጉ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችንም በመድረኩ መነሳቱን ከሰላም ሚኒስቴር በኩል የወጣው መረጃ ያሳያል።

ባለፈው ዓመት በተነሳ ግጭት ከዘጠኝ ወር በላይ ቤታቸው ተፈናውለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በየዘመዶቻቸው ቤት የተጠለሉ በርካታ ወገኖች እንዳሉ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#Afar

ከትላንትና በስቲያ ፤ በአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳ ከምሽት 1 ሰዓት አንስቶ ለሊቱን ሙሉ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ በተለያዩ የቤት እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

የክልሉ አደጋ መከላከልና ስጋት አመራርና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ ሀሙስ ከምሽቱ 1 ሰአት ጀምሮ ሌሊቱን ሙሉ በጣለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት ፦

👉 13 ሺህ 834 ፍየል እና በግ፣
👉 180 የቀንድ ከብት፣
👉 20 ግመሎች እና 3 አህዮች ሞተዋል።

በክልሉ ባለዉ ድርቅ የቤት እንስሳዎቹ በመኖ እጥረት የተጎዱ በመሆናቸዉ ዝናቡን መቋቋም አለመቻላቸው አደጋውን የከፋ አድርጎታል ተብሏል።

በወረዳው ደርጌራ ፣ አፉማና ወአማ ቀበሌዎች በዝናቡ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።

የቤት እንስሳቶቻቸው ለሞቱባቸው ቤተሰቦች ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።

የጭፍራ ወረዳ አርብቶ አደር ጽ/ ቤት በበኩሉ ፤ ከወረዳዉ ስፋት ጋር በተያያዘ ገና መረጃ እየተሰበሰበ የሚገኝ በመሆኑ የሞቱ የቤት እንሰሳዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ለኢዜአ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከግንቦት 15 እስከ 20/2014 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙ ሰመራ እና አጋቲና ካምፖች በመባል በሚታወቁ ቦታዎች ውስጥ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ " ለደኅንነታቸው ጥበቃ እና በወንጀል ጥርጣሬ የሚፈለጉ ሰዎችን ለመለየት " በሚል ምክንያት ከትግራይ ክልል አዋሳኝ ከሆኑ 3 የአፋር ክልል ወረዳዎች ፦ - ከአባላ - ከኮነባ - ከበረሃሌ…
#Afar

በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ በሚገኝ የማቆያ ካምፕ ውስጥ #ያለፈቃዳቸው ተይዘው ከነበሩት የትግራይ ተወላጆች መካከል የተወሰኑት በአውቶብሶች እና የደረቅ ጭነት መኪኖች ተሳፍረው ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እየተወሰዱ እንደሆነ መግለፃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

በሺዎች የሚቆጠሩት የትግራይ ተወላጆች ከአፋሯ አብኣላ ተይዘው ወደ ሰመራ ተዘዋውረው የነበረ ሲሆን  ከ8 ወራት እስር በኋላ ወደ አብኣላ እየተመሰሉ መሆኑን ተናግረዋል።

በሰመራ ተይዘው የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን "በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል ብሎ ነበር።

https://t.iss.one/tikvahethiopia/71528?single

የትግራይ ተወላጆቹ ቀደሞ ወደሚኖሩበት የመኖሪያ ስፍራቸው እንዲመለሱ እያመቻች የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት (OCHA Ethiopia) መሆኑ የተነገረ ሲሆን ድርጅቱ ሰዎቹን " የአገር ውስጥ ተፈናቃይ (IDP) " ሲል ገልጿቸዋል።

ዜጎችን ወደነበሩበት ቦታ የመመለሱ ስራ በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደሚቀጥልም ገልጿል።

ነገር ግን ተመድ ባሰራጨው መረጃ ላይ በርካቶች በቃል አጠቃቀሙ ላይ ያለቸውን ተቃውሞ የገለፁ ሲሆን እነዚህ ተይዘው የነበሩት ዜጎች " ያለአንዳች ፍላጎታቸው በመውሰድ ነው " እንጂ የውሥጥ ተፈናቃይ አይደሉም ብለዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩት እዚህ ዜጎች ለወራት ተይዘው በቆዩበት ካምፕ ውስጥ የምግብ እና ሌሎች አገልግሎቶች ችግሮች እንደነበሩባቸው የተናገሩ ሲሆን ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋልጠው መቆየታቸውን እንደገለፁለት ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Oromia #Afar

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል እና በአፋር ክልል በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በኦሮሚያ ክልል አደጋው የደረሰው በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ሲሆን በአደጋው የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ከ6 ሟቾች በተጨማሪ 15 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

አደጋው ከአዳባ ከተማ ወደ ላጆ ከተማ ሲጓዝ በነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ መኪና በመገልበጡ የተከሰተ ነው።

መኪናው የመጫን ልኩ 28 ሰው ብቻ የነበረ ቢሆንም ከመጠን በላይ በመጫን 40 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ አደጋው መድረሱ ተገልጿል፡፡

በአፋር ክልል ደግሞ የትራፊክ አደጋ የደረሰው በሎጊያ ከተማ ሲሆን መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ተሽከርካሪው ጥዋት ከሎጊያ 15 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ አፍዴራ ሲጓዝ ኮሪ ወረዳ ልዩ ቦታው " ጉያህ " ላይ ተገልብጦ ነው አደጋው የደረሰው።  5 ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ 10 ሰዎች ቀለል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው።

አሸክርካሪዎች ይዛችሁ የምትጓዙት ክቡር እና የማይተካውን የሰው ህይወት ነው እና ሁሌም ጥንቃቄ ማድረግ፣ ህግ እና ስርዓትን ማክበር አትዘንጉ።

@tikvahethiopia