በሪያድ ከተማ ማንፋሐ እና ነሲም ተብለው በሚታወቁ አካባቢዎች ባለፉት 15 ውስጥ ቀናት የሳዐዲ ፀጥታ ኃይሎች ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ የኢትዮጵያውያን መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በመግባት ፍተሻ ሲያካሄዱ እንደነበር በወቅቱ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በሪያድ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ማድረሳቸው ተገልጿል።
በፀጥታ ኃይሎች በተካሄደው ፍተሻ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ወይም ዕቃማ ያላቸውን ሆነ የሌላቸውን አንድ ላይ ወደ ማረፍያ ተወስደው እንደነበረና ዕቃማ ያላቸውን ዕቃማቸው ተቀምቶ ከእስር ቤት የተለቀቁ ሰዎች መኖራቸውን ኤምባሲው መረጃ እንደደረሰው አሳውቋል።
በዚህ መሰረት ባለፉት ቀናት የሳዑዲ ፀጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት ፍተሻ ባካሄዱበት ወቅት የሳዑዲን ህግ በመጣስ የተለያዩ የመብት ጥሰት ድርጊቶች ተፈፅመውብናል / ጉዳት ደርሶብናል የሚሉ የኢትዮጵያ ዜጎች የደረሰባቸውን የመብት ጥሰት / ጉዳት በማስረጃ በማስደገፍ ከእሁድ ነሐሴ 3 ጀምሮ ኤምባሲው ድረስ በአካል በመቅረብ የተሟላ መረጃ እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ሒሩት ክፍሌ በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ!
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሒሩት ክፍሌ ለ3ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበር፡፡
ፖሊስ የምርመራ ስራውን እንዳልጨረሰ በመግለፅ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀጠሮ መዝገቡን ዘግቶ በ6,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል - #EZEMA

አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ!
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራራ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው ዕለት (ሐምሌ 28/2012 ዓ/ም) ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራራ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው ዕለት (ሐምሌ 28/2012 ዓ/ም) ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሹመት!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል። በዛሬ ውሎው በኢ/ር ታከለ ኡማ የቀረበለትን የሁለት ቢሮ ሃላፊዎችን ሹመት አፅድቋል።
በዚህ መሰረት:-
1. ወ/ሪት ፋይዛ መሐመድ ኡመር- የባህል ቱሪዝም እና ኪነጥበብ ቢሮ ኃላፊ
2. ወ/ሪት ሓዳስ ኪዱ ትዓራ - የሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል - #AMN

#ATTENTION
ይህ ከላይ በፎቶ የምትመለከቱት ሰልፍ 'የካ ክፍለ ከተማ' አነስተኛ ግብር ከፉዮች ጽህፈት ቤት ነው።
በቦታው የሚገኙ ተገልጋዮች 'አካላዊ ርቀታቸውን' ሳይጠብቁ ለኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተጋላጭነት በሚጨምር መልኩ እጅግ ተጠጋግተው ተሰልፈዋል።
በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ አባል ባለጉዳዮች ሀምሌ 30 አልፎ ላለመቀጣት በሚል እራሳቸውን ለቫይረሱ አጋልጠው እየተገለገሉ ነው ብሏል።
ጉዳዮ የሚመለከታችሁ አካላት የኮቪድ-19 በአዲስ አበባ ከተማ ያለበትን እጅግ አደገኛ ደረጃ በመረዳት መፍትሄ ብታፈላልጉ የተሻለ ነው።
ሌሎች ቦታዎች ላይም ተመሳሳይ ሁኔታ ካለ ተከታትሎ ማስተካከያ ቢደረግ መልካም ነው። ነገን የተሻለ ለማድረግ በሁሉም ቦታዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ብቸኛው አማራጭ ነው።

Audio
ምስጋና!
'LIFT ETHIOPIA' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝቡ ያለውን ድጋፍ የሚሰጥበትን በአይነቱ የተለየ መርሃ ግብር አዘጋጅቶ እንደነበር ይታወሳል።
'LIFT ETHIOPIA' ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው የድምፅ መልዕክት የቀረበውን ጥሪ ለተቀበሉና ለህዳሴ ግድብ በመላው ዓለም ባሉበት ሀገር ሆነው ድምፃቸውን ላሰሙና አጋርነታቸውን ለገለፁ የኢትዮጵያ ዜጎችና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ ምስጋና አቅርቧል።

#AtoLidetuAyalew
ኢዴፓ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በላከው ደብዳቤ አቶ ልደቱ አያሌው የአስም እና የልብ ህመም እንዳለባቸው በመግለፅ ፍፁም ለጤናቸው #አስጊ በሆነ ሁኔታ በቢሾፍቱ እስር ቤት ውስጥ መታሰራቸውን አሳውቋል።
ኢዴፓ የአቶ ልደቱ መርማሪን ጨምሮ አምስት (5) ፖሊሶች በእስር ቤቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አቶ ልደቱ እራሳቸው አረጋግጠውልኛል ብሏል።
ይህ ሁኔታ ከአቶ ልደቱ የጤና ሁኔታ አንፃር ለኮቪድ-19 ይበልጥ ተጋላጭ የሚያደርጋቸው ቢሆንም ምንም አይነት ጥንቃቄ በማይደረግበት እስር ቤት ውስጥ አሁንም እንዲታሰሩ በመደረጉ ህይወታቸው አደጋ ላይ ወድቋል ሲል አስታውቋል።
ፓርቲው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከሰላማዊ የትግል መስመር ውጭ ለአንድም ቀን ተንቀሳቅሶ እንደማያውቅና በአመፅና በነውጥ ዘላቂ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይገነባል ብሎ እንደማያምን በደብዳቤው ገልጿል።
ነገር ግን መንግስት በህግ ማስከበር ስም ከሁከትና ብጥብጥ ጋር ግንኙነት የሌለውን የተለየ ሃሳብ በማራመዱ የፓርቲውን የብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ልደቱን በግፍ አስሮታል ብሏል።
ኢዴፓ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የፃፈውን ደብዳቤ መሉ ሃሳብ ከላይ ባሉት ምስሎች ማንበብ ትችላላችሁ።
#TikvahEthiopia

አቶ ጉማ ሰቀታ በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ!
ዛሬ (ሃምሌ 28/2012 ዓ/ም) ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ጉማ ሰቀታ በ7,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ (ሃምሌ 28/2012 ዓ/ም) ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ጉማ ሰቀታ በ7,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሒሩት ክፍሌ በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ! በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሒሩት ክፍሌ ለ3ተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበር፡፡ ፖሊስ የምርመራ ስራውን እንዳልጨረሰ በመግለፅ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀጠሮ መዝገቡን ዘግቶ በ6,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ…
#UPDATE
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ተኛ ወንጀል ችሎት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ በዋስትና እንዲፈቱ የሰጠውን ውሳኔ ፖሊስ አልቀበልም ማለቱን ኢዜማ አሳወቀ።
ፍርድ ቤቱ ያሳለፈውን የዋስትና ውሳኔ ትዕዛዝ የኢዜማ ጠበቃ ሂሩት ታስረው ወደሚገኙበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይዘው የሄዱ ቢሆንም ፖሊስ የትዕዛዝ ወረቀቱን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም ብሏል ፓርቲው።
ፖሊስ በሂሩት ክፍሌ ዋስትና ጉዳይ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ ልደታ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይዟቸው መሄዱን ከኢዜማ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#COVID19
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረባ የሆኑ የፖሊስ አባላት በኮቪድ-19 መያዛቸውን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል።
ጋዜጣው በኮቪድ-19 የተያዙት አባላት ለጊዜው ቁጥራቸው ባይታወቅም ነገር ግን #በርካታ እንደሆኑ ለማወቅ እንደቻለ ገልጿል።

በአባይና ተከዜ ወንዝ ተፋሰስ ስር ባሉ አካባቢዎች በቀጣይ ቀናት ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ አጀንሲ #አስጠንቅቋል።
በተፋሰሱ ስር ያሉ ነዋሪዎች እራሳቸውን እና ንብረቶቻቸውን ከጎርፍ እንዲጠብቁ ኤጀንሲው ማሳሰቢያ መስጠቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል።

ችሎት!
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/አመራር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው እለት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ነበር።
በዚህም አቶ በቀለ የእርስ በእርስ ግጭት ወንጀል በማነሳሳት የተጠረጠሩ መሆናቸውን ተከትሎ መርማሪ ፖሊስ በቂ ምርመራ ማድረጉን በመግለፅ የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ መክፈቱን ለችሎቱ አስረድቷል።
መርማሪ ፖሊስ አቶ በቀለ ገርባ በአዲስ አበባና በአካባቢው እንዲሁም በሻሸመኔ ባስተላለፉት ትእዛዝ በተፈጠረ ሁከትና ብጥብጥ በትራንስፖርት ዘርፉ ብቻ በመንግስት 7 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ፤ በግል ደግሞ 29 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የሚያመላክት 45 ገፅ ሰነድ ማሰባሰቡን ጠቅሷል : https://telegra.ph/fbc-08-04

የአቶ በቀለ ገርባ ቀጣይ ቀጠሮ !
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቃቤ ህግ በአቶ በቀለ ገርባ ላይ የከፈተውን የቅድመ ክስ ምርመራ ለመመልከት እና በዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሐሙስ ሃምሌ 30/2012 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

#UPDATE የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ተኛ ወንጀል ችሎት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ በዋስትና እንዲፈቱ የሰጠውን ውሳኔ ፖሊስ አልቀበልም ማለቱን ኢዜማ አሳወቀ። ፍርድ ቤቱ ያሳለፈውን የዋስትና ውሳኔ ትዕዛዝ የኢዜማ ጠበቃ ሂሩት ታስረው ወደሚገኙበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይዘው የሄዱ ቢሆንም…
ሂሩት ክፍሌ በእስር እንዲቆዩ ተደረገ!
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የፖሊስን አቤቱታ የሚያይ ዳኛ ስላልተገኘ ሂሩት ክፍሌ በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ያስጠበቀላቸውን መብት ፖሊስ ጥሶ በእስር እንዲቆዩ አድርጓል ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ /ኢዜማ/ አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የፖሊስን አቤቱታ የሚያይ ዳኛ ስላልተገኘ ሂሩት ክፍሌ በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ያስጠበቀላቸውን መብት ፖሊስ ጥሶ በእስር እንዲቆዩ አድርጓል ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ /ኢዜማ/ አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 588 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,201 የላብራቶሪ ምርመራ 588 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 309 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 19,877 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 343 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 8,240 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 8,201 የላብራቶሪ ምርመራ 588 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 309 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 19,877 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 343 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 8,240 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦
- በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 75 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ ከነዚህ ውስጥ 16 ከለገጣፎ፣ 15 ከቢሾፍቱ፣ 11 ከአዳማና 11 ከምስራቅ ሸዋ ይገኙበታል።
- በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 19 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤13 ሰዎች ንክኪ ያላቸው፣6 ሰዎች የጉዞ ታሪክ ያላቸውና 3 ሰዎች የጉዞ ታሪክና ንክኪ የሌላቸው ናቸው።
- በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 19 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 181 ደርሰዋል።
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ባለፉት 24 ሰዓት አንድ ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 219 ደርሰዋል።
- በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 27 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፤ ከነዚህ መካከል 14 ሰዎች ከሰ/ሸዋ ዞን ናቸው። በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 607 ደርሰዋል።
- በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 8 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 291 ደርሰዋል።
- በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ፤ በቫይረሱ መያቸው የተረጋገጠው ሰዎች ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች አይደሉም።
- በአዲስ አበባ ባለፉት 24 ሰዓት 329 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 13,826 ደርሰዋል። በኢትዮጵያ ከተመዘገበው 7 ሞት ስድስቱ (6) በአ/አ ከተማ የተመዘገበ ነው (5 ከአስክሬን ምርመራና 1 ከጤና ተቋም)

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቤሩት በፍንዳታ ተናወጠች!
ዛሬ ከሰዓት የሊባኖስ ዋና ከተማ የሆነችው #ቤሩት በከፍተኛ ፍንዳታ መናወጧ ተሰምቷል። የሊባኖስ ጤና ሚኒስትር ሃማድ ሀሰን በፍንዳታው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን እና ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ለሊባኖስ ቴሌቪዥን (LBC) ተናግረዋል።
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

በመቐለ 'ዓዲ-ሓቂ' ትልቁ የገበያ ማእከል በደረሰው የእሳት አደጋ የወደሙት ሱቆች ቁጥር ከ520 እንደሚበልጡ የከተማውን ፖሊስ ዋቢ አድርጎ የጀርመን ሬድዮ ዘግቧል።
የእሳት አደጋው የደረሰው ባለፈው ቅዳሜ ለእሁድ አጥብያ ሲሆን የአደጋው መነሻ በትክክል አለመታወቁ ተጠቅሷል፡፡
የእሳት አደጋ በተከሰተበት የገበያ አዳራሽ ልብስ እና ጫማ መሸጫ ፣ የጥቅል ጨርቆች ማከፋፈያ፣ የቤትና ቢሮ እቃዎች መሸጫ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ መዉደማቸዉን ፖሊስ አረጋግጧል።
በአደጋው በንብረት እና ገንዘብ ላይ ከደረሰ ቃጠሎ ውጭ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የመቐለ ከተማ ፖሊስ ማሳወቁን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ መረጃ ይጠቁማል።