TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#PMOEthiopia

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 84ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2013 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 476,012,952,445 ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሹመት !

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥቅምት 04 ቀን 2013 ዶ/ር አረጋዊ በርሔን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብ/ም/ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ተቀንሰው የነበሩ መኮንኖች ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል።

ወደ ሰራዊቱ እንዲመለሱ ትዕዛዛ የተሰጣቸው ፦

1. ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ
2. ሌ/ጄኔራል ዬሐንስ ገ/መስቀል
3. ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ ናቸው።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በዛሬው እለት ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ ወደ ሀገር መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል - #PMOEthiopia

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እውቅና ያላቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጨምሮ ሁሉም ግለሰብ በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ የማያንፀባርቅ እና ያልተረጋገጠ መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PMOEthiopia

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል እያካደ የሚገኘውን "ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ" በብሔር ወይም በሌላ ወገንተኝነት ላይ የተቃኘ ነው የሚለውን የተሳሳተ እሳቤ አጥብቆ እንደሚያወግዝ ዛሬ ህዳር 9/2013 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

እየተካሄደ ባለው "የህግ ማስከበር ዘመቻ" የትግራይ ህዝብ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ይሆናል ሲል በመግለጫው ላይ ገልጿል።

* የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrAbdallaHamdok 

ዛሬ ጥዋት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብደላ ሃምኮድ ለ2 ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ቦሌ ኤርፖርት ተገኝተው ለሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የሱዳን የደህንነትና የፀጥታ እንዲሁም ወታደራዊ ባለስልጣናት አብረዋቸው መጥተዋል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

በኢትዮጵያ ገለልተኛ የብሔራዊ ኢኮኖሚ ም/ቤት ተመሰረተ።

* ዝርዝር መረጃ እና የምክር ቤቱ አባላት ስም ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@TIKVAHETHIOPIA
ከመጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.መ ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ ሹመቶች :

- መሐመድ ኢድሪስ መሐመድ የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

- ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

- ግዛው ተስፋዬ የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
'ምርጫው መራዘሙ አላስደሰተንም' - ክልሎች

ከጥር 2013 ዓ.ም. አንስቶ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ጋር በመሆን የክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ለምርጫ የሚያደርጉትን ቅድመ ዝግጁነት ለመገምገም እና ለሚነሱ ጉዳዮች መፍትሄ ለመስጠት ስብሰባዎችን ሲያካሂዱ የጠ/ሚ ፅ/ቤት አስታውሷል።

ከእነዚህ ስብሰባዎች የቀጠለ ስብሰባ ዛሬ ተካሂዷል።

የዛሬው ስብሰባ ከምርጫ ቁሳቁስ አቅርቦት፣ የምርጫ ጣቢያዎችን ከማዘጋጀት፣ ከመራጮች ምዝገባ እንዲሁም ሰላማዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ምርጫ እንዲከናወን የጸጥታ አካላት ካላቸው ዝግጁነት አንጻር በየክልሉ ያለውን የቅድመ ዝግጁነት ስራ ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

ከየክልሉ የተገኘው ሪፖርት ፥ በአጠቃላዩ የመራጮች ምዝገባ ቁጥር እና የምርጫ ፖሊሶችን አሰልጥኖ ዝግጁ የማድረግ ሂደቱ ጭማሪን ማሳየቱ ተመላክቷል።

የምርጫ ቦርድ መጪውን ምርጫ ለአጭር ጊዜ ማዘግየቱን አስመልክቶ፣ የክልል አመራሮች ምርጫው በቀደመው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንዲካሄድ ለማስቻል ያላቸውን ዝግጁነት እና ቁርጠኝነት በመጥቀስ መራዘሙ 'አላስደሰተንም' ስለማለታቸው ተገልጿል።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት የሚኒስትሮች ምክር ቤት 100ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 100ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጉዳዮች ፦

1.የፌዴራል የገቢ ግብር ደንብ፤
2. የመንግሥት ሠራተኞች እና የግሉ ዘርፍ ሠራተኞች ጡረታ ለመደንገግ በቀረቡት ረቂቅ ዐዋጆች ላይ ፤
3. የማዕድን ስምምነቶች
4. የተሐድሶ ሕክምና አገልግሎት ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው።

* ዝርዝር ጉዳዩ ከላይ ተያይዟል።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia