TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀዋሳ-ወቅታዊ ጉዳይ⬇️

ያልተጣራ ወሬ በህዝቦች መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ያደርጋል።

ከተማችን ሀዋሳ በርካታ ብሄሮችና ብሄረሰቦች #ተቻችለው እና #ተከባብረው የሚኖሩባት እንደሆነ ማንም የሚያውቀው ሀቅ ነው።

ይሁንና በቅርቡ በከተማው የተከሰተውን የፀጥታ ችግር መነሻ በማድረግ በከተማው ነዋሪዎቾ መካከል #ጥርጣሬ እና #አለመደማመጥ እንድፈጠር እንዲሁም ለዘመናት የከተማችን እሴቶች የሆኑት መከባበርና መቻቻል እንድሸረሸሩ እኩይ አላማ ያላቸው ግለሰቦች የተለያዪ የውሸት መረጃዎችን በማህበራዊ ገፅ ላይ እየለቀቁ እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ።

ለአብነትም በ13/12/2010 በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን የጫነ ተሽከሪካሪ ተይዟል ተብሎ የተለቀቀው #የሀሰት ወሬ እንደሆነ #ከፓሊስ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

#እውነታው የተያዘው ተሽከሪካሪ 15 ቦንዳ በህገ ወጥ መልኩ /ኮንትሮባንድ/ የገባ እቃ የጫነ እንደሆነ የተረጋገጠ ሲሆን ሌላው በህገ ወጥ መልኩ የተገነቡ ቤቶችን ለማፍረስ የተንቀሳቀሱ ፖሊሶች ተገደሉ ተብሎ የተለቀቀው ፎቶግራፍ የጥፋት ሀይሎች አቀነባብረው የለቀቊት
#የሀሰት_መረጃ እንደሆነ ለመጠቆም እንወዳለን።

በመጨረሻም የከተማችን #ፀጥታ እና #ሰላም እንዳይደፈርስ እንዲሁም በከተማው ህዝብ መካከል ጥርጣሬና አለመተማመን እንዳይፈጠር በዚህ በውሸት መረጃ ህብረተሰቡን በስጋት ላይ የሚትጥሉ አካላት #ከእኩይ ዲርጊታችሁ እንድትታቀቡ እያለ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር #ያሳስባል

የከተማችን ህዝብ በማህበራዊ ገፅ የፌክ አካውንት የከፈቱ አካላት በየጊዜው በሚያሰራጬት #የአሉባልታ ወሬ #እንዳይሸበር እናስታውቃለን።

©አቶ ደስታ ዶጊሶ #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ በረከት ስምዖን☎️ታዲያስ አዲስ⬇️

ዛሬ ከታዲያስ አዲስ ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ በረከት ስምዖን፦

▪️አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ኤርትራ ሄደዉ የህዋት ባለስልጣናት አስቸገሩኝ በማለት ለኤርትራዉ ኘሬዘዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ሲነግሯቸዉ አባሯቸዉ ብለዋል።

▪️እኔ አንድም ብር አልበላሁም መፅሐፌን በስፖንሰር ነዉ ያሳተምኩት።

▪️እኔ በፖለቲካዉ አልቀጥልም የራሴን ሥራ እሰራለሁ።

▪️አቶ ደመቀ መኮንን አልደግፍም በማለቴ ነዉ ከብአዴን የታገድኩት።

▪️አቶ ገድ አንዳርጋቸዉ የወጣቶች ዙሪያ ለዉጥና ልማት እንዲፍጠን ኘሮጀክት ቀርጪ ሰጥቸዉ ሼልፍ ላይ አስቀምጦታል።

▪️አሁን ያለሁ ሁኔታ አስጊ ነዉ ይህም የአመራሩ ድክመት ነዉ።

▪️ዜጎች ከቄያቸዉ ይፈናቀላሉ ይሄ #በቀደሙት አመታት #የለም ነበር።

▪️እኔ ለዉጥ እናምጣ ስል ጥርስ ውስጥ ገባሁ ያጠፋሁት ነገር የለም፣ እያወኩ ያደረኩት ነገር የለም ይቅርታ የሚያስጠይቀኝ ነገር የለም።

▪️መደር መቀነስ የሚባለዉ አልደግፍም
ለዉጡን እደግፋለሁ ዶ/ ር አብይም አህመድ ጋርበአካል ባለፈዉ ሳምንት ተገናኝተናል።

▪️ዛሬም በስልክ አግኝቻቸዋለሁ ያዘዙኝ ስራ አለ እየሠራሁ ነዉ።(ዶ/ር አብይ)

▪️አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር የነበረዉ ድክመት ለዉሳኔ ቁርጠኛ አይደለም አይወስንም ዶ/ ር አብይ አህመድ ይወስናል በዚህ የተሻለነዉ ቁርጠኝነቱም አለዉ።

▪️እገዳዉን በሚዲያ ነዉ የሰማዉት ስብሰባዉ ዉስጥ ስለ #ጥረት የተባለ የለም።

▪️ስብሰባ ጠርተዉኝ ነበር በኢሜል ለብአዴን ጽ / ቤት ኃላፊ ጋር ደዉዬ የክልሉን #ፀጥታ ጠይቄ አስተማማኝ ስላልሆነ #አትምጣ ተባልኩ።

▪️ዜናዉን ስሰማ ደመቀ መኮንን ጋር ደወልኩ አያነሳም ሌሎቹም እንደዛዉ።

▪️እኔ በአገሬ በነፃነት መንቀሳቀስ ነዉ የምፈልገዉ ልጆቼም እኔም እዚህ ነዉ መኖር የምንፈልገዉ።

▪️ቀሪ እድሜይን ባህር ዳር ጊዜ አሳልፋለሁ ብዬ አስባለሁ።

▪️እንደ ልደቱ ሁኔታወች ጥሩ ስላልሆኑ መራቅ ነዉ የሚሻለዉ።

▪️አሁን ነፃነትን ተንቀሳቅሶ የመኖርና የመስራት መብቴን አስከብራለሁ ምን የሚያስፈራኝ ነገር የለም የወፊቱን አብረን እናያለን።

▪️አናጎሜዠ አርፈሽ ስራሽን ስሪ በዉስጥ ጉዳያችን ጣልቃ አትግቢ ይሄ ፖልቹጋል ወይም አዉሮፖ ጉዳይ አደለም ነዉ የምላት።

▪️ዶ/ ር አብይ ወደ ስልጣን እንደመጣ በቤልጅየም የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር እንድሆን ጠይቆኝ ነበር ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች አንደኛ እኔ ከኢትዮጵያ ርቄ መኖር ስለማልችልና ስለማልፈልግ የሃገሬን ሁኔታ በቅርብ
ለመከታተል ስል ጥያቄውን አልተቀበልኩም ነበር እኔ አምባሳደር ብሆን ቤተሰቤን ይዤ መሄድ እችላለሁ ነገር ግን ሃገሬ ውስጥ ሆኜ ሁኔታዎችን በቅርብ ለመከታተል ስል ነው የዶ / ር አብይን ጥያቄ ያልተቀበልኩት እሱም ተረድቶኛል።

▪️ከዶ/ ር አብይ ጋር በየጊዜው እንገናኛለን ለምሳሌ ዛሬ ጠዋት በስልክ ተገናኝተናል። በአካል ደግሞ የዛሬ ሳምንት ተገናኝተን ተወያይተናል። ጥሩ ግንኙነት አለን።

(አቶ በረከት ስምኦን ከታዲያስ አዲስ ሰይፉ ፋንታሁን ጋር በነበራቸው ቆይታ ከተናገሩት)

©ዘሪሁን ግርማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ብዙዎቹ ቦታዎች ላይ(አንፎ፣ አሸዋ ሜዳ፣ ቡራዩ) የፀጥታ ካላት ገብተው ሰላም ለማስከበር እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። እስካሁን ከቻናላችን አባላት የሚጡት መልዕክቶች ብዙ ቦታ ላይ #ፀጥታ መስፈኑን የሚገልፁና ለደህንነታቸው አስተማማኝ ጥበቃ እንዲደረግ የሚጠቁሙ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update የባሕር ዳር ከተማ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር በመተባበር በበጎ ፎቃደኛነት #ፀጥታ የማስከበር ተግባር እያከናወኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

©የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tiovahethiopia
#Update የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዮስ ለክልሉ #ሰላምና #ፀጥታ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መግለጫ‼️

(15.04.2011ዓ.ም የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ)

ወቅታዊ የሀዋሳ ከተማን #ፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በከተማው አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የተሰጣዊ ዜጣዊ መግለጫ፦

ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈጣን ፖለቲካዊ የለውጥ ሂደት ውስጥ መሆኗ በግልፅ የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡ ለውጡን ተከትሎ በከተማችን ሀዋሳም አልፎአልፎ አሉታዊ ክስተቶች ይስተዋላሉ፡፡

ከእነዚህ አሉታዊ ክስተቶች መካከል ከሰኔ 10/2010 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ እየተስተዋሉ ያሉት ግጭቶችና የፀጥታ መናጋት በቀዳሚነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ይህን አልፎ አልፎ የሚከሰተው ግጭት ሀዋሳ ከተማ የምትታወቅበትን ነዋሪዎቿ ለዘመናት ያዳበሩት የመከአበክሮ የመፈቃቀድ እና አብሮ የመኖር እሴት እንዳይሸረሽር መንግስት አበክሮ በመስራት ላይ ነው፡፡

በከተማዋ ለዘመናት የቆየውን አብሮ የመኖር እሴት ለማጠልሽት፣ ቅሬታ ለመፍጠርና የጥላቻ ጥቁር ነጥብ ጥለው ለማለፍ የሚዳክሩ አካላትን ጥረት ለማክሸፍና የህግ የበላይነትን ለማስፈን ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ ግጭቶች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ የጥፋት ሀይሎችን ለህግ በማቅረብ ባጠፉት ልክ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፤ ወደፊትም ተጠናክሮ ቀጥላል፡፡

ይሁንና ፀረ-ሰላም ሀይሉ ከድርጊቱ ባለመቆጠብ የተሳሳተ የትግል ስልቱን በመቀያየር የእውቀት መገበያያ የሆነውን ትምህርት ቤት የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለትም በሀዋሳ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ በሚገኘው አዲስ ከተማ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት
ቤት ሁከትና እረብሻ በመፍጠር 12 ወጣቶች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሰባቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ ተማሪ ያልሆኑ መሆናቸው ተለይቷል፡፡

በግጭቱም እርስበእርስ ድንጋይ በመወራወር በአስሩ ላይ ቀላል ጉዳት እንዲሁም ለፀጥታ ሀይሉ ባለመታዘዝ በሁለቱ ላይ ደግሞ ከባድ አደጋ ደርሷል፡፡

ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ ወጣቶች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል እና በአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

የረብሻው መንስኤ ገና በፀጥታ ሀይሉ #በመጣራት ላይ ያለ ቢሆንም በርካታ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ አካላት ያልሆኑ ነገር ግን እራሳችውን ከተማሪ ጋር ያመሳሰሉ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት ተማሪዎችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ከተዋል፡፡

ክስተቱን #የብሔር_ግጭት ቅርፅ ለማስያዝ ጥረት ለማድረግ የሞከሩ ቢሆንም አብሮ መኖርን ባህሉ ያደረገው የከተማው ነዋሪ ግን አልተባበራቸውምና ልፋታቸው ሳይሳካ #መና ሆኖ ቀርቷል፡፡

በዚህ ድርጊት #ጠንሳሽነትና ተሳታፊነት የተጠረጠሩ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር የማዋል ስራ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም
ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በፀጥታ ሀይሉና በህብረተሰቡ የጋራ ጥረት የከተማው #ፀጥታ_ሁኔታ ወደነበረበት የተመለሰ ሲሆን ለከተማው ሰላም ወዳድ ህዝብ የከተማው አስተዳደር ያለውን ክብርና አድናቆት እየገለፀ በቀጣይም ነዋሪው ከመንግስት ጎን በመቆም የከተማውን ሰላም ለማደፍረስና አብሮ የመኖር እሴትን ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ አካላትን አጋልጦ በመስጠት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪውን እያቀረበ የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ሰላም እና ፀጥታ የማስጠበቅ ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታውቃል፡፡

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
BBC አማርኛ ~ ስለቴፒ ከተማ ግጭት‼️

በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገለፁ።

ግጭቱን ተከትሎም ጥር 5/2011 ዓ. ም የዓመቱን ትምህርት መስጠት የጀመረው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ትምህርት #መቋረጡን ተሰምቷል።

ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገው በዩኒቨርሲቲው ቴፒ ግቢ ተማሪ እንዳለው ከትናንት በስቲያ ግጭቱ ሲፈጠር መስጊድ ሰፈር (ባጃጅ ሰፍር) አካባቢ ከጓደኞቹ ጋር ወጣ ብሎ ነበር።

"በድንገት አካባቢው በግርግር ተናወጠ፤ በተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ማን ለማን እንደሚተኩስ አይታወቅም፤ ቀውጢ ተፈጠረ" ይላል።

በወቅቱም እነርሱም ራሳቸውን ለማዳን መንደር ለመንደር እየተሹለከለኩ ወደ ግቢያቸው እንዳመሩ ይናገራል።

በጊዜው በቴፒ ካምፓስ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት ችግር አጋጥሞ ስለነበር በግቢው ውስጥም ውጥረት ነግሶ ነበር ይላል። ምክንያቱ ምን እንደነበር እርግጠኛ ባይሆንም በከተማው ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ ምግብ አብሳዮቹ በሥራ ገበታቸው ላይ ባለመገኘታቸው መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።

አካባቢው #ከተረጋጋም በኋላ በርካታ ቤቶች ወደተቃጠሉበት ስፍራ እንደሄዱና 'ጀምበሬ' እየተባለ የሚጠራው ሰፈር ሙሉ በሙሉ #መውደሙን እንደተመለከተ ተናግሯል።

በዩኒቨርሲቲው የ3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ይህ የዓይን እማኝ እንደሚለው በአካባቢው በየዓመቱ ችግር እንደሚነሳ በማስታወስ አሁንም በግጭቱ ምክንያት ትምህርት #ተቋርጧል

በሚዛን ቴፒ አካባቢ የቆየ የመዋቅር ጥያቄ ነበር የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የቴፒ ከተማ ነዋሪ እንደገለፁት በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በግምት የአንድ ትልቅ ቀበሌ 1/3ኛ የሚሆን ሰፈር ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

"ከዚህ በፊት ቴፒ በሸካ ዞን ሲተዳደር ቆይቷል፤ ሕዝቡ ያንን በመቃወም በዞኑ መተዳደር አንፈልግም የሚል ጥያቄ በማቅረቡ እርሱን ሰበብ ተደርጎ ጉዳዩ ወደ ብሔር ግጭት አመራ" ይላሉ።

ህዝቡ የተለያየ ኮሚቴ አዋቅሮ ለጥያቄው መልስ ለማግኘት እየተጠባበቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ባልታሰበ ሁኔታ ሌሊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ይናገራሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድንጋይ በመወራወር ተጀምሮ በመንገድ ዳር ያሉ የሚከራዩ ቤቶችን #በማቃጠል ነው የተጀመረው።

ጥቃቱ ቀን ጋብ ብሎ ከቆየ በኋላ ሌሊት ከ9:00 ሰዓት በኋላ በርካታ ቤቶች እንደተቃጠሉና ንጋት ላይ ወደ #ጫካ ሸሽተው የነበሩት የሰፈሩ ነዋሪዎች ደርሰው ለማጥፋት ሲሞክሩ እንደነበር ይናገራሉ።

ሰዎች በተኙበት ቤቶችና መጋዘኖች ተቃጥለዋል፤ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል የሚሉት መምህሩ፤ "በወቅቱ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ እርስ በርስ እየተጠራሩ ወደ ጫካ ሸሹ፤ ይሁን እንጂ አዛውንቱ የጓደኛዬ አባት አገር ሰላም ብለው በተኙበት በስለት ተገድለዋል" ይላሉ።
"የእኔ ቤተሰቦች ንብረታቸው ተዘርፏል፤ ቤታቸው ወድሟል" ሲሉ በሃዘን ይገልፃሉ።

ትናንት በቴፒ ከተማ በየመንገዱ ላይ የሚቃጠሉ የመኪና ጎማዎች፤ በቁጣ የተነሱ ወጣቶችና ነበር የሚታየው፤ የተኩስ ድምፅም ይሰማ ነበር።

በአንፃሩ ዛሬ የከተማው ነዋሪዎች በግጭቱ የሞቱትን ሰዎች ለመቅበር በተለያየ ቦታ ተበታትነው ስለሚገኙ በአንፃሩ #መረጋጋት ይታይበታል ብለዋል።

በወቅቱ ሕዝቡ የፀጥታ ኃይሎች #ጣልቃ ይገባሉ ብሎ ቢጠባበቅም ግጭቱን ለማስቆም ምንም እርምጃ ባለመወሰዱ ጉዳት መድረሱንና ችግሩ ከተከሰተ በኋላ ከስፍራው መድረሳቸውን ተናግረዋል።

መምህሩ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ትምህርት የጀመረው ዘግይቶ ቢሆንም አሁንም በዚሁ ግጭት ምክንያት በቴፒ ካምፓስ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን ይገልፃሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት ለተማሪዎቹ ደህንነት ሲባል ተማሪዎች በግቢው ውስጥ እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን በዩኒቨርስቲው ሁለት ግቢዎች ውጥረትና ስጋት ይታያል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳረ አቶ የሽዋስ አለሙ በበኩላቸው #ራስን_በራስ የማስተዳደር የቆየ ጥያቄ ቢኖርም የአሁኑ ግጭት መነሻ ግን ተቋርጦ የነበረ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመር ነው ይላሉ።

አስተዳዳሪው እንዳሉት በግጭቱ 7 ሰዎች ሲሞቱ 100 የሚጠጉ ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 1500 ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

የፌደራል፣ የክልልና የመከላከያ የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው #ፀጥታ ለማስፈን እየሰሩ መሆናቸውን አስተዳዳሪው ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia