TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ዳግም #ሞት እና #ውድመት ውስጥ መግባቱ ይቅርብን " - የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፤ በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ጦርነት ባስቸኳይ እንዲቆምና ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ተማጸነ።

" ዳግም ሞት እና ውድመት ውስጥ መግባቱ ይቅርብን " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

ጉባኤው በላከልን መግለጫ ጦርነት ለየትኛውም አይነት የፖለቲካዊ ችግር መፍትሔ ሆኖ አያውቅም ብሏል።

" ፖለቲካዊ ችግር መፈታት ያለበት መከባበር ባለበት የጋራ ጥቅም በሚያስቀድም ሁኔታ በሚደረግ የፖለቲካ ውይይት ነው " ያለው ጉባኤው ፤ " ውይይቱ ፦
- ብሶት የወለዳቸውን ምሁራንን፣
- የሀገር ሽማግሌዎችን፣
- የሃይማኖት አባቶችን፣
- ወጣቶችን እና ሴቶችን ጭምር ያካተተ ቢሆን የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ሙሉ እምነታችን ነው " ሲል ገልጿል።

ይህ እንዲሆን የመንግሥት #የፖለቲካ_ፈቃደኝነት በጣም አስፈላጊ እንደሚሆን አመልክቷል።

ምክንያቱም " መንግስት ከሁሉም በላይ እኛ በብዙ መልኩ ወንድማማችና እህትማማች የሆነውን ኢትዮጵያውያንን በጋራ የማምጣት አቅም አለው ብለን ስለምናምን ነው " ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በዚሁ መግለጫው ፤ በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ጦርነት ባስቸኳይ እንዲቆምና በውይይት ችግሮች እንዲፈቱ መንግስትንና ተፋላሚ ወገኖችን አጥብቆ ተማጽኗል።

" በዚህ በፍልሰታ ጾም ጸሎት ወቅት ልቦናችንን ወደ እግዚአብሔር እንድንመልስ ፤ ስለ ሰላም ፣ ፍትህ፣ ውይይት እንድንጸልይ ለምዕመኖቻችንና በጎ ፊቃድ ላላቸው ወገኖቻችን ሁሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን " ብሏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia