TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update BiT-ባህር ዳር⬇️

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የ3ኛ ዓመት ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች አጠቃላይ ፈተና (Holistic Exam ) አንፈተንም በማለታቸው የባሕር ዳር ቴከኖሎጅ ኢንስቲትዩት የአካዳሚክ ካውንስል የ3ኛ አመት ተማሪዎች ለአንድ አመት ማለትም 2011 የትምህርት ዘመንን ከትምህርት ገበታ እንዲታገዱ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ይህ ግን የዩንቨርሲቲው ሴኔት ውሳኔ
አለመሆኑን #ተረጋግጧል

አሁን ላይ ደግሞ ዩኒቨርሲቲው በባሕር ዳርና አካባቢው ያሉ የተማሪዎች ወላጆችን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ሊያወያይ ነው። ውይይቱ ነገ ሰኞ
ነሐሴ 21/2010 ዓ.ም. በቴክኖሎጄ ኢንስቲትዩት ፖሊ ግቢ ከቀኑ 8፡00 ይጀመራል። አወያዩም የዩኒቨርሰቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኘ ናቸው።

ዶክተር ፍሬው ተገኘ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንደተናገሩት የውይይቱ ዓላማ በተማሪዎቹ እና በቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩቱ መካከል የተፈጠረውን ችግር ትክክለኛ ምክንያት ለወላጆች ለማስረዳት እና መፍትሄ ለመሰጠት ነው።

በምዘና መመሪያው ላይ ግን #ማሻሻያ አልተደረገም ነው ያሉት። በመሆኑም ተማሪዎች ፈተናውን ለመፈተን ፈቃደኛ ከሆኑ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት #ይቅርታ ሊያደርግላቸው እንደሚችል ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት።

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተመን ማሻሻያ‼️

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመን #ማሻሻያ
ማድረጉን አስታወቀ።

የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ #ሽፈራው_ተሊላ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ አዲሱ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመን ከፊታችን ታህሳስ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ነው።

የዋጋ ንረትና አለም ላይ ያለው የሃይል ተመን ለማሻሻያው ምክንያት መሆናቸውንም ዋና ስራ አስፈጻሚ ተናግረዋል።

አሁን በተደረገው ማሻሻያ መሰረትም ተጠቃሚው ከ12 አመት በፊት በነበረው የሃይል ዋጋ ተመን መሰረት የሚከፍል ይሆናል ነው ያሉት።

በተመኑ መሰረት ተጠቃሚው የወጭውን 25 በመቶ ሲሸፍን ቀሪው 75 በመቶ ደግሞ በመንግስት ድጎማ የሚደረግበት ነው ተብሏል።

ማሻሻያው በሰባት እርከኖች የተከፈለ ሲሆን፤

እርከን 1: እስከ 50 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በነበረው ክፍያ በኪሎ ዋት 0 ነጥብ 2730 ብር ይቀጥላል፤

እርከን 2: እስከ 100 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 0 ነጥብ 6644 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 0 ነጥብ 7670 ብር፤

እርከን 3: እስከ 200 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 3436 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 1 ነጥብ 6250 ብር፤

እርከን 4: እስከ 300 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 6375 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ብር፤

እርከን 5: እስከ 400 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 7917 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ነጥብ 2000 ብር፤

እርከን 6: እስከ 500 ኪሎ ዋት ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 1 ነጥብ 9508 ብር የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ነጥብ 4050 ብር እንዲሁም

እርከን 7: ከ500 ኪሎ ዋት በላይ ለሚጠቀሙ ከዚህ ቀደም በኪሎ ዋት 2 ነጥብ 0343 የነበረው በአዲሱ ተመን 2 ነጥብ 4810 ብር ይሆናል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ‼️

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ ታሪፍ ላይ #ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።

ኢንተርፕራይዙ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የተሻሻለው ታሪፍ ከየካቲት 22 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

ማስተካከያው በክፍያ ጣቢያና በተሽከርካሪ አይነት የተደረገ ሲሆን ከ2 እስከ 16 ኪሎ ሜትር ለተሽከርካሪ 1 እና 2 የተደረገው የዋጋ ተመን 15 ብር ነው።

ከ2 እስከ 64 ኪሎ ሜትር ከተሽከርካሪ 5 እስከ 7 የተደረገው የዋጋ ተመን 80 ብር ሆኗል።

ሌሎች የዋጋ ጭማሪዎችን በኢንተርፕራይዙ ድረገጽ www.etre.com.et መመልከት ይቻላል።

ኢንተርፕራይዙ አብዛኛው ለጥገና የሚውል ጥሬ ዕቃ በአገር ውስጥ ስለማይገኝና ከወቅቱ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አንጻር የውጭ ብድርን በብቃት ለመክፈል የታሪፍ ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉን አስታውቋል።

ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ግሽበት የሚያስከትለውን ጫና ለመቋቋምና በአገልግሎት አሰጣጥ የተገኙ ልምዶችን በመውሰድ አሳማኝና መጠነኛ የታሪፍ ማሻሻያ ተደርጓል ነው ያለው።

የመንገዱ ተጠቃሚዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግና የተደረገውን የታሪፍ ለውጥ አውቀው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ኢንተርፕራይዙ አሳስቧል።

ኢንተርፕራይዙ ለጥገናና ለውጭ እዳ ክፍያ በየዓመቱ የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚያደርግ ቢያስታውቅም ለ4 ዓመታት በነበረው ታሪፍ ሲሰራ ቆይቷል።

በተያዘው በጀት ዓመት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የክፍያ ታሪፍ ማሻሻያ አጥንቶ ተግባራዊ አድርጓል።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን የአዲስ አዳማን የፍጥነት መንገድ የማስተዳደር፣ በክፍያ የመንገድ አገልግሎት የመስጠት፣ መንገዱን የማስጠገንና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎች ሃላፊነት ተሰጥቶታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ዲዛይን #ማሻሻያ እንዲደረግ አሜሪካ ቦይንግ ኩባንያን ጠየቀች፡፡ አሜሪካ ጥያቄውን ያቀረበችው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይግ 737 ማክስ 8 አሮፕላን እሁድ እለት ተከስክሶ 157 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን ተከትሎ ነው፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባለፉት ስድስት ወራት #ማሻሻያ ሲደረግበት በቆየው የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የማሻሻያ ሰነድ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማሻሻያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብድር ላይ ጥሎት በነበረው ገደብ ላይ ማሻሻያ አደርጓል።

ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ከብድር አቅርቦት ጋር በተያያዘ የጣለውን ገደብ ታሳቢ ያደረገ ማሻሻያ በማድረግ፣ ባንኮች አምስት የብድር ዓይነቶችን መፍቀድ እንደሚችሉ አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ አርብ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ለባንኮች ባስተላለፈው መልዕክት እንዳስታወቀው፣ ባንኮች የሰጡትን ብድር ለማስመለስ ሐራጅ ያወጧቸውን ንብረቶች ለመግዛት ለሚጠይቁ ገዥዎች ብድር መስጠት ይችላሉ፡፡

ብሔራዊ ባንክ ብድር ይፈቀዱ ያላቸው በሁለተኛና በሦስተኛ ወገኖች መካከል የሚደረግ ግብይትና ለባንክ ሠራተኞች የሚሰጥ አስቸኳይ ብድር መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልተው የመኖርያ ቤት ለመግዛት ወይም ለመገንባት ከታመነባቸውና ከፀደቁ ድርጅቶችና ከተቋም ሠራተኞች ለሚቀርቡ የብድር ጥያቄዎች፣ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት የሚችሉ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች የላከው ማሻሻያ ያመለክታል፡፡

Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#ማሻሻያ

በደቡብ ክልል ለአስቸኳይ አዋጁ ማስፈጸሚያ የተጣሉ ገደቦች ላይ ማሻሽያ መደረጉን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

በክልሉ ነዋሪዎች እጅ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ለመመዝገብ እስከ ህዳር 10/2014 ድረስ በገደብ የተያዘ ስራ የተሰራ ሲሆን በዚህም ወቅት 27 ሺሕ 477 የጦር መሳሪያዎች ተመዝግቧል።

ነገር ግን በክልሉ አለ ተብሎ ከሚገመተው አንጻር ቁጥሩ ዝቅተኛ ነው።

የምዝገባው ጊዜ አጭር በመሆኑና በተላያዩ ምክንያቶች የምዝገባውን ጊዜ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እስከ ሕዳር17/2014 ዜጎች በእጃቸው ያለውን የጦር መሳሪያ በአፋጣኝ ወደ ሚመለከተው አካል ቀርበው እንዲያስመዘግቡ ተብሏል።

ይሄን መመሪያ ተላልፈው የጦር መሳሪያ ይዘው በተገኙ ግለሰቦች ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሏል።

እስካሁን ባለው ከ80 ሺህ በላይ የሚሆኑ ባለ 2 ሞተር ሳይክሎች ተመዝግበው ወደ ህጋዊ ሰርዓት የገቡ ሲሆን አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሞተር ሳይክሎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደ ምዝገባው አልመጡም።

በዚህም ተጫማሪ ሰባት ቀናት የምዝገባ እድል የተሰጠ በመሁኑ ባለንብረቶች እስከ ህዳር 17/2014 ድረስ እድሉ እንዲጠቀሙ ተብሏል።

ከዚህ በፊት በ2 እግር ሞተር ስይክልና ባለ3 እግር ባጃጆች እስከ አመሻሽ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ መመሪያ የተላለፈ ሲሆን አሁን ግን ከጥብቅ ቁጥጥር ጋር እስከ ምሽት 2 ሰዓት ድረስ ፍቃድ ተሰጥቷል።

ሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ተነስቶ በጥብቅ ቁጥጥር ተተክቷል።

#SRTA

@tikvahethiopia
#DireDawa

#ማሻሻያ

በድሬዳዋ አስተዳደር እሁድ ጠዋት ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ እንዲሆን የተወሰነው ውሳኔ ላይ ማሻሻዮች ተደርጎበታል።

በድሬዳዋ አስተዳደር በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ላይ ከጠዋት 12 ሰአት እስከ 4 ሰአት ድረስ በከተማዋ ላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል ።

በዚሁም ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ ከሀይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል ።

በተለይም እድሜያቸው የገፍ እናት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እሁድ ወደ ቤተ-እምነቶች ለመሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በእጅጉ እየተቸገሩ ከመሆናቸው ባለፈ የጤና እክል ያለባቸው አካላትም ረጅም እርቀት በእግር ለመሄድ መቸገራቸውንም የሀይማኖት አባቶቹ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

ስለሆነም ማሻሻያ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እሁድ ጠዋት በከተማዋ ላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከነዋሪው ህብረተሰብ እንዲሁም ከሀይማኖት አባቶች የተነሱትን ጥያቄዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት እሁድ ጠዋት ሙሉ ከተማው ለትራንስፖርት ክፍት እንዲሆን መወሰኑን አሳውቀዋል።

ነገር ግን ከኮኔል ድልድይ አንስቶ ከዚራ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ለትራንስፖርት ዝግ እንደሚሆንም ከንቲባው ተናግረዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከሰኔ 23 / 2015 እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባለበት እንደሚቀጥል አስታውቋል። በዚሁ መሠረት ፦ 1. ቤንዚን 👉 በሊትር 69 ብር ከ52 ሳንቲም 2. ነጭ ናፍጣ 👉 በሊትር 71 ብር ከ15 ሳንቲም በሊትር…
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የሁሉም ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እስከ ነሀሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በሀምሌ ወር ሲሸጥ በነበረው ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት ፦

1. ቤንዚን 👉 በሊትር 69 ብር ከ52 ሳንቲም

2. ነጭ ናፍጣ 👉 በሊትር 71 ብር ከ15 ሳንቲም በሊትር

3. ኬሮሲን 👉 በሊትር 71 ብር ከ15 ሳንቲም

4. የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 በሊትር 65 ብር ከ35 ሳንቲም

5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 57 ብር ከ97 ሳንቲም

6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 56 ብር ከ63 ሳንቲም ይሸጣል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በመጪዎቹ ጊዜያት የአለም የነዳጅ ገበያን መነሻ በማድረግ አስፈላጊው #ማሻሻያ የሚደረግ መሆኑን አመልክቷል።

@tikvahethiopia