TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዓለም ዙሪያ ፦

#ካናዳ ፦ የካናዳው ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ አነስተኛ የእጅ ሽጉጥ መግዛትም ሆነ መታጠቅ እንዲከለከል ጠይቀዋል። የትሩዶ መንግሥት በጠቅላላው የእጅ ሽጉጥ መግዛት ሆነ ቤት ማስቀመጥ በሕግ እንዲያስቀጣ ረቂቅ እያወጣ ነው። ረቂቁ እንደሚለው ካናዳዊያን የእጅ ሽጉጦቻቸውን ባይነጠቁም ከዚህ በኋላ አዲስ መግዛት ግን አይችሉም። ትሩዶ ይህን ሐሳብ ያፈለቁት በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት አንድ አፍላ ታጣቂ 19 ሕፃናትን ተኩሶ ከገደለ በኋላ ነው።

➡️ #እስራኤል #UAE ፦ እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የነፃ ንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል ፤ ይህ እስራኤል ከአረብ ሀገር ጋር ያደረገችው የመጀመሪው ትልቅ ስምምነት ነው።

➡️ #ሴኔጋል ፦ የሴኔጋል ፖሊስ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰው እና የ11 ህጻናት ህይወት ከቀጠፈው የእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል።

➡️ #ሩስያ ፦ በያዝነው ዓመት 70ኛ ዓመታቸውን የሚደፍኑት የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጤና እክል ምናልባትም በካንሰር ህመም እየተሰቃዩ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ያልተረጋገጡ የመገናኛ ብዙኃን ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ግን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታመዋል መባሉን ሀሰት ሲሉ አስተባበሉ። ላቭሮቭ ፕሬዚዳንት ፑቲን በየቀኑ በአደባባይ እንደሚታዩ እና እንደማኛውም ጤነኛ ሰው የህመም ምልክት አያታይባቸውም ብለዋል።

➡️ #ሶማሊያ ፦ የሶማሊያ ባይዶዋ ከተማ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነች። ከተማዋ ፕሬዝዳንቱ ፈርማጆን አሸንፈው ዳግም የፕሬዜዳንትነት መንበሩን ከተረከቡ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጎበኟት ከተማ ትሆናለች።

#ቢቢሲ #ቲአርቲ #ሲጂቲኤን #SNTV

@tikvahethiopia
#Sidama #Hawassa

" የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ባለማግኘታችን ከሀገር ወጭ ያገኘነው የስራ እድል ሊያልፍብን ነው " - ወጣቶች

" ያለው አንድ ማሽን ብቻ በመሆኑ ችግሩን ባፋጣኝ መቅረፍ አልተቻለም " -  የሀዋሳ ከተማ ገቢዎች መምሪያ

በሀዋሳ ከተማ እና በአካባቢዉ ያሉ ስራ አጥ ወጣቶች ያገኙትን የውጭ ሀገር የስራ እድል ተከትሎ ማሟላት ካለባቸዉ መስፈርት ውስጥ አንዱ የሆነዉ የግብር መለያ ወይም ቲን ነምበር ለማግኘት ወደ ሀዋሳ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ቢያቀኑም ላለፉት ሰላሳ ቀናት ሊሳካላቸዉ አልቻለም።

እነዚህ ከሀዋሳና አካባቢዋ የተሰባሰቡ ወጣቶች ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት በተለያዬ መልኩ ያገኙትን የስራ እድል ለመጠቀም የጀመሩትን እንቅስቃሴ  የቲን ነምበር ጉዳይ እንቅፋት እንደሆነባቸዉና አሁን ላይ ጭራሹኑ " አናስተናግድም " የሚል ማስታወቂያ መውጣቱን ይናገራሉ።

ከዚህ በተጨማሪም ቢሮዉ " አናስተናግድም " የሚል ማስታወቂያ ካወጣ በኋላ በጎን አገልግሎት ሲሰጥ ይገኛል የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች በዚህ ምክኒያትም በከፍተኛ  ሁኔታ እየተጉላሉ መሆኑን ያነሳሉ።

ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ በሀዋሳ ከተማ ገቢዎች መምሪያ የግብር አወሳሰንና የደንበኞች አገልግሎት ሀላፊዋ ወይዘሮ ሙላት ዮሴፍ እንደገለፁት ፤ በከተማዉ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ስምንት የቲን ነምበር ማሽኖች ስራ ማቆማቸዉን በማንሳት አሁን ላይ በአንድ ማሽን ብቻ እየታገሉ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም " በከተማዉ አገልግሎት እየሰጠ ያለዉ አንድ ማሽን ብቻ በመሆኑ መፍትሄ መስጠት አልቻልንም " ያሉት ሀላፊዋ አገልግሎቱ እስከ ጥር ሰላሳ የታገደው ጫና በመፈጠሩና ወሩ የግብር መሰብሰቢያ ወቅት በመሆኑ ወጣቶችን ማስተናገድ ባለመቻሉ መሆኑን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፤ የክልሉ መንግስት እንደሀገር የተጀመረዉን የውጭ ሀገር ህጋዊ  የስራ ስምሪትና ኮታ ተከትሎ የተቀመጠውን የትምህርት ደረጃ እድሜና ፍላጎት የመሳሰሉ መስፈርቶች ያሟሉ ከ900 በላይ ወጣቶች ወደ ሳውዲና መሰል የአረብ ሀገራት መላኩን በመግለጽ  አሁን ላይ የቲን ነምበር ፍላጎት ያላቸዉ ወጣቶች እድሉን በመንግስት በኩል ያገኙ  ሳይሆን ይልቁንም በራሳቸዉ መንገድ ያገኙ መሆናቸዉን የክልሉ የስራ ክህሎት ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀገረጺዮን አበበ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ኃላፊዋ እንደሚሉት ወደ #ካናዳ እና ሌሎችም ሀገራት በራሳቸዉ ጥረት ለመሄድ ቲን ነምበር የሚያስፈልጋቸው ወጣቶችን ለመርዳት ጥረት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ መምሪያዉ ያለዉ አንድ ብቻ የቲን ነምበር ማሽን ግን ችግር መፍጠሩን አመልክተዋል።

ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ለመፍጠር ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር እየተወያዩ መሆኑን አስረድተዋል።

አሁን ላይ እስከ ጥር 30 አገልግሎት እንደማይኖር የሚገልጸዉን ማስታወቂያ የሰሙ ወጣቶች ጭንቀት ዉስጥ ሲሆኑ የሚመለከተዉ አካል አስፈላጊዉን መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ ጠይቀዋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ጥያቄ ብናቀርብም አስተያዬት ከመስጠት ተቆጥቧል።

መረጃውን የላከው የሀዋሳዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

" ተጠርጣሪው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል " - ፖሊስ

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ቪዛ እናስጨርሳለን ! " በሚል #ቲክቶክ በተሰኘው የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ሲያጭበረብር የነበረ ግለሰብ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለሚጓዙ ሰዎች ቪዛ እናስጨርሳለን ! " እያለ በቲክቶክ ሲያጭበረብር የነበረው ይኸው ግለሰብ ከ25 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦችን  በማጭበርበር ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር ከእያንዳንዳቸው መቀበሉ ተረጋግጧል።

በቲክቶክ ሀሰተኛ የግለሰቡ ማስታወቂያ የተጭበረበሩት አብዛኞች ወደ #ካናዳ ለመጓዝ ፍላጎት አሳይተው ከተጠርጣሪው ጋር የተገናኙ ናቸው።

" ያለምንም ቅድመ ክፍያ የቪዛ ፕሮሰስ እጨርሳለሁ " ቢልም ተበዳዮችን የተለያየ ቦታ እየቀያየረ እያገኛቸው  ቪዛ እንዳለቀላቸው እየነገረ እና ሌሎች ምክንያቶችን እየሰጠ ከእያንዳንዳቸው ከ50 ሺህ እስከ 600 ሺህ ብር የሚደርስ ገንዘብ ተቀብሏል።

ተጠርጣሪው የማታለል ወንጀል እየፈፀመ መሆኑ የታወቀው " ቪዛ አልቆልሃል " ተብሎ 600 ሺህ ብር የከፈለ አንድ ግለሰብ ወደ ካናዳ ሀገር ለመሄድ አየር መንገድ በተገኘበት ወቅት #ቪዛው_ሃሰተኛ መሆኑ ከተነገረው በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ ነው፡፡

አሁን ላይ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በህግ አግባብ ቤቱ ሲበረበር ሀሰተኛ ሰነዶች እና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።

#AddisAbabaPoliceCommission

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በደቡብ ኮሪያ ፣ ሙዋን በደረሰው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት 181 ሰዎች 177 ሰዎች መሞታቸው መረጋገጡን " ሮይተርስ " ዘግቧል። የቀሩት ሁለት ሰዎች በህይወት ይገኛሉ የሚለው ተስፋ እየተሟጠጠ ነው ተብሏል። ንብረትነቱ የ " ጄጁ አየር መንገድ " በሆነው Boeing 737-800 የአውሮፕላን አደጋ በህይወት የተረፉት ሁለት ሰዎች ሲሆኑ እነሱም የበረራ ሰራተኞች ናቸው። የደረሰባቸው…
#ካናዳ

በካናዳ፣ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በእሳት መያያዙ ተሰምቷል።

73 መንገደኞችን እና የበረራ ሰራተኞችን የያዘው በፒኤኤል አየር መንገድ የሚሰራው የኤር ካናዳ በረራ ቁጥር 2259 አውሮፕላን በሚያስደነግጥ አኳኋን ሊቆም ችሏል።

በህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተነግሯል።

ከሴንት ጆንስ ተነስቶ ሀሊፋክስ ኤርፖርት ሲያርፍ የነበረው አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመው ነው የተነገረው።

አውሮፕላኑ ሲያርፍ ከማረፊያው መንገድ ወጥቶ በእሳት ተያይዟል።

ለሲቢሲ ኒውስ ቃላቸውን የሰጡ አንድ መንገደኛ ፥ " አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ወቅት አንዱ ጎማ በትክክል አልተዘረጋም ነበር ፤ በጣም የሚያስፈራ ድምጽም ነበር " ብለዋል።

አንዱ የአውሮፕላን ክፍል በእሳት መጋየቱን ነው የጠቆሙት።

የክስተቱ ምክንያቱ እየተመረመረ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia