TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Congratulations የዲላ ዩኒቨርስቲ በክረምት ወራት ያሰለጠናቸውን 2ሽህ 286 ተማሪዎች ዛሬ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ አስመረቀ። ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 504 ሴቶች ይገኙበታል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኦቶና ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በነርሲንግና በህክምና ዶክትሬት ድግሪ ያሰለጠናቸውን 63 ዕጩ ምሩቃንን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምረቃ ሥነስርዓቱ የተገኙት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ወንድሙ ወልዴ በህክምናው ዘርፍ በሰው ሃይል ልማት ላይ መስክ ዩኒቨርሲቲው አበረታች ሥራ እየሰራ መሆኑን አውስተዋል፡፡

የህክምና ሳይንስ ጥልቅ ዕውቀትን እና ሙያዊ ታማኝነትን የሚሻ በመሆኑ ምሩቃን ወደስራ ሲገቡ እያንዳንዱን የማህበረሰብ ክፍል በታማኝነት እና በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Via WSU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

የቅዱስ አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በተቀናጀ የክሊኒካልና ህብረተሰብ አቀፍ የአእምሮ ጤና በሁለተኛ ዲግሪ ያስመረቃቸውን 25 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ ሆስፒታሉ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ የዘንድሮው ለአስረኛ ግዜ ሲሆን፤ ከ25ቱ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል ሶስቱ ሴቶች ናቸው። ሆስፒታሉ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደር ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር በተቀናጀ የክሊኒካልና ህብረተሰብ አቀፍ ጤና ትምህርት ዘርፍ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ የቆየ ሲሆን፤ የዘንድሮዎቹን ጨምሮ የተመራቂዎችን ቁጥር ወደ 245 ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CONGRATULATIONS

በአሁን ሰዓት "ጎንደር ዩኒቨርስቲ" የህክምና ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ እያስመረቀ ይገኛል፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተማሪ ወላጆች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine
#congratulations

ጎንደር ዩንቨርሲቲ በዛሬው ዕለት 251 የህክምና ዶክተሮችን አስመርቋል። ተመራቂዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ!

(ፎቶ-ቴዎድሮስ-ቲክቫህ ቤተሰብ ጎንደር)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations

የኢትዮጵያ አየር መንገድ "አቪዬሽን አካዳሚ" በተለያዩ የትምህርት ዘርፎት ያሰለጠናቸውን 384 ተማሪዎች አስመርቋል። ከተመረቁት 384 ተማሪዎች ውስጥም 67 የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ 70 የአውሮፕላን ቴክኒሻኖች፣ 109 የበረራ አስተናጋጆች፣ 90 የሽያጭና 48 የምግብ ዝግጅት አገልግሎት ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል።

(FBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations - አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲው ለ 6ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 140 የሕክምና ዶክተሮች ትላንት ታኅሣሥ 11/2012 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡ ከእነዚህም መካከል 37ቱ ሴቶች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#CONGRATULATIONS

#MEKELLE #HARAMAYA

- በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የሐረር የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ያሰለጥናቸውን 239 የህክምና ዶክተሮች ዛሬ አስመርቋል፡፡ ኮሌጁ ለ7ኛ ዙር ያስመረቀ ሲሆን ከተመራቂዎቹ 56ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሃረሪ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋና ሌሎች የክልልና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተው ነበር።

- በመቐለ ዩንቨርስቲ የአይደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ11ኛ ጊዜ 390 የህክምና ዶክተሮችን አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል በጥርስ የህክምና ሙያ የተማሩ ይገኙበታል። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የፌዴራል የጤና ጥበቃ እና የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

(EBC)
@tikvahethmagazine
#Congratulations

በዛሬው ዕለት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 221 የህክምና ዶክተሮችና ስፔሻሊስቶችን አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 192 የህክምና ዶክተሮች ሲሆኑ 29 ስፔሻሊስት ዶክተሮች ናቸው። ከዛሬዎቹ 221 ተመራቂዎች ውስጥ 22 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውንም ተጠቁሟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Congratulations

የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በአጠቃላይ እና የጥርስ ሕክምና ያሰለጠናቸውን 301 ባለሙያዎች አስመረቀ። ከተመራቂዎቹ መካከል 292ቱ በአጠቃላይ ሕክምና፣ 9ኙ ደግሞ በጥርስ ሕክምና ሙያ የሰለጠኑ ናቸው። ከተመራቂዎቹ መካከል 30 በመቶው ሴቶች ሲሆኑ 170 የሚደርሱት ደግሞ የላቀ ውጤት አስመዝግበዋል።

PHOTO : Tikvah Family
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TikvahFamilyMekelle

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በስልክ ያገኘናቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የሆኑ የቲክቫህ አባላት ከብዙ ውጣ ውረድ በኃላ ለዚህ ቀን በመብቃታቸው ደስ እንደተሰኙ ገልፀውልናል።

እጅግ በጣም ፈታኝ እና አስቸጋሪ በነበሩ ወቅቶች የመቐለ ነዋሪዎች አብሯቸው ስለነበሩ ፣ አይዞአችሁ እኛ አለንላችሁ ስላሏቸው ፣ ለእራሳቸው እየተቸገሩ ከሚበሉት ላይ ቀንሰው ስላካፈሏቸው ፣ ከሚጠጡት ቀንሰው ስላጠጧቸው፣ ፍቅር ስላስተናገዷቸው ፣ እንደልጆቹ ስለተንከባከባቸው ምስጋና እንድናደርስላቸው ጠይቀውናል።

እኛም ምንም እንኳን የመቐለ ነዋሪዎች በኢንተርኔት መቋረጥ ይህንን መልዕክት ባያዩትም ምስጋናውን አድርሰናል።

#Congratulations

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia