TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል‼️

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ #ጭማሪ ማድረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አለም ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ጭማሪን ግምት ውስጥ በማስገባት፥ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህ መሰረት ቤንዚን በሊትር 19 ብር ከ69 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 17 ብር ከ78 ሳንቲም፣ ነጭ ጋዝ በሊትር 17 ብር 78 ሳንቲም፤ ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 15 ብር ከ41 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 14 ብር ከ90 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ
በሊትር 27 ብር ከ08 ሳንቲም ሆኗል።

የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋው ከዛሬ ህዳር 4 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ማደያዎች ተግባራዊ እንደሚሆንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወዴት ወዴት ነው ነገሩ

ከሰሞኑ በሁሉም መሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ተስተውሏል፡፡ በተለይ ደግሞ ብዙ ዳቦ ቤቶች በዱቄት እጥረት በሚል ምክንያት ተዘግተዋል፡፡ አገልግሎት የሚሰጡትም በእያንዳንዱ ዳቦ ላይ በፊት ከነበረው ዋጋ የአንዳንድ ብር ጭማሪ አድርገዋል፡፡ የሸቀጦች እና የፍራፍሬ ዋጋም በተመሳሳይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ #ጭማሪ ከቀን ወደ ቀን እያሳየ መሆኑን ሸማቾችና ቅኝት በተደረገባቸው የንግድ ቦታዎች ማረጋገጥ ተችሏል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ያልተገባ #ጭማሪ ተደርጎብናል" የዩኒቲ ተማሪዎች

የዩኒቲ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለ2012 የትምህርት ዘመን ተቋሙ ያልተገባና ከፍተኛ ጭማሪ አድርጎብናል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። በጉዳዩ ላይ ዩኒቨርስቲ ማብራሪያ አልሰጠንም ሲሉም ወቅሰዋል።

•TIKVAH-ETH ተማሪዎች እያነሱት ባለው ቅሬታ ላይ ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው ምላሽ ካለ ተከታትሎ ያሰደርሳል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋና ጤና ባለሞያዎች ለ3 ወር ከታክስ ነፃ ሆኑ!

የጋና ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሕሙማንን የሚንከባከቡ እንዲሁም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጦርነቱን ከፊት መስመር ሆነው ለሚመሩት የጤና ባለሙያዎች ወርሃዊ ደሞዛቸው ላይ #ጭማሪ እንደሚኖር ግልፀዋል። በተጨማሪ በጋና ውስጥ ያሉ ሁሉም ጤና ሰራተኞች ለሶስት (3) ወራት ከታክስ ነጻ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮድ 2 የቤት ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ክልከላ ተነስቷል!

ከኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ መግለጫ የተወሰደ ፦

... በአጠቃላይ በኮድ ሁለት (2) የቤት ተሸከርካሪዎች ተጥሎ የነበረዉ ክልከላ ተነሰቶ #አጠቃላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ለመገደብ የሚያስችል አማራጭ ክልከላ እንድተገበር የሚኒስትሮች ኮሚቴ ወስኗል፡፡

የእንቅስቃሴ ገደብ መቀነሻ አሰራሮች አንዱ የሆነዉ በሀገር አቋራጭ ተሸከሪካሪዎች የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ነው፡፡

የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ለመገደብ አሰተዋጽኦ እንደሚያደረግ በትራንስፖርት ሚኒስቴር የተደረገው ጥናት ያመላክታል፡፡

አገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች መደበኛ የወንበር አቅማቸዉ ከ45 (አርባ አምስት) ሰዉ በላይ የሆነ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ #ጭማሪ ከመደበኛ ዋጋዉ 75% እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን መደበኛ የወንበር ቁጥራቸዉ እስከ (45) አርባ አምስት ሰዉ የሆኑ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች የሚያስከፍሉት የታሪፍ ጭማሪ ደግሞ 100% መሆኑ ተወሰኗል፡፡

https://telegra.ph/COVID19Ethiopia-05-27

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ሐጅ

" በዘንድሮ አመት ሐጅ ለማድረግ ዕቅድ ያላችሁ ቀድማችሁ የጉዞ ሰነዳችሁን (ፓስፖርታችሁን) ከወዲሁ ዝግጁ አድርጉ " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

የ2015/1444 አሂ የሃጅ መስተንግዶ በተሻለ መልኩ ለመስጠት ከክልልና ከተማ አስተዳደር የመጂሊስ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳውቋል።

የ2015/1444 የተከበሩ የአሏህ እንግዶች (ሁጃጆች) መስተንግዶ ቀልጣፋ ለማድረግ የተለያዪ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት የዘንድሮ የሐጅ መስተንግዶ ዘመኑን በዋጀ በአይ ሲቲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚከናወን መሆኑ ተፈልጿል።

የሁጃጆችን አንግልት ለመቀነስ መስተንግዶው በየክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤቶች አማካኝነት ይከናወናል የተባለ ሲሆን የክልል መጅሊሶች ስራቸውን ለማሳለጥ ተጨማሪ ቅርንጫፎችን እንደሚከፍቱ ተገልጿል።

ሰፊ ቁጥር የአሏህ እንግዶች (ሁጃጆች) ተመዝጋቢ የሌላቸው ክልሎች  ወደ አጎራባች ክልል እስልምና ጉዳዮች በመሄድ መስተንግዶ እንዲያገኙ አሰራሮች መዘርጋታቸውን በውይይቱ ወቅት ተመላክቷታ።

ለዘንድሮ  የሐጅ ተጓዦች ጉዞ ከማድረገቸው በፊት በሐጅ ስርዓት (መናሲከል ሐጅ) ዙሪያ በዑለሞች ስልጠና ይሰጣቸዋልም ተብሏል።

በዘንድሮ አመት ሐጅ ለማድረግ ዕቅድ ያላቸው ቀድመው የጉዞ ሰነዳቸውን (ፓስፖርታቸውን) ከወዲሁ ዝግጁ እንዲያደረጉ ጥሪ ቀርቧል።

የዘንድሮ የሐጅ ጉዞ መስተንግዶ ክፍያ ከውጪ የገንዘቦች ምንዛሪ አኳያ የተወሰነ #ጭማሪ እንደሚኖረው የታወቀ ሲሆን ከቀናት በኃላ ይፋ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኢትዮ ቴሌኮም 630 ሺ ደንበኞቹ ዛሬ ይፋ ያደረገውን የ5G ኔትወርኩን መጠቀም ይችላሉ ብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ እንዲሁም በአዳማ ከተሞ በሙከራ ደረጃ ሲያቀርብ ቆይቶ ዛሬ በይፋ በአዲስ አበባ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል። ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከው በአዲስ አበባ…
የ5G ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት ዋጋ ስንት ነው ?

ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ 81.8 ሚሊዮን ከኔትዎርክ የተገናኙ መሳሪያዎች መኖራቸውን ያሳወቀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 42 በመቶ የሚሆነው ስማርት ስልኮች (Smart Phones) መሆናቸውን ገልጿል።

በተጠቃሚዎች ቁጥር ደግሞ 34.4 ሚሊዮን ሰዎች የኢንተርኔት ዳታ ተጠቃሚ ናቸው ያለው ተቋሙ፥ እነዚህ ደንበኞቹ በአማካይ በቀን 2,087 GB ዳታ ዝውውር (Average Daily data traffic) የሚፈጽሙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የ4G ተጠቃሚዎቹ 66 በመቶ የሚሆነውን እንደሚሸፍኑ አስታውቋል።

አዲሱ የኢትዮ ቴሌኮም የ5G ኔትዎርክ በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰነ ክልል ለተጠቃሚዎች የቀረበ ሲሆን የራሱ የክፍያ ፖኬጆችም ተዘጋጅተውለታል።

ይህ የክፍያ ፖኬጅ ከዚህ በፊት ከነበሩት የኔትወርክ አገልግሎቶች (4G, 3G, 2G) የዋጋ #ጭማሪ ያለው ነው።

በዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ወርኃዊ ያልተገደበ የ5G አገልግሎቱን በ1,199 ብር እና በ300 GB ፍትሃዊ የአጠቃቀም ፖሊሲ ባለው (FUP) እንዲሁም ፕሪሚየም የተሰኘውን ወርኃዊ ያልተገደበ ጥቅሉን በ1,299 ብር በ400 GB ፍትሃዊ የአጠቃቀም ፖሊሲ ባለው (FUP) ለተጠቃሚዎች አድርሷል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮ ቴሌኮም ያልተገደበ 150 GB የ5G ኢንተርኔት በ929 ብር እንዲሁም 250 GB ደግሞ 979 በር ለተጠቃሚዎች አቅርቧል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም በነበረው ኔትዎርክ ወርኃዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት በ999 ብር ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ይታወሳል።

የ5G ኔትዎርክ አገልግሎት ለመጠቀም ምን ላድርግ ?

ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ 5G ኔትዎርክ መቀበል የሚችሉ መሳሪያዎችን የያዙ ደንበኞችን ልየታ አጠናቆ ወደ ኔቶርኩ እያስገባ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ይህ ሥራ እንደሚጠናቀቅም አሳውቋል።

በመሆኑም ደንበኞች ወደ ኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት ሳይሄዱ አገልግሎቱን መጠቀም የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጹሑፍ መልዕክት የሚደርሳቸው ይሆናል ተብሏል።

ደንበኞች በራሳቸው ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም መጀመሪያ የያዙት ስልክ ወይም ኢንተርኔት ማስጠቀም የሚችል ቁስ (Device) የ5G ኔትዎርክ መቀበል እንደሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ።

NB : የፍትሃዊ አጠቃቀም ፖሊሲ (FUP) ማለት ኢንተርኔት አቅራቢዎች ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አላግባብ የመጠቀምን ወይም የመተላለፊያ ይዘትን (Bandwidth) ከመጠን በላይ መጠቀምን ለመከላከል የሚያስችላቸውና ፍጥነትን የሚቀንሱበት አሰራር ነው። ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን ፖሊሲ ከዚህ ቀደም የሰዓት እና የቀን ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ላይ ተግባራዊ አድርጓል።

ፎቶ 1 ፦ ለተጠቃሚዎች የቀረበውን የዳታ ጥቅል የሚያሳይ

ፎቶ 2፦ የ5G አገልግሎት የተዘረጋባቸው አከባቢዎች የሚያሳይ

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#NBE

ብሔራዊ ባንክ " ሪፖርተር ጋዜጣ " ላይ ወጥቷል ባለው አሳሳች ዘገባና አሉባልታ ምክንያት በዋጋ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም ሰው ሠራሽ #ጭማሪ ተቀባይነት የለውም፤ ጥብቅ ክትትልም ይደረጋል ብሏል።

ብሔራዊ ባንክ ምን አለ ?

-  በጋዜጣዊ በህዳር 23/2016 እትም ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማ የፕላን፤ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ከአንድ የፓርላማ አባል ቀረበ ከተባለ አስተያየት ላይ ተነሥቶ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ተመን ላይ በቅርብ ጊዜና በከፍተኛ ደረጃ ለውጥ ለማድረግ ማቀዱን በማስመልከት የወጣው ዘገባ ፈጽሞ ሐሰተኛና አሳሳች፣ ከጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ያፈነገጠ ድርጊት ነው ብሏል።

- " ለፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዮን በተመለከተ የቀረበ ዕቅድ የለም " ሲል ገልጿል።

- እስከ 4 ስዓት በፈጀው ውይይት ወቅት በብሔራዊ ባንክ የተነገረ ነገር እንደሌለ ህብራተሰቡ መረዳት አለበት ብሏል።

- በዚህ አሳሳች ዘገባና አሉባልታ ምክንያት በዋጋ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም ሰው ሠራሽ ጭማሪ ተቀባይነት የለውም ጥብቅ ክትትልም ይደረጋል ብሏል።

በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣው ዘገባ ምን ይላል ?

- ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊውና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን ሰፊ የውጭ ምንዛሪ ተመን ልዩነት #በ95_በመቶ ለማጥበብ ዕቅድ መያዙ መታወቁ ፤ ይህ ዕቅድ ግን መቼና እንዴት እንደሚፈጸም የታወቀ ነገር እንደሌለ ያስረዳል።

- ይህ ባንኩ ዕቅድ የተሰማውም ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ/ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የብሔራዊ ባንክን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድና የመጀመርያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው ብሏል።

- ብሔራዊ ባንክ ይህንን ዕቅዱን በቋሚ ኮሚቴው የግምገማ መድረክ ላይ #በይፋ_ባያቀርብም፣ ለቋሚ ኮሚቴው የቀረበን #ሰነድ የተመለከቱ አንድ የም/ ቤት አባል፤ ዕቅዱን ከሪፖርቱ ላይ እንደተመለከቱ ጠቅሰው ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የም/ቤቱ አባሉ ምን አሉ ?

" ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊው የውጭ ምንዛሪ ተመንና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን ልዩነት በ95 በመቶ የማቀራረብ ዕቅድ ይዟል።

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በሕጋዊው የምንዛሪ ተመንና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው ልዩነት እጥፍ ነው።

ስለዚህ ልዩነቱን በ95% ለማጥበብ የተያዘው ዕቅድ በተጨባጭ የሚቻል ነው ወይ ? ወይስ ዲቫሉዌሽን ለማድረግ (የብርን የመግዛት አቅም ለማዳከም) አስባችኋል? " ሲሉ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

- የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ፤ "እንደየ ሁኔታው እየተመዘኑ የሚወሰዱ ዕርምጃዎች ይኖራሉ እንጂ በዚህ ወቅት ይህ ዕርምጃ ይወሰዳል ብሎ ብሔራዊ ባንክ ሊናገር አይችልም "  የሚል ምላሽ መስጠታቸው በጋዜጣው ላይ ሰፍሯል።

- አቶ ማሞ " የውጭ ምንዛሪ ጉዳይን በተመለከተ ሁሉን ነገር እዚህ መናገር አልችልም። ብሔራዊ ባንክን በሚመለከቱ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ የምናደርገው ውይይት ተገቢ ላልሆነ ስፔኩሌሽን (ግምት) የሚያጋልጥ መሆን የለበትም። ገና ጥናት ያልተደረገበት ጉዳይ ላይ ብንወያይም ትርጉም የለውም። ዋናው ቁልፍ ነገር ዓላማችን ላይ መወያየት ሊሆን ይገባል። የባንኩ ዋና ዓላማ የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታና የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት እንዲኖር ማስቻል ነው " ማለታቸውንም ጋዜጣው አስፍሯል።

ብሔራዊ ባንክ ይህን ዘገባ ነው #አሳሳችና #አሉባልታ ነው ያለው።

$ በአሁኑ ወቅት የዶላር ሕጋዊው የውጭ ምንዛሪ ተመን 55.5 ብር የደረሰ ሲሆን፣ በጥቁር ገበያው ግን አንድ ዶላር እስከ 110 ብር እየተመነዘረ ይገኛል።

@tikvahethiopia
#ጭማሪ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

አሁን አገልግሎት እየተሰጠበት ያለው 10 ብር ሲሆን ወደ 20 ብር ጭማሪ እንደተደረገ ታውቋል።

የታሪፍ ጭማሪው ከታኅሣስ 1/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
 
@tikvahethiopia