TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrAbiyAhmed

የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ ከሰዓቱን በጠሩት የጂ-20 ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ የተሰኘ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበይነ መረብ በመታገዝ ተሳትፈዋል።

“ለንግድ እና ለኢንቨስትመንት ማሕቀፋዊ ሁኔታዎች” በሚል ርዕስ የሚካሄደው ጉባዔ የስምምነቱ ፈራሚ የሆኑ ሀገራት ተጨማሪ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲያገኙ በሚያስችል ሁኔታ ማሕቀፋዊ ሁኔታዎችን ወደ ቀጣይ ርምጃዎች ለመውሰድ የታለመ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፣ ለሙዐለ ነዋይ ፍሰት ምቹ ነባራዊ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል በኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አማካኝነት ማክሮ ኢኮኖሚያ፣ መዋቅር እና የዘርፍ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ገልጸዋል።

#PMofficeEthiopia

@tikvahethiopia
#Senegal

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ሴኔጋል፤ ዳካር ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሴኔጋል ቆይታቸው ከሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ጋር የሁለትዮሽ ጉዳዮችና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

#PMofficeEthiopia

@tikvahethiopia
ሹመት !

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡-

1. አቶ አደም ፋራህ - በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ

2. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ - በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ

3. ዶ/ር ስለሺ በቀለ - በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ

4. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ

በተጨማሪም ፦
- ዶ/ር ምህረት ደበበ - የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፤

- አቶ ፍሰሃ ይታገሱ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤

- እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡

#PMOfficeEthiopia

@tikvahethiopia
#Update

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የፊልድ ማርሻል ወታደራዊ ማዕረግ ለጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተሰጠ።

በተጨማሪ ፦

• 4 ሌትናል ጀነራሎች ወደ ሙሉ ጀነራልነት፣
• 14 ሜጀር ጀነራሎች ወደ ሌትናል ጀነራልነት፣
• 24 ብርጋዴር ጀነራሎች ወደ ሜጀር ጀነራልነት፣
• 58 ኮሎኔሎች ወደ ብርጋዴር ጀነራልነት በአጠቃላይ 100 ከፍተኛ የጦር አመራሮች እድገት ተሰጥቷል።

ሹመቱ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አህመድ አቅራቢነት በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኩል ነው የተሰጠው።

የማዕረግ እድገት ያገኙ ከፍተኛ መኮንኖች ሙሉ ዝርዝር : https://telegra.ph/Tikvah-01-08

#PMOfficeEthiopia

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA🇪🇹 #UAE🇦🇪

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) አየር ኃይል አባላት በጋራ ሆነው " ጥቁር አንበሳ " የተሰኘ የአየር ላይ ወታደራዊ ትርዒት አቀረቡ።

ትርዒቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደ ስነስርዓት ላይ ነው።

በስነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይሎች በጋራ የቀረበው ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት በትብብር ከሠራን የምንደርስበትን ደረጃ ያሳየ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው የአየር ትርዒቱ ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢማራት በፖለቲካው እና በውትድርናው መስክ ያላቸውን መልካም ግንኙነት፣ ወዳጅነትና ትብብር ያሳየ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከተመሰረተ 88ኛ አመቱን የያዘ ሲሆን ካለፈው ህዳር 20 ጀምሮ የምስረታ በዓሉ እየተከበረ ነው።

Photo Credit - #PMOfficeEthiopia

@tikvahethiopia