TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ... ከጌታቸው ጨምሮ ከራሳቸው ከTPLF ሰዎች አጣርቻለሁ ያ የተነገረው የድሮን ጥቃት የሚባለው ውሸት ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የተፈፀመ " የድሮን ጥቃት " የለም ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።

ይህን የተናገሩት " የኢትዮጵያ ሚዲያ ሰርቪስ (ኢ ኤም ኤስ) " ለተባለና በኢንተርኔት ላይ ለሚሰራጭ ሚዲያ ነው።

" በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ አንዳንድ ክስተቶች ተፈጠሩ ሲባል መረጃ እንለዋወጣለን። ስምምነት ተፈራርመናል ስለዚህ የስልክ ችግር የለብንም። " ያሉት አምባሳደር ሬድዋን በኬንያ ናይሮቢ ፤ ከእነ አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከወታደራዊ አዛዦቹም ጋር መነጋገራቸውን እና የድሮን ጥቃት ተፈፀመ የተባለው ውሸት መሆኑን  ገልፀዋል።

" #ስምምነት_ከመፈረሙ_በፊት የነበረ (incident) ክስተትን ከስምምነት በኃላም ለማምጣት የሚሞክሩ አሉ። በዚህ ግጭት ውስጥ ገንዘብ ይከፈላቸው የነበሩ ጥሩ ሃብት ያፈሩበት ሰዎች አሁንም ግጭት እንዲቀጥል የማቀጣጠል ፍላጎት ያላቸው እንዳሉ እናያለን ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ፤ ከውስጥም በተለያየ መንገድ ስሜታዊ የሆነ ሰው ሊያራግበው ይችላል የትግራይ ሚዲያም ፤ የወያኔ ቴሌቪዥንም ሰርተውት ነበር" ብለዋል።

" በእኛ በኩል #ንግግሮችን ለማስተካከል ሞክረናል " ያሉት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን " አሁን ሰው ተስፋ እንዳያድርበት ወደፊትም ይሄን ነገር እንዲያመጣ ነው እንጂ ቁርሾውን በ 'Transitional Justice' በሂደት ይሄዳል ፣ በምህረት የሚታለፈው ይታለፋል መፀፀቱ ከታየ እውነት ከተናገረ ፤ የግድ በፍርድ ቤት ማለቅ ያለበት ከባድ ወንጀል የሆነ ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳል፣ ተጠያቂነትንም የማህበራዊ ህክምናንም ትስስርንም እኩል የሚያማክል መንገድ አለን እሱ ይደረሳል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ያልነበረ ነገር እያጋጋሉ የውሸት ሚፅፉ አሉ ከራሳቸው ከTPLF ሰዎች አጣርቻለሁ ጌታቸውን ጨምሮ ያ የወጣው መግለጫ (የGSTS መግለጫ ማለታቸው ነው) የጋራቸው አቋም እንዳልሆነ፣  የተባለው የድሮን ጥቃትም ውሸት እንደሆነ አጣርቻለሁ " ብለዋል።

በስናይፐር ፣ በድሽቃ አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ ሊያጋጥም እንደሚችል የጠቆሙት አምባሳደሩ " ይሄ የተለመደ ነው፤ የሰላም ፊርማ ሲፈረም የተወሰኑ ቀናት እየሞተ እስከሚሄድ ድረስ የሰማም በስሜት ተውጦ እምቢ ብሎ ሊያደርገው ይችላል፣ ሳይሰማ የሚቀርም ያደርገዋል፤ ነገር ፈልጎ ነገሩ እንዲበላሽ  የሚፈልግም ሊያደርገው ይችላል በታንክ እና በመድፍ እንድካልሆነ ድረስ በድሽቃ እና በስናይፐሮች የሚደረግ አንዳንድ የተኩስ ምልልሶች እዚህም እዚያም ያጋጥማሉ " ሲሉ አስረድተዋል።

" ሰው ይሄንን (አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚያጋጥሙትን የተኩስ ልውውጦችን ማለታቸው ነው) ለመዘገብ የሚቸኩለውን ያህል ከTPLF ካምፕ ወደኛ ወታደር መጥቶ አብሮ በልቶ ፣ ... ፣ ተጫውቶ ፣ ፎቶ ተነስቶ የሚመለሰውን ለመዘገብ ፍላጎት የላቸውም እኛ ነን መግፋት ያለብን የሚል ነገር በሁለቱም በኩል አለ ካማንደሮቹ ይሄን ጉዳይ መልክ ካስያዙት በኃላ ሁሉ። የራሳቸውን Discipline ያሲዛሉ " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia