TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የፀጥታ_ችግር

ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ አሶሳ ከተማ 96 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ማና ሲቡ ፤ መንዲ ከተማ (ምዕራብ ወለጋ) እና አካባቢው ላይ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።

አንድ በአካባቢው ላይ ቤተሰቦቹ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል፤ ከትላንት ወዲያ ሰኞ  ታጣቂዎች ከማለዳ ጀምሮ ቶክስ በመክፈት ወደመንዲ ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት በመንግስት መ/ቤቶችና ተቋማት ላይ ጥፋት ሲያደርሱ እንደነበር አመልክቷል።

ባንኮችም ተዘርፈዋል።

በከተማው የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ እንደሆኑና ከአሶሳ-መንዲ የህዝብ ትራንስፖርት ሙሉ ለሙሉ እንደተቋረጠ በክስተቱ ንፁሃን ሰዎች እየተገደሉ ገልጿል።

መንዲ እና አካባቢው ከባድ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት ያለው የኸው የቤተሰባችን አባል "ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዛት ያላቸው የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ወደ ከተማ ዘልቀው ገብተው ጥፋት ያደረሱት" ሲል አስረድቷል።

ከአሶሳ ጋር የሚያገናኘውን ዋናውን አስፓልት በመቆረጡ ነዋሪው ትልቅ ስጋት ላይ እንደሆነ ገልጾ " የንፁሃን ደም ከመፍሰሱ በፊት መንግስት ፈጣን መፍትሄ እንዲሰጥ  እንፈልጋለን " ብሏል።

"  ብዙ ዘመዶቼ እዛ ስላሉ እኔም ጨንቀት ላይ ነኝ " ሲል ሀሳቡን አጋርቷል።

የምዕራብ ወለጋ ዞን የአስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደበላ ኦላና ደግሞ " ከሰኞ ጀምሮ እስከ ትላንት ማክሰኞ ድረስ የፀጥታ ኃይሉ እና ታጣቂዎች እየተዋጉ ነው " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

አቶ ደበላ በአካባቢው ከሰኞ ጀምሮ ተኩስ እንደነበርና #ከተማው ውስጥም ተኩስ እንደነበር አመልክተዋል።

ታጣቂዎቹ ወደ ከተማ ዘልቀው ሳይገቡ እንዳልቀረ ጥርጣሬ እንዳላቸውም ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

@tikvahethiopia