TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት...

ባሳለፍነው ሳምንት የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የ11.3 ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ ተመሠረተባቸው ተብሎ የተሰራጨው ዜና #የተሳሳተ መረጃ ነው ሲል የናፍያድ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ገለፀ፡፡

እንደ ተቋሙ ገለፃ የተቋሙ ባለቤት #ናፍያድ_ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሚል ድርጅት ስም በከፈቱት አካውንት ከሳሽ ለተባሉት አቶ አንተነህ ዘለቀ ምንም አይነት ቼክ እንዳልሰጡ እና ከግለሰቡ ጋርም በስራ ዘርፍም ሆነ በሌላ ጉዳይ የማይገናኙ እንደሆኑ ጠቅሶ ተሰጠ የተባለው ቁጥሩ ኤ 4178436 የሆነ ቼክ መሰረቁን ቀደም ተብሎ ለፖሊስ ሪፖርት እንዳደረገ ገልጾአል።

በጉዳዩ ላይ ክስ ተመስርቶ እየታየ እንደነበር የገለፀው የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለዚህም ድርጅቱ ከሚገኝበት ከኦሮምያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፖሊስ የደረሰበትን ውጤት የሚያሳይ ለተቋሙ የተፃፈን ደብዳቤን አቅርቧል፡፡

ፖሊስ ቁጥሩ ኤ 4178436 የሆነ ቼክ ከወጋገን ባንክ አዳማ ቅርንጫፍ ስለመሰረቁ በተመለከተ እየተደረገ ስላለው የወንጀል ምርመራ በሚመለከት የፃፈው ደብዳቤ ጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ይጠቁማል፡፡

"በዚህ ጉዳይ ከሳሽ ነኝ ያሉት አቶ አንተነህ ዘለቀ የተባሉት ግለሰብ በጠፋው ቼክ ጉዳይ ተጠርጥረው በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በኦሮምያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ እና በዋስ መብት የተለቀቀቁ" ናቸው ያለው የህዝብ ግኝኑነት ክፍሉ “ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኃል እንዲሉ በተገላቢጦሽ ግለሰቡ ከሳሽ ሆኖ መቅረባቸው አስገራሚ ሆኖብናል” ያለ ሲሆን ጉዳዩ በህግ የተያዘ መሆኑን አስታውሶ "ክሱ ሆን ተብሎ የድርጅቱን ባለቤት እና የተቋሙን መልካም ስም ለማጉደፍ የተቀናባበረ" መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

Via ሸገር ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia