TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Turkey

ቱርክ ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 7 ቶን መጠን ያለው የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ሳምንት ከቱርኩ ፕሬዘዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶሃን ጋር በስልክ መወያየታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በውይይታቸው ወቅት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ቱርክ ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀው ፕሬዘዳንቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው ተገልጾ ነበር።

በዚህም መሰረት ቱርክ 1 ነጥብ 7 ቶን መጠን ያላቸው የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጋለች።

ድጋፉን በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ለሴቶች ፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳዮች ሚኒስትር ፊልሳን አብዱላሂ ዛሬ በአዲስ አበባ አስረክበዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቱርክ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደሀገር ተመለሱ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ፥ "ከተከበሩ የቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር የነበረንን ውድ ጊዜ አጠናቀን ወደ ሀገር ተመልሰናል።" ብለዋል። አክለውም ፥ "የቱርክ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን…
#Turkey #Ethiopia #Sudan

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶጋን በኢትዮ - ሱዳን ድንበር ጉዳን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለሸማገላችሁ ሲሉ ሀሳብ አቅርበዋል።

ኤርዶሃን ሃሳቡን ያቀረቡት፤ ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ትላንት በአንካራ በሰጡት መግለጫ ነው።

በትላትናው የዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን መግለጫ ወቅት የትግራይ እና የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳዮች ተነስተዋል።

ኤርዶጋን ሀገራቸው ቱርክ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሚወዛገቡበትን የድንበር ጉዳይ ለማደራደር ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።

ኤርዶጋን “ውዝግቡ በ2ቱ አገሮች መካከል በሚደረግ ውይይት በመልካም ጉርብትና ላይ በመመስረት እንዲፈታ የልብ ፍላጎቴ መሆኑን ገልጫለሁ ፤ ቱርክ ጉዳዩ በሰላም እልባት እንዲያገኝ ሽምግልናን ጨምሮ ማናቸውንም አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ ናት" ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኤርዶጋን በሰሜን ኢትዮጵያ ስለተፈጠረው ጦርነት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አላት ያሉትን ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ እና ጠቀሜታ ጠቅሰው ለሀገሪቱ ሰላም፣ ጸጥታ እና አንድነት ትኩረት እንደሚሰጡ ገልጸዋል። 

“የቀጠናውን ሰላም እና መረጋጋት ከመጠበቅ አኳያ ለወቅታዊው ችግር በለዘብተኛ አካሄድ መፍትሔ ማበጀት ያስፈልጋል ብለን እናምናለን” ብለዋል።

አክለውም 9 ወራት በላይ ያስቆጠረው ውጊያ ከተባባሰ ዳፋው በአካባቢው አገራት ሊዳረስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።  

#EthiopiaInsider #Anadolu

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቱርክ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደሀገር ተመለሱ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ፥ "ከተከበሩ የቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር የነበረንን ውድ ጊዜ አጠናቀን ወደ ሀገር ተመልሰናል።" ብለዋል። አክለውም ፥ "የቱርክ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን…
#Ethiopia #Turkey

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የልዑካን ቡድናቸው ወደ ቱርክ (አንካራ) አቅንተው የአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አድርገው ወደሀገር ቤት መመለሳቸው ይታወቃል።

ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን የቱርክ የስራ ጉብኝት የተጠቃለለ አጭር ሪፖርት አቅርቧል።

ይፋዊ ጉብኝቱ የኢትዮጵያ እና የቱርክ ሁለትዮሽ ግንኙነት 125ኛ ዓመት ላይ የተከናወነ ሲሆን 4 ስምምነቶችን በመፈራረም ነው የተጠናቀቀው።

4ቱ ስምምነቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. በውሀ ዘርፍ ትብብር ለማድረግ የጋራ መግባቢያ ሰነድ
2. የወታደራዊ ማህቀፍ ስምምነት
3. የፋይናንስ ድጋፍን የተመለከት የትግበራ ሰነድ
4. የወታደራዊ ፋይናንስ የትብብር ስምምነት

በጉብኝቱ መካከል ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በአኒትካቢር መካነ መቃብር የመታሰቢያ ጉንጉን አሰቀምጠው፣ “ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ያላት ትስስር በመከባበር እና በመተማመን የጋራ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ የበለፀገ ባህል እና ትውፊት ለሞላቸው ሁለት የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤቶች የሚመጥን ነው” በማለት ተናግረዋል።

በፕሬዚደንቱ ቤተመንግሥት ለጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ደማቅ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ሁለቱ መሪዎች ከልዑካን ቡድኖቻቸው ጋር በመሆን የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ላይ ሁለቱም ወገኖች ትብብሩን በቀጣይነት ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

@tikvagethiopia
#Sudan #Turkey

ጎረቤት ሀገር ሱዳን የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ላይ ውዝግብን ለመፍታት #ቱርክ ያቀረበችውን የማደራደር ጥያቄ መቀበሏ ታውቋል።

የቱርክን የማደራደር ጥያቄ ሱዳን መቀበሏን ያሳወቁት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማሪያም አል-ሳዲቅ አል-መሃዲ ናቸው።

ይህንንም ጉዳይ የቱርክ የዜና ወኪል የሆነው አናዱሉ እና የሱዳን መንግሥት የዜና ወኪል ሱና ዘግበውታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ፥ "የሱዳን የሉዓላዊ ም/ ቤት ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታህ አል-ቡርሐን ባለፈው ወር ወደ ቱርክ በተጓዙ ወቅት ፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረውን የድንበር አለመግባባት ለመፍታት ከቱርክ ባለሥልጣናት የቀረበውን የማደራደር ጥያቄ ተቀብለዋል" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በኩል በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤቱ ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታህ አል-ቡርሐን አብዱል ራህማን ሰኔ ወር ላይ ወደ ቱርክ መጓዛቸው ይታወሳል። አል-ቡርሐን በአንካራ ቆይታቸው ከፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋር ተገናኝተው በርካታ ምጣኔ ሀብታዊ ስምምነቶችን ተፈራርመው ነበር።

በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የኢትዮጵያው ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ቱርክ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ የተለያዩ የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ስምምነት ተፈራርመው እንደነበር ይታወሳል።

Credit : BBC/SUNA/ANADOLU

@tikvahethiopia
#Turkey : ቱርክ ተዋጊ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ እና ለሞሮኮ ለመሸጥ መስማማቷን 4 የመረጃ ምንጮች ገለፁልኝ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የቱርክ ባለልስጣን ለሮይተርስ በሰጡት ቃል፥ ኢትዮጵያ እና ምርኮ የመለዋወጫ አቅርቦትና ስልጠናን ባካተተ ስምምነት " ባይራክታር TB 2 " የተባሉ የጦር አውሮፕላኖችን ለመግዛት መጠየቃቸውን ተናግረዋል።

ስማንቸው እንዲገለፅ የልፈለጉ አንድ ዲፕሎማት ደግሞ ሞሮኮ ግንቦት ወር ላይ ያዘዘቻቸውን ተዋጊ አውሮፕላኖችን መረከቧን አሳውቀዋል።

ዲፕሎማቱ ፥ ኢትዮጵያም የሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከቱርክ ለመግዛት ጥያቄ አቅርባ ትእዛዙን ምን ደረጃ ላይ እንዳለ አይታወቅም ብለዋል።

ኢትዮጵያ፣ ሞሮኮ፣ ቱርክ ስለስምምነቱ ምንም ያሉት ነገር ባይኖርም ሮይተርስ ግን ስምምነቱን በደንብ ከሚያውቁ የመረጃ ምንጮች ዝርዝር መረጃ እንዳገኘ ዘግቧል።

2 የግብፅ የፀጥታ ምንጮች አሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ሽያጩን ለማስቆም ሀገራቸው መጠየቋን ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ሌላ ምንጭ ደግሞ የሽያጩ ስምምነት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማደስ ጥረት እያደረጉ ያሉት ግብፅና ቱርክ ውይይት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል።

ቱርክ ለኢትዮጵያና ሞሮኮ የምትሸጣቸው የመከላከያ እና የአቪዬሽን ቁሳቁሶች ባለፉት 2 ወራት መጨመሩን ይፋዊ መረጃዎች ቢያሳዩም ስለ ድሮን የቀረበ መረጃ የለም።

የቱርክ የወጪ ንግድ ምክር ቤት መረጃ እንደሚያሳየው እኤአ 2021 የመጀመሪያ 3 ወራት 51 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የመከላከያ እና አቪዬሽን ቁሳቁስ ሸመታለች።

ግብይቱ በነሃሴ እና መስከረም ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ሮይተርስ ገልጿል።

የዜና ወኪሉ፤ ከመከላከያና ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ጥረት እንዳደረገ ነገር ግን እንዳልተሳካለት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Turkey_Africa

የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በአፍሪካ ሀገራት 4 ቀናት ይፋዊ የስራ ገብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

በመጀመሪያው ቀን ጉብኝታቸው በአንጎላ፣ ላውንዳ ተገኝተው ከሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ጃኦ ሎሬንኮ ጋር መክረዋል።

በመቀጠል በበቶጎ ሎሜ ከፕሬዚዳንት ፋውሬ ናሲንግቤ ጋር ተገናኝተው መክረዋል፤ በተጨማሪ ከቡርኪና ፋሶ ፕሬዜዳንት ሮች ማርክ ክርስትያን ካቦሬ እንዲሁም ከላይቤሪያ ፕሬዝዳት ጆርጅ ዊሃ ጋር ተገናኝተው መክረዋል (ሁሉም ምክክሮች ለሚዲያ ዝግ ነበሩ) ።

ዛሬ በመጨረሻው የስራ ጉብኝት መርሃግብራቸው ፕሬዜዳንት ሬስፕ ጣይብ ኤርዶጋን ወደናይጄሪያ አቅንተው በአቡጃ በፕሬዜዳንት ሙሀመድ ቡሃሪ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፤ መሪዎቹ ምክክርም አድርገዋል።

ቱርክ እና ናይጄሪያ ከኃይል እስከ መከላከያ ድረስ በርካታ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፤ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከርም ስምምነት አድርገዋል።

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን እ.ኤ.አ በ2003 ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ቱርክ በአፍሪካ ውስጥ ያላትን ተሳትፎ እና ከሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገች ነው።

@tikvahethiopia
#Turkey : ቱርክ የአሜሪካንን ጨምሮ የ10 አገራት አምባሳደሮች አገሯን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የቱርክ ፕሬዘዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ባስተላለፉት ውሳኔ የአሜሪካንን ጨምሮ የ10 የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች አንካራን ለቀው እንዲወጡ ተወስኗል።

አምባሳደሮቹ እንዲባረሩ የተወሰነው በፈረንጆቹ 2016 ዓመት ከተካሄደው እና ከከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጀርባ እጁ አለበት በሚል ተጠርጥሮ ጉዳዩ በፍርድ ሂደት ላይ ያለ አንድ ግለሰብ ከእስር እንዲፈታ መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው።

ኦስማን ካቫላ የተሰኘው ይህ የመፈንቅለ መንግስት ተጠርጣሪ በፈረንጆቹ 2013 ዓመት በቱርክ ረብሻ እንዲከሰት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል እና በ2016ቱ የከሸፈው መፈንቅለ መንግስት እጁ አለበት በሚል በእስር ላይ ይገኛል።

ግለሰቡ ባሳለፍነው ሳምንት የፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበረው ሲሆን በአንካራ የሚገኙ የአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ፣ ሆላንድ፣ እና ኒውዝላንድ አምባሳደሮች የፕሬዘዳንት ረሲፕ ኤርዶሀን መንግስት ተከሳሹን በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ በጋራ ጠይቀዋል።

የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም አምባሳደሮቹን ጠርቶ ስለጉዳዩ እንዲያብራሩ የጠየቀ ሲሆን ድርጊቱ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው እና በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት መሆኑን ጠቅሶ ውድቅ አድርጎታል።

ፕሬዘዳንት ኤርዶሃን በአምባሳደሮቹ ድርጊት መበሳጨታቸውን ገልጸው በአስቸኳይ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ተናግረዋል።

የአሜሪካ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ በጉዳዩ እስካሁን ያሉት ነገር እንደሌለ ሮይተርስ በዘገባው አክሏል።

ምንጭ፦ አል ዓይን / ሮይተርስ
Photo Credit : AFP

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነሳ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሃገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቷል። ምክር ቤቱ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የወሰነው። ይህን ውሳኔ ተከትሎ÷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ስራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት…
#Turkey

" የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱ ሰላም እና መረጋጋት ለማምጣት ወሳኝ እርምጃ ነው " - ቱርክ

ቱርክ የኢትዮጵያ ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን በበጎ እንደምትቀበል ገልፃለች።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት ትክክለኛ እርምጃ ነው ስትልም ገልፃለች።

በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የሚደረጉ ሁሉንም ጥረቶች መደገፏን እንደምትቀጥል የገለፀችው ቱርክ ለስኬታማነቱም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እሰራለሁ ብላለች።

@tikvahethiopia
#UAE #Turkey #Kenya

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሁለት ቀናት ጉብኝት አድርገዋል።

ኤርዶጋን ጉብኝቱ ስኬታማ ነበር ብለዋል።

ሁለቱ ሀገራት አስራ ሶስት ስምምነቶችን የተፈራረሙ ሲሆን ስምምነቶቹ በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያዳብርና ኢንቨስትመንቶችን የሚያሳድግ እንዲሁም ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑ ተነግሯል።

በሌላ መረጃ የጎረቤት ሀገር #ኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ይገኛሉ። ፕሬዝዳንት ኬንያታ ከአቡዳቢ አልጋወራሽ እና ከዩኤኢ ምክትል ጦር አዛዥ ከሆኑት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይታቸው በአካባቢያዊ ፣ በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎች ዙሪያ እንደነበር አል አይን ኒውስ ዘግቧል።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ባለፈው ጥር ወር እንዲሁም አሁን ባለንበት የየካቲት ወር ውስጥ በአጠቃላይ የስድስት ሀገራት መሪዎችን ማለትም ፦
- የግብፅ ፕሬዜዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ
- የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
- የእስራኤል ፕሬዜዳንት አይዛክ ሄርዞግ
- የሶማሊያ ጠ/ሚር መሀመድ ሁሴን ሮበል
- የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን
- የኬንያ ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሀገሯ አስተናግዳ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክራለች።

@tikvahethiopia
#Turkey

" ...በኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት የሚያመጣ ማንኛውንም መንገድ እየደገፍን ነው " - ያፕራክ አልፕ

ቱርክ በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የሚያመጣ ማንኛውንም መንገድ እየደገፈች መሆኑን በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ገልፀዋል።

አምባሳደሯ ይህን የገለፁት በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ግጭት በቀጠለበት በዚህ ወቅት ነው።

ቱርክ በቅርቡ የተጀመረውን ብሔራዊ የውይይት ሂደት በደስታ እንደምትቀበል አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ተናግረዋል።

ሁለቱ ሀገራት [#ቱርክ እና #ኢትዮጵያ] በአስቸጋሪ ጊዜያት እርስበርስ መደጋገፋቸውን ያነሱት አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ፥ " በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የሚደረጉትን ሁሉንም እርምጃዎች በደስታ እንቀበላለን። አሁን ይህ እየሆነ በመምጣቱ ደስተኛ ነን ፤ ለሁሉም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ግጭቱ በቅርቡ እንደሚቆም ተስፋ እናደርጋለን " ብለዋል።

ቱርክ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ እና ወደ ንግግር እንዲገባ ለሁሉም ወገኖች ጥሪ ስታቀርብ እንደነበር የቱርክ መንግሥት ደጋፊ እንደሆነ የሚነገረው ዴይሊ ሳባህ ፅፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PMOEthiopia የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ (ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ) @tikvahethiopia
#Turkey #Ethiopia

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ አካሂዶት በነበረው 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ከቱርክ ሪፐብሊክ ጋር የተደረጉ ወታደራዊ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ውይይት አድርጓል።

ምክር ቤቱ ፤ ቱርክና ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ ጥብቅ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑን በማስታወስ ቱርክ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን አጋር መሆኗን በተደጋጋሚ ያረጋገጠች አገር ናት ብሏል።

በዚህ መነሻነት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቱርክ አንካራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቀት ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ/ም የተፈረሙ ሶስት ስምምነቶች ለምክር ቤቱ ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ገልጿል።

ከስምምነቶቹ አላማ ፦

👉 በትምህርትና ስለጠና፣
👉 የጋራ ወታደራዊ ልምምዶች፣
👉 በመከላከያ ኢንዱስትሪ ግንባታ፣
👉 የሳይበር ጥቃት መከላከል፣
👉 በሰላም ማስከበር፣
👉 የወታደራዊ ፋይናንስ ትብበብር፣
👉 በባህር ላይ ዉንብድና መከላከል ላይ በሚደረጉ ዘመቻዎች ለመተባበር የሚያስችል ማዕቀፍ መፍጠር ነው ብሏል።

ምክር ቤቱ በቀረቡት ሶስት የሁለትዮሽ ስምምምነቶች ላይ በመወያየት ይጸድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ መወሰኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia