TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Irreechaa2019

የኢሬቻ በዓል #በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ታዬ ግርማ ኮሚሽኑ በቅርቡ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል እና ከዚያ በፊት ለሚከበሩት ፌስቲቫሎች ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

#ኢሬቻ2012
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል!

"ጠቅላይ ሚንስትሩ(ዶ/ር አብይ አህመድ)እና ከሳቸው ጋር ያሉት አባላት በሰላም ወደ ሸገር ተመልሰዋል። የመከላከያ ሰራዊት እስከአሁን ላሰየው እርጋታ ክብር ይገባዋል። ህዝቡም በተቻለ መጠን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለመሪዎቹ ደስተኛ አለመሆኑን በመግለፅ ወደ ድንጋይ ውርወራ አለመግባቱ እና ያደረገውን በሙሉ #በሰላም መድረጉ ያስመሰግነዋል። በአጠቃላይ ነገሮች በሰላም እንዲሆኑ ያደረጉት በሙሉ ክብር ይገባቸዋል። ከዚህ በኃላም ሁሉም ነገር በሰላም እንዲጠናቀቅ አለመዘናጋት ጥሩ ነው።" ዶክተር ደረጄ ገረፋ ቱሉ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለውጭ ሀገር ሚዲያዎች የሰጡት መገለጫ ሲዳሰስ !

[በጋዜጠኛ ሰለሞን ሙጬ/DW]

የመግለጫው ዋነኛ ጉዳዮች የነበሩት፦

- የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር
- የሱዳን ወረራ እና ያልተገባ ጫና
- 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ

የታላቁ የህዳሴ ግድብን ግንባታ በተመለከተ ግብፅ በውሃ ላይ ምንም አበርክቶ ሳይኖራት እያሳደረች ያለው ጫና ተገቢነት እንደሌለው አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አሁንም ድርድሩን በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ማስቀጠል እንደምትቀጥል አሳውቀዋል።

አምባሳደር ዲና የሁለተኛው ዙር ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ግብፅና ሱዳን በሙሌቱ ላይ ስምምነት ካልደረሱ ምን ይሆናል ተብለው የተጠየቁ አምባሳደሩ ተከታዩን ምላሽ ነው የሰጡት፦

"በ3ቱ ሀገሮች በ2015 በሱዳን ካርቱም በተፈራረሙት የመርሆች መግለጫ መሰረት የግድቡ ሙሌት የግድቡ የስራ ሂደት አካል ነው። ስለዚህ የውሃ ሙሌቱ የግድቡ አካል ነው። ግድብ ከገነባህ ውሃ መሙላትህ እርግጥ ነው፤ ያ ነው ሊሆን የሚችለው ፤ በመጀመሪያው ዙር የግድቡ ሙሌት የሆነውም ይኸው ነው። አሁንም ተስፋ የምናደርገው በአሞላሉ እና በሂደቱ ላይ እንደምንስማማ ነው።"

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብን አስመልክቶ ሱዳን ከሰሞኑ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ላይ የባለቤትነት ጥያቄን ማንሳቷን አውግዘዋል።

በተለይ የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የውክልና ተልዕኮ አስፈፃሚነት ውስጥ መግባቱን አሳይቷል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ጉዳዩ አሁንም #በሰላም እንዲፈታ ግፊት ማድረጓን ቀጥላለች ብለዋል።

ምርጫ 2013 በተመለከተ አምባሳደር ዲና ፥ ከትላንት ጀምሮ የአውሮፓ ህብረት የባለሞያዎች ቡድን ለመላክ መስማማቱን አሳውቀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/MFA-Ethiopia-05-08

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ፦

- የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ መዘግየት ፣
- በድምፅ አሰጣጥ ላይ የሚታይ መደነጋገር፣
- ሰዓት አለማክበር፣
- የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል አለመጠበቅ፣
- ረጃጅም ሰልፎች (በፍጥነት አለመሄድ) ፣
- የሰልፍ ተራ አለመጠበቅ፣
- የምርጫ ቁሳቁስ መቀያየር
- ቀልጥፍ ያለ መስተንግዶ ክፍተት
- መራጮች ምርጫ ካርዳቸውን የወሰዱበትን መታወቂያ ሳይዙ መሄድ
- "እከሌን ምረጡ" የሚል ቅስቀሳ ለማድረግ መሞከር የመሳሰሉት ችግሮች ከመስተዋላቸው በዘለለ የምርጫ ሂደቱ #በሰላም እየተካሄድ መሆኑን ከአዲስ አበባና ከክልል የምርጫ ጣቢያዎች የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

የ Tikvah - Ethiopia አባላት በተመለከቷቸው የምርጫ ጣቢያዎች እድሜያቸው የገፋ ዜጎች ፣ እናቶች አባቶች ድምፅ ለመስጠት ተሰልፈው ተመልከተዋል። ነፍሠ ጡሮች፣ ልጅ የታቀፉ እናቶች ተሰልፈው ድምፅ ሲሰጡ አስተውለዋል።

በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ በፀጥታ እና በሰላም ረገድ ምንም ጥቆማ ከአባላቶቻችን አልተላከም፤ ሁሉም ሂደት #በተረጋጋ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ገልፀውልናል።

Photo Credit : Tikvah Family (Addis Ababa)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ህወሓትን እና ሸኔን የሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ነው። በሰልፉ ላይ የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነትንና የውጭ ሀገር መገነኛ ብዙሃንን አጥብቀው የሚተቹ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የተፃፉ የተለያዩ መፈክሮች በሰልፈኞች ተይዘዋል። ሰልፈኞች ካያዟቸው መፈክሮች መካከል ፦ - የአሜሪካ…
#Update

" ሰልፉ በሰላም ተጠናቋል " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

በመስቀል አደባባይና በዙሪያው የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ #በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማው ነዋሪ በተለይ ደግሞ የሰላማዊ ሰልፉ ታዳሚዎች ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር በማድረጋቸው ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።

በተጨማሪ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ላሉ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ሰልፉን ላስተባበሩ እና ለመሩ አካላት በሙሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት #በሰላማዊ_መንገድ ለመፍታት ሰላማዊ ድርድሮች እንዲጀመሩ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ አቅጣጫ አስቀመጠ። በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዉይይት በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በማእከላዊ ኮሚቴዉ መካሄዱን የፍትሕ ሚኒስትርና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ አስታወቁ። ዶ/ር…
#Peace

የተደራዳሪ ቡድኑ !

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት #በሰላም_ድርድር እንዲፈታ ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት በፌዴራል መንግሥት በኩል የሰላም ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙ ተረጋግጧል።

የቡድኑ አባላት ፦

1ኛ. አቶ ደመቀ መኮንን ➡️ ሰብሳቢ
2ኛ. ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ➡️ አባል
3ኛ. አቶ ተመስገን ጥሩነህ ➡️ አባል
4ኛ. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ➡️ አባል
5ኛ. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ➡️ አባል
6ኛ. ሌ/ል ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ ➡️ አባል
7ኛ. ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር ➡️ አባል መሆናቸውን የኢፕድ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ህወሓት ፤ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ባወጣው መግለጫ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ ዘግናኝ ግፍ እየፈፀሙ ነው ብሏል።

በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን #ሁሉን_አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ከሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት #ኃላፊነቱን_እንዲወጣ ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይና በህዝቡ ላይ እየፈጸመው ያለውን ግፍ እና በደል በአስቸኳይ እንዲያስቆም እንዲያደርግ ፤ ከትግራይ እንዲወጣ እንዲያስገድዱ ፤ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል #ተጠያቂ እንዲሆን እንዲያደርጉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" ህወሓት " በዛሬው መግለጫው ያነሳቸው ነጥቦች ምንድናቸው ?

- በተፈረመው #የሰላም_ስምምነት መሰረት ጦርነት እንዲቆም ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት እንዲከበር፣ የኤርትራና ሌሎችም ሃይሎች ከትግራይ እንዲወጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- ህወሓት ፤ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፤ በሰላም ስምምነቱ #እንዳልተደሰቱ ገልጾ ፤ " ወታደሮቹን ያስወጣል ተብሎ ቢጠበቅም ተጨማሪ ክፍሎችን (ኃይሎቹ) ወደ ትግራይ እያመጣ ነው " ብሏል። ይኸው ጦር በህዝባችን ላይ አሰቃቂ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል ሲል ገልጿል።

- የኤርትራ ጦር በሴቶቻችን ላይ ጾታን መሰረት ያደረገ እጅግ አረመኔያዊ ጥቃት እየፈፀመ ፤ ንፁሀን ዜጎችን እየጨፈጨፈ ፣ የህዝብና የግል ንብረት እየዘረፈ ወደ ኤርትራ እያጓጓዘ ፤ የተረፈውን ደግሞ #እያጠፋ እና እያቃጠለ ነው ፤ የትግራይ ቅርሶችም በከፍተኛ ደረጃ እየወደሙና እየተዘረፉ ነው ፤ በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ) የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል።

- ህወሓት የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ እና በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል #በአስቸኳይ_እንዲያስቆም ፤ ከትግራይ እንዲወጣም እንዲያስገድደው እንዲሁም በትግራይ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆን ማደረግ አለበት ብሏል።

- ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም አፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ፣ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በኢሳያስ አፈወርቂ " አምባገነን " ስርዓት ላይ ትክክለኛ ማዕቀብ እንዲጥልና ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን የህወሓት ክስ በተመለከተ ከ "ኤርትራ" በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ጦርነት እንዲያበቃ ፤ ያሉት ችግሮችም #በሰላም እንዲፈቱ ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ ያለገደብ ለተቸገሩት ዜጎች ሁሉ እንዲደርስ ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ እንዲጀምሩ ለማድረግ በደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ (የስምምነቱ ማስፈፀሚያ ላይ) ስምምነት መፈረማቸው አይዘነጋም።

በናይሮቢ ስምምነት በትግራይ ክልል ያሉ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት የውጭ ኃይሎችን እና ከኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ኃይሎችን ሁሉ ከክልሉ (ከትግራይ ክልል) ከማስወጣት ጋር #አብሮ እንደሚከናወን መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ መንገደኞችን ይዞ የበረረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን #በሰላም አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አርፏል። ዛሬ መቐለ ያረፈው የመንገደኞች አውሮፕላን ከ19 ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

Photo : Addis Ababa Bole Airport (ENA)

@tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ !

እንኳን ለጥምቀት ከተራ በዓል #በሰላም አደረሳችሁ።

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ #በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ።

መልካም የጥምቀት በዓል!
Baga Ayyaana Cuuphaa Nagaan Geessan! Ayyaana Gaarii
ርሑስ በዓል ጥምቀት !

@tikvahethiopia
#ከተራ #ጥምቀት

መንግስት የዘንድሮ ዓመት የከተራ እና የጥምቀት በዓል በመላው ሀገሪቱ #በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን አሳውቋል።

የበዓላቱን በሰላም መጠናቀቅ አስመልክቶ ዛሬ ማምሻውን በኮሚኒኬሽን አገልግሎት በኩል መግለጫ ያወጣው መንግሥት ፤ የከተራ እንዲሁም የጥምቀት በዓላት በድምቀት እና በሰላም እንዲጠናቀቁ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia