TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.6K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድብቅ እስር ቤቶቹ‼️

በአዲስ አበባ የተገኙት 7ቱ ድብቅ እስር ቤቶች #ንብረትነታቸው የቤቶች ኮርፖሬሽን መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለሸገር ራድዮ ተናገረ፡፡

ዜጎች የተለያየ ስቃይ እና እንግልትን አሳልፈውባቸዋል የተባሉት እነዚህ ድብቅ እስር ቤቶች በቀድሞው የኪራይ ቤቶች ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በአሁኑ የቤቶች ኮርፖሬሽን ሲተዳደሩ እንደቆዩ #ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ እንደነገሩን ከ7ቱ ድብቅ እስር ቤቶች መካከል የሚደረግባቸው
ምርመራ ተጠናቆ የተወሰኑት ለቤቶች ኮርፖሬሽን ተመልሰዋል፡፡ የቀሩት ግን የሚካሄደው ምርመራ ስላላለቀ ታሽገው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በድብቅ እስር ቤትነት ሲያገለግሉ የቆዩት ቤቶች በየትኛው ክፍለ ከተማና ወረዳ የሚገኙ እንደሆኑ ግን አቶ ዝናቡ በግልፅ ለመናገር #አልፈቀዱም፡፡

#የቤቶች_ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የሚያስተዳድራቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶቹን ገሚሱን ለመንግስት ሹማምንት በመስጠት የተረፉትንም ለተለያዩ ግለሰቦች በዝቅተኛ ዋጋ #በማከራየት ያስተዳድራል፡፡

ድብቅ እስር ቤት ሆነው ቆይተዋል የተባሉት ቤቶች ኮርፖሬሽኑ ለባለስልጣናት ከሰጣቸው መኖሪያዎች መካከል ይሁኑ ወይንም ሌላ እስካሁን አልታወቀም፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia