TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETRSS1 ታህሳስ 10 ከንጋቱ 12:21 ...

የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሳተላይት (ETRSS1) በታቀደላት ጊዜ ለማምጠቅ ምቹ የአየር ፀባይ በመኖሩ ሳተላይቷ ከቤጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኝ ስፍራ ታህሳስ 10 ቀን ከንጋቱ 12፡21 ላይ ለማምጠቅ ሙሉ ዝግጅቱ ተጠናቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETRSS1 የመጀመሪያችን...

የመጀመሪያችን ስልክ - 1883
የመጀመሪያችን መኪና - 1900
የመጀመሪያችን የባቡር ሃዲድ - 1910
የመጀመሪያችን አውሮፕላን - 1938
የመጀመሪያችን የቴሌቪዥን ጣቢያ - 1955
የመጀመሪያችን ሳተላይት - 2012

Via @ETRSS_ethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
READY FOR LAUNCH? ለምጥቀት ዝግጁ?

#ETRSS1 #ESSS #ESSTI #Ethiopia #SpaceGeneration #SatelliteLaunch
#እውንሆነ

(Ethiopian Space Science Society)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS1

- ሀገራችን ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነውን ሳተላይት ወደ ህዋ አምጥቃለች። መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በዚህ ታሪካዊ ቀን በሰማነው የብስራት ዜና እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን።

እውን ሆኗል!

(Armonium Solomon)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE #ETRSS1

የኢትዮጵያ የመሬት ምልከታ ሳተላይት የ700 ኪሎ ሜትር ጉዞዋን አጠናቅቃ የታሰበላትን ምህዋር በመያዝ መረጃ መላክ መጀመሯን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS1-EBC የኢትዮጵያን ባንዲራ አድርጎ በፎቶ ሾፕ አቀናብሮ ያሰራጨው ፎቶ የETRSS1 ሳተላይት ትክክለኛ ፎቶ አይደለም። ትክክለኛውን ፎቶ ማግኘት ባለመቻሉ እጅግ በርካታ የተቀናበሩ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ነው። EBC ፎቶውን ካሰራጨ በኃላ በርካታ የመንግስት ተቋማት፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ሚዲያዎችም ፎቶውን ሲጠቀሙት ተመልክተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS1

በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ኢትዮጵያ ያመጠቀችው ሳተላይት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚመዘገብ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ገለፀ፡፡ በአሁኑ ወቅት ሳተላይቷ ምህዋሯን ይዛ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ኢንስትቲዩቱ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በቀጣዩ ጥቂት ቀናት ውስጥ ደግሞ ሳተላይቷ ወደ ዋናው ስራዋ ትገባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሶስት ዓመት ጊዜው ውስጥ የኮሚኒኬሽን ሳተላይት ለማስወንጨፍ መታቀዱም ተነግሯል፡፡

(MinT-EBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS1

ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ወደ ህዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት ከህዋ ያነሳቸውን የመጀመሪያ ምስል ልካለች። ምስሉን በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ይፋ ያደረጉ ሲሆን የት አከባቢን የሚያሳይ እንደሆነ ግን አልተመለከተም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የመሬት ምልከታ ሳተላይት፤ ETRSS-1, የተነሱ የሙከራ ምስሎች!

#ETRSS1
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS1

"ሳተላይቱ ከቴሌቪዥን ጣቢያም ሆነ ስርጭት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም!"

Ethiopian Remote Sensing Satellite (ETRSS-1)

- ለግብርና፣ የተፈጥሮን ሃብት ለመቆጣጠር፣ ለአየር ንብረት ትንበያ፣ ለካርታ ስራ፣ለተፈጥሮ አደጋዎች ትንበያ (ድርቅ፣ ጎርፍ)፣ ለማዕድን ፍለጋ ጥናት፣ ለየብስና ለባህር ትራንስፖርት ክትትል በዋናነት ይጠቅማል።

- ሳተላይቱ ከቴሌቪዥን ጣቢያም ሆነ ስርጭት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም፣ ሳተላይቱ የመሬት/የምድር ምልከታ ሳተላይት ነዉ።

- ይህንን ሳተላይት ከኢትዮጵያ ውጪ ማንም መቆጣጠር አይችልም።

- ሳተላይት ሰው አይጭንም። ሳተላይቱ አይመለስም።

#TheSpaceGeneration

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia