TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Congratulations #ሚዛን_ቴፒ_ዩኒቨርሲቲ

ተመራቂ ተማሪዎች ያስተማራቸውን ህዝብና ሀገራቸውን #በቅንነትና #በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም #ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም አሳስበዋል። የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በቅድመና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸው 1ሺህ 495 ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት አስመርቋል።

በምርቃው ስነስዓት ወቅት በክብር እንግድነት የተገኙት ሚኒስትሯ  እንዳሉት መንግስት ለትምህርት ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶና ሰፊ ሀብት መድቦ እየሰራ ይገኛል። በዚያው ልክ ተመራቂ ተማሪዎችም ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነት በማገልገል ኃላፊነታቸውን በቅንነት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia