TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተጨማሪ‼️

"የጥቁር አንበሳ የዘንድሮ ተመራቂ ሀኪሞች #ሀኪም_2018 ባደረጉት መዋጮ #30,000 ብር ተሰብስቦ ለእህታችን ተማሪ ማሪያም ተስፋዬ በተከፈተው የሂሳብ ደብተር ቁጥር አስገብተናል። እህታችንን ፈጣሪ ሙሉ በሙሉ ድና ወደ ትምህርቷ ተመልሳና ወገኖቿን በሞያዋ ስትረዳ ለማየት እንዲያበቃን እንመኛለን። #Hakim_2018_Black_Lion!!!"
.
.

እኛም ለማርያም ህክምና አለን ያሉ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤና #ተማሪዎች 3,515 ብር ድጋፍ አድርገዋል። የቀረውን ነገ እናስገባልን ብለውኛል።
.
.
በሌላ በኩል...

ቀደም ብለው የማርየም ጓደኛ የሆኑ ወጣቶች በሀዋሳ እና በሻሸመኔ ከተማ ለማርያም ማሳከሚያ የሚሆን ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ እየሰሩ ነበር ስራቸው እስከ እሁድ ድረስ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። በመሆኑም በሀዋሳ እና ሻሸመኔ ያለው ነዋሪ ይህን እንዲረዳቸው ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ👆

"የጎንደር ዩኒቨርስቲ ኢንተርን ሀኪሞች ግቢውን ለቀው በመውጣት ላይ ይገኛሉ። University of Gondar Interns are currently leaving the campus!" #Hakim

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብርሃም ታሪኩ ምን ይላሉ፦

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ በረራ በኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ ወደተጠቁ ሀገራት ለጊዜው ማቆም አለበት ስንል፦

1. ኮሮና ቫይረስ አደገኛ የሳምባ ምች ሊያመጣ የሚችል እንዲሁም የመተንፈሻ አካል ስራ ማቆም ሊያስከትል መቻሉ!

2. septic shock ወይም ደም ውስጥ የሚሰራጭ ኢንፌክሽን አምጥቶ ኩላሊት ስራ እንዲያቆም አድርጎ ለሞት መዳረጉ

3. ኢንፌክሽኑ ሀገራችን ከተከሰተ ተጠጋግቶ የመኖር ባህላችን አንፃር ለመቆጣጠር በጣም ከባድ ስለሚሆን

4. የሀገራችን የንፅህና ባህል፣የተዳከመ የጤና ስርአት እንዲሁም ከምግብ አለመመጣጠን ጋር ተያይዞ ለስርጭቱ ምቹ ሊሆን ስለሚችል

5. በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚያስፈልጉት የፅኑ ህሙማን መርጃ ክፍሎች (ICU rooms and beds) ፣ መተንፈሻ ማሽኖች (Mechanical ventilators) ፣ አብሮ መደረግ ያለባቸው ምርመራዎች የደም ጋዝ መጠንን (blood gas analysis) ጨምሮ በበቂ ሀገራችን ስለሌሉ በተለይ ደግሞ በሺዎች ለወረርሺኝ ከተፈለገ፤

6. የአለም የጤና ድርጅት የአለም የጤና ስጋት ብዬ ያወጅኩት ደካማ የጤና ስርአት ላላቸው ሀገራት በመስጋት ነው ማለቱ

7. የአለም የጤና ድርጅት ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ውስጥ 12 ከፍተኛ ስጋት (high risk countries) ውስጥ ማስቀመጡ

8. የመንለካው የትኩሳት መጠን ከ14 ቀናት በኋላ ሊከሰት መቻሉ

9. በበረራ ማቋረጥ ምክንያት ልናጣው ከምንችለው ገንዘብ (economy) በላይ በወረርሽኝ ብዙ ሰው ቢሞት ልናጣ የምንችለው በገንዘብ ሲሰላ ስለሚበልጥ (disease burden, disability burden and death burden)

More https://telegra.ph/DrAbrhamTariku-02-02

#HAKIM
@tikvahethiopia
ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ [Social Distancing] እራስ ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅ አለው። ይህ ከላይ የምትመለከቱት ፎቶ ማህበራዊ ርቀትን የጠበቀ አምልኮ በአክሱም ፅዮን ማርያም ሲካሄድ የሚያሳይ ነው። #HAKIM

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
👏የጤና ባለሙያዎቻችንን እናመስግናቸው👏

በዛሬው ዕለት 'በሚሌኒየም ማገገሚያ ማዕከል' ውስጥ ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ 87 ታካሚዎች አገግመው ወጥተዋል፡፡

ማዕከሉ ከተከፈተ በኋላ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ናቸው፡፡ የህክምና ባለሙያዎቻችንን የዛሬው ቀን በእጅጉ የተደሰቱበት ነበር፡፡ እንኳን ደስ ያለችሁ!

በአሁኑ ወቅት ማዕከሉ ውስጥ 656 ታካሚዎች ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

#HAKIM #SPHMMC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia