TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Canada #StudentVisa

ካናዳ በእ.ኤ.አ. 2024 የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቪዛን (የምትቀበላቸውን ተማሪዎች ቁጥር) ትቀንሳለች። ይህም ለሁለት ዓመታት ይቀጥላል።

ሀገሪቱ በ2024 ዕድገቷን ለማረጋጋት ስትል የምትቀበለው 360,000 ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ብቻ እንደሆነ ይፋ አድርጋለች።

የካናዳ ኢሚግሬሽን ስደተኞችና ዜግነት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ብሏል።

አንዳንድ ተቋሞች ገቢያቸውን ለማሳደግ በሚል የቅበላ መጠናቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል እንዲሁም ብዙ ተማሪዎች ለስኬታማነት ተገቢውን ድጋፍ ሳያገኙ ወደ ካናዳ እየመጡ ነው ሲል አስረድቷል።

ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ለካናዳ ማኀበራዊ፣ ኢኮኖሚያና ባህላዊ ለውጥ አንድ አካል ናቸው ሲል ገልጿል።

ይሁን እንጂ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ወደ ካናዳ መምጣት ፦
* በጤና አገልግሎት
* በቤት አቅርቦት ላይ #ጫና እየፈጠረ መጥቷል ነው የተባለው።

በመሆኑም፣ " ተማሪዎችን ከሕገ ወጦች ለመከላከልና የሀገሪቱን የሕዝብ ቁጥር ተመጣጣኝ ለማድረግ አዲስ ሕግ አስፈልጓል " ነው ያለው፡፡

የካናዳ ኢሚግሬሽን ስደተኞችና ዜግነት ሚኒስትር ማርክ ሚለር፣ " አዲሱ ሕግ ለሁለት ዓመት ይቆያል። በ2024 የ360,000 ማመልከቻ ብቻ እንቀበላለን " ብለዋል፡፡

" ይህም ከባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በ35% ይቀንሳል" ብለዋል ሚለር፡፡

" ከመጠን በላይ እየጨመረ የመጣው የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቁጥር በካናዳ ያልተረጋጋ እድገት እያሳዬ " ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ይህን ችግር ለመቅረፍም ከየግዛት አስተዳዳሪዎች ጋር መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ካናዳ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለትምህርት እንዲሁም ለስራ ከሚመርጧትና ለመሄድም ጥረት ከሚያደርጉባት ሀገራት አንዷ እንደሆነች ይታወቃል።

More : https://t.iss.one/ThiqaMediaEth/185

@tikvahethiopia @thiqamediaeth
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከሳቸው የተሻለ ሰው አይገኝም " - ትራምፕ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በአሜሪካ የሚገኙ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስደተኞችን እንደሚያባርሩ የገቡትን ቃል የሚያስፈጽሙላቸውን ቶም ሆማን የተባሉ ባለስልጣን ሾመዋል። የአሜሪካ ድንበር ቁጥጥር ዋና ባለስልጣን " ቦርደር ዛር " ሆነው የተሾሙት በአንድ ወቅት የሀገሪቱ የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ጉዳይ ዋና መሥሪያ ቤት ተጠባባቂ…
#Canada

ካናዳ በስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንደሆነች ተሰምቷል።

ካናዳ ዶናልድ ትራምፕ ልክ ስራ ሲጀምሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ከሀገር ለማባረር ከያዙት እቅድ ጋር በተያያዘ ሊከሰት ለሚችል ማንኛውም ነገር የራሷን ዝግጅት ማድረግ መጀመሯ ተሰምቷል።

በዶናልድ ትራምፕ እቅድ ምክንያት ወደ ሀገሪቱ ለመግባት የሚሞክሩ የስደተኞች ቁጥር ሊበዛ ይችላል በሚል ስጋት የራሷን ዝግጅት እያደረገች ነው።

የትራምፕ ትግበራ በካናዳ ድንበር የጥገኝነት ጠያቂዎችን (asylum) ቁጥር ያበዛዋል በሚል ስጋት ተደቅኗል።

ካናዳ ሂደቶችን በንቃት በመከታተል ላይ ትገኛለች የተባለ ሲሆን ሊከሰት የሚችለውን ማንኛውም አይነት ሁኔታ ለመቆጣጠር ዝግጅት እያደረገች ነው።

የትራምፕ ጥብቅ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ሚሊዮኖችን ማባረር እና የዜግነት ህግን መቀየርን ያጠቃልላል። ይህም ብዙ ሰዎች በህገወጥ መንገድ ወደ ካናዳ ለመሻገር እንዲሞክሩ ሊያደርግ ይችላል።

የካናዳ ባለስልጣናት በድንበር ላይ ሊከሰት የሚችለውን ችግር ለመፍታት ከወዲሁ ዝግጅት እያደረጉ ነው።

ብዙዎች የትራምፕ እርምጃ ወደ ካናዳ ትልቅ የስደተኞች ማዕበል ይዞ ይመጣ ይሆን ? ብለው እያሰቡ ናቸው።

ባለስልጣናቱ ግን የደንበር ቁጥጥርን ለማጠናከር እንዲሁም በህገወጥ መንገድ ሰዎች እንዳይገቡ ፣ ድንበር ላይም ችግር እንዳይፈጠር ትኩረት አድርገው እየሰሩ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia