TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#OLF #BALDERAS

ዛሬ "በብሄራዊ መግባባት" ላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባካሄዱት ውይይት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጥሪ እንዳልተደረገለት አሳውቋል።

ፓርቲው ዛሬ በብሔራዊ መግባባት ላይ ውይይት ሊያደርጉ ነው መባሉ የሰማው ከሚዲያ እንደሆነና ከዚህ ባለፈ ለድርጅቱ የቀረበ ጥሪ የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በፌስቡክ ገጹ እንደገለጸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በብሄራዊ መግባባት ዙሪያ "በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ" እያካሄደ ያለው ውይይት ሁሉን አሳታፊ አይደለም ሲል ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

Via @tikvahethmagazine

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Balderas : አቶ እስክንድር ነጋ ማረሚያ ቤት ውስጥ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ገለፀ።

አቶ እስክንድር በተፈፀማባቸው ድብደባ ምክንያት ጉልበታቸው መቁሰሉን ዋና ሳጅን መስፍን ይልማ (የቂሊንጦ ወህኒ ቤት የፈረቃ ሓላፊ) ለፍርድ ቤት መናገራቸውን ፓርቲው ገልጿል።

አቶ እስክንድር ዛሬ ችሎት መቅረብ እንዳልቻሉ ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት በተከታታይ ምስክር የመስማት ቀጠሮ ተሰርዞ ፤ ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም መዘዋወሩን ባልደራስ አሳውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ችሎት ለመታደም የተገኙ በጅምላ ታፍሰው ልደታ ፖሊስ ጣቢያ መምሪያ ተወስደዋል ሲል ፓርቲው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas : አቶ እስክንድር ነጋ ማረሚያ ቤት ውስጥ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ገለፀ። አቶ እስክንድር በተፈፀማባቸው ድብደባ ምክንያት ጉልበታቸው መቁሰሉን ዋና ሳጅን መስፍን ይልማ (የቂሊንጦ ወህኒ ቤት የፈረቃ ሓላፊ) ለፍርድ ቤት መናገራቸውን ፓርቲው ገልጿል። አቶ እስክንድር ዛሬ ችሎት መቅረብ እንዳልቻሉ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት በተከታታይ ምስክር የመስማት…
#Balderas

ባልደራስ ፓርቲ በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ስለተፈጸመው ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቀ።

ፓርቲው ይህን የጠየቀው በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባሰራጨው መልዕክት ነው።

ባልደራስ ፥ አቶ እስክንድር ነጋ በሚኖሩበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ውስጥ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም. ንጋት 12፡20 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ገልጿል።

አቶ እስክንድር ነገ ወህኒ ቤት ውስጥ በተደራጀ የውንብድና ቡድን መደብደባቸውን ከአቶ እስክንድር ጋር በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ስንታየሁ ለፍርድ ቤት መናገራቸው ተመላክቷል።

አቶ እስክንድር በተፈጸመባቸው ድብደባ ግንባራቸው፣ ዓይናቸው አካባቢ እና ጉልበታቸው ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ፓርቲው ማረጋገጡን ገልጿል።

ለደረሰባቸው ጉዳት የተደረገላቸው ህክምና አለመኖሩም ተመላክቷል።

ባልደራስ ፓርቲ አቶ እስክንድር በአስቸኳይ ቤተሰቦቻቸው ወደ መረጡት ሆስፒታል ተወስደው እንዲታከሙ የጠየቀ ሲሆን ስለተፈጸመው ከባድ ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በቀጥታ ለሕዝብ መግለጫ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የአቶ እስክንድር ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ አቶ እስክንድር ድብደባ የተፈጸመባቸው ከዚህ ቀደምም ያሰጓቸው ስለነበር ወደ ሌላ ማረሚያ ቤት ከተወሰዱ በኋላ በድጋሚ ወደ ቂሊንጦ በተመለሱ 2 ግለሰቦች ነው ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት የመንግሥት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፥ ክስተቱ በግለሰቦች መካከል የተፈጠረ አለመግባባት እንጂ ሆነ ተብሎ አቶ እስክንድርን ለማጥቃት ታስቦ የተደረገ አይደለም ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas ባልደራስ ፓርቲ በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ስለተፈጸመው ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቀ። ፓርቲው ይህን የጠየቀው በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባሰራጨው መልዕክት ነው። ባልደራስ ፥ አቶ እስክንድር ነጋ በሚኖሩበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ውስጥ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም. ንጋት 12፡20 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ገልጿል። አቶ እስክንድር…
#Balderas

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በነአቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ሂደት ችሎት ታድመው የነበሩ 42 የፓርቲው አባላት ታፍሰው ልደታ ክፍለ ከተማ የፖሊስ መምሪያ ከቆዩ በኋላ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው እንዲታሠሩ እንደተደረጉ ገልጿል።

ከታሠሩት ውስጥ አስራ ሁለቱ (12) ሴቶች መሆናቸውን ፓርቲው አረጋግጫለሁ ብሏል።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ባልደረስ) ፥ የታሠሩት አባሎቹ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ሲል ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በነአቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ሂደት ችሎት ታድመው የነበሩ 42 የፓርቲው አባላት ታፍሰው ልደታ ክፍለ ከተማ የፖሊስ መምሪያ ከቆዩ በኋላ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው እንዲታሠሩ እንደተደረጉ ገልጿል። ከታሠሩት ውስጥ አስራ ሁለቱ (12) ሴቶች መሆናቸውን ፓርቲው አረጋግጫለሁ ብሏል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ…
#Balderas : ከታሰሩት የባልደራስ አባላት እና ደጋፊዎች መካከል 2ቱ በዋስ ሲለቀቁ 40ዎቹ ለሰኞ ተቀጥረዋል።

የእነ አቶ እስክንድር ነጋን የችሎት ውሎ ለመታደም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጥቅምት 11/2014 የሄዱ 42 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው ዕለት በፓሊስ መታሰራቸው መግለፁ ይታወሳል።

ባልደራስ ፓርቲ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ የታሰሩት ፥ አቶ እስክንድር በእስር ቤት የደረሰባቸውን ድብደባ በችሎት ከሰሙ በኃላ እያለቀሱ ችሎቱን አቋርጠው ከችሎት ወጥተው በመንገድ ላይ እያኑ ነው ፖሊስ የታሰሩት ብሏል።

ታሳሪዎቹ ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ " ችሎት ውስጥ ረብሸዋል፣ ሲወጡ ደግሞ ፍትህ የለም ፣ መንግስት የለም በማለት ሁከት እና ብጥብጥ በመቀስቀስ " ሲንቀሳቀሱ መያዙን ገልጿል።

ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ የምስክሮችን ቃለ ለመቀበል እና ማስረጃቸውን ለማሰባሰብ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ቆጠሮ ጠይቋል።

የ42ቱ ተጠርጣሪዎች ጠበቆች ፖሊስ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ አቤቱታ ውድቅ እንዲሆን ጠይቀዋል።

"በችሎት ውስጥ ተፈጸመ ለተባለው ድርጊት ፖሊስ የሚመለከተው ሳይሆን በወቅቱ ችሎቱ በራሱ ትዕዛዝ የሚሰጥበት ነው። ሆኖም ግን ችሎቱ ምንም አይነት ትዕዛዝ ባልሰጠበት ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ተገቢ አይደለም" ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ " ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀበት ምክንያት በሕግ ምንም አይነት ድጋፍ " የለውም በማለት የጊዜ ቀጠሮው ውድቅ እንዲሆን በመጠየቅ ከእስር እንዲለቀቁ ለፍ/ቤት ጥያቄ አቅርበዋል ።

ያንብቡ : telegra.ph/BALDERAS-10-22

@tikvahethiopia
#Balderas

በትላንትናው ዕለት ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ ቀለብ (አስቴር) ስዩም በዋና ጽ/ቤት አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopia
#Balderas

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

ፓርቲው በመግለጫው የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሳ ሲሆን ከነዚህ መካከል የሰሜኑ ጦርነት እና የእነ አቶ ስብሃት ነጋ ክስ ማቋረጥ ጉዳይ አንዱ ነበር።

ፓርቲው የሰሜኑ ጦርነት መነሻ ህወሓት የጀመረው ቅድመ ጥቃት እንደሆነ እረዳለሁ ብሏል።

የፌዴራል መንግስቱ በርካታ የአፈፃፀም ችግሮች ቢኖሩበትም ያደረገው የመከላከል ጦርነት ፍትሃዊ እንደሆነ ባልደራስ እንደሚያምን አሳውቋል።

በዚህም ፓርቲው ፖለቲካዊ ድጋፍ ከማድረግም ባለፈ በአካል ቦታው ድረስ በመሄድ ቁሳዊ እገዛ ማድረጉን አስታውሷል።

ነገር ግን መንግስት " ምዕራፍ አንድ " ያለውን ዘመቻ የኢትዮጵያን ሉኣላዊነት ሳያረጋግጥ ማቆሙ ትልቅ አደጋ ያዘለ መሆኑን ፓርቲው መገምገሙን ገልጿል።

ዘመቻውን ያቆመበት አመከንዮ ከማስረዳት አኳያ ሆነ እሱን ተከትሎ ከህዝብ ከሚነሳው ተጨባጭ ስጋት ዙሪያ በቂ ምላሽ አልሰጠም።

ባልደራስ ፓርቲ ፥ " መንግስት ' ተከድተናል ' ለሚለው የኢትዮጵያ ህዝብ እያሳየ ያለውን ንቀት ማስተካከል ይገባዋል። ህወሓት አሁንም የሀገሪቱን አንድነት ሊፈታተን በሚችል ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል። የዘመቻው ፍፃሜ የኢትዮጵያ አንድነት አደጋ ላይ የሚጥለውን የህወሓት ወታደራዊ አቅምን በመስበር መቋጨት ይገባል። " ብሏል።

በተጨማሪም የህወሓት የፖለቲካ እና የጦርነቱ ዋነኛ ቀስቃሽ የሆኑ ጉዳያቸውን በህግ ጥላ ስር ሆነው እየተከታተሉ የነበሩ እስረኞችን ሰሞኑን መፍታት መጀመሩ የህግ የበላይነትን የጣሰ ውሳኔ ሆኖ ማግኘቱን ባልደራስ በመግለጫው ላይ ገልጿል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tikvah-01-13

@tikvahethiopia
#Balderas

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአፋር እና አማራ ክልል የሚያደርጉትን ጉዞ ዛሬ ጥር 6 ቀን 2014 ዓ/ም ጀመሩ።

በፓርቲው ፕሬዜዳንት አቶ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአመራሮች ቡድን ዛሬ ወደ አፋር ክልል ገብተዋል።

ቡድኑ በአፋር የዛሬ ውሎው ከሰመራ 10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ዱቢቲ ሪፈራል ሆስፒታል በማቅናት በግንባር የተጎዱ የጦር አባላትን ጠይቋል።

ባልደራስ ፓርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ የጦር አባላቱ በግንባር ለከፈሉት የህይዎት እና የአካል መስዕዋትነት የተሰማቸውን ታላቅ ክብር በራሳቸውና በድርጅቱ ስም ገልፀው ዕውቅናም እንደሚሰጡት ተናግረዋል።

በአፋር ዱቢቲ ሪፈራል ሆስፒታል በጦርነቱ ሳቢያ የተጎዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣የአፋር ልዩ ኃይል፣ የአፋር ህዝባዊ ሰራዊት እና ሚሊሻ እንዲሁም ቁስለኛ የህወሓት ሰራዊት አባላት እንደሚገኙ ተገልጿል።

አመራሮቹ ከሆስፓታል መልስ በክልሉ መስተዳድር ጥያቄ መሠረት በአፋር ዱፍቲ በአዋሽ ወንዝ እየለማ ያለውን የስንዴ ምርት መጎብኘታቸውን ፓርቲው አሳውቋል።

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች በአፋር ጉብኝታቸውን ሲያጠናቅቁ ወደ አማራ ክልል እንደሚያመሩ ይጠበቃል።

ፎቶ ፦ ባልደራስ ፓርቲ

@tikvahethiopia
#Balderas

" ጉዳት ያደረሱት የፀጥታ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ እንጠይቃለን " - ባልደራስ ፓርቲ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፥ ዛሬ ጥር 12/2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ በሚገኘው የወይብላ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለጥምቀት የወጣ ታቦታ እና አጅበውት በነበሩት ህዝበ ክርስቲያን ላይ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ተኩስ በመክፈት ታቦቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገባ ባደረጉት ክልከላ እና ይህን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት በርካታ ምዕመናን ለጉዳት መዳረጋቸውን አሳውቋል።

ፓርቲው፥ " በዚህ ግጭት ከልጅ እስከ አዛውንት የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት በምዕመናኑ ላይ መድረሱን ተገንዝቤያለሁ " ብሏል።

በርካታ ምዕመናን በህክምና መስጫ ተቋማት ህክምና እየተከታተሉ እንደሆነም ለመረዳት ተችሏል፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በመግለጫው ላይ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን ገልፆ ፥ " የኦህዴድ/ብልፅግና ’መንግስት’ አሁንም ህግ የማስከበር ተቀዳሚ ተግባሩን አለመወጣቱን ባልደራስ አበክሮ ያወግዛል " ብሏል።

አክሎም ፥ " አሁንም እየደረሰ ላለው ውጥረት እና ግጭት ’መንግስት’ ህግ እንዲያስከብር እንጠይቃለን። ጉዳት ያደረሱትን የፀጥታ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑም ባልደራስ ይጠይቃል " ብሏል በመግለጫው።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት ወይም ከኢኦተቤ መገናኛ ብዙሀን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት በኩል የወጣ ተጨማሪ መረጃ ለመፈለግ ጥረት ብናደርግም ለጊዜው ማግኘት አልቻልንም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የታሰሩበት 33 አባላቱ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን አስታወቀ። ከ33ቱ መካከል ሁለቱ ለለ14 ቀን ሲቀጠሩ ቀሪዎቹ 31 አባላቱ ለሀሙስ መጋቢት 1 ተቀጥረዋል ብሏል። ተከሳሾቹ ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡት ለሁለት ቡድን ተከፍለው ሲሆን 31ዱ እስረኞች ከልደታ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው የቀረቡት። ሁለቱ ደግሞ ጊዮርጊስ የሚገኘው…
#Balderas

ከዓድዋ እና ካራማራ ድል መታሰቢያ በዓላት ጋር በተያያዘ ታስረው የቆዩ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት ሁሉም ከእርስ ተለቀዋል።

ከእስር የተለቀቁት በዋስትና ነው።

ፖሊስ ወጣቶቹ በእስር ላይ በነበሩ ሰዓት ለፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ከዓድዋ እና ካራማር በዓላት ጋር በተያያዘ ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት ፣ ህዝብን በመንግስት ላይ እንዲያምፅ የመንግስት ባለስልጥናትን በአደባባይ በመስደብ ተግባር ላይ አግኝቻቸዋለሁኝ ብሏል።

የፓርቲው ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ ክሱን በተመለከተ " ወጣቶቹ ትግላችን ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ነው፤ ሁለቱም አደጋ ላይ ናቸው ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን " ሲሉ መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ ለ41 ቀናት መታሰራቸውን ገልፆ ትላንት እና ዛሬ በዋስ ከእስር መፈታታቸውን አሳውቋል።

@tikvahethiopia