TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሰርሓ ከተማ⬆️

በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የጎሎመኻዳ ወረዳ የልዑካን ቡድን ኤርትራ ገብቷል።

40 ሰዎችን ያካተተው የልዑካን ቡድን #ከዛላንበሳ አለፍ ብሎ በሚገኘው ሰርሓ ከተማ ገብተዋል።

የልዑካን ቡድኑ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና እናቶች የሚገኙበት ሲሆን፥ ከኤርትራ አቻዎቻቸው ጋር #የሰላም ውይይት አድርገዋል።

ቡድኑ ወደ ሰርሓ ሲገባም #የኤርትራ ወታደሮች አቀባበል እንዳደረጉላቸው የትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትግራይ_ክልል፣_አክሱም_ከተማ_የተፈጸመው_ከፍተኛ_የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰት_ምርመራ_ሪፖርት.pdf
610.2 KB
የአክሱም ሪፖርት ፦

በኣክሱም ከተማ ትግራይ ክልል የደረሰውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፣ የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርቱን ትላንት ለሊት ይፋ አድርጓል።

ከበርካታ ሳምንታት ጥረት በኋላ የምርመራ ባለሞያዎቹን ወደ አክሱም ከተማ መላክ መቻሉን ገልፆ ፤ ባለሞያዎቹ ከየካቲት 20 እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ድረስ በከተማዋ በመቆየት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን፣ 45 የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የዓይን ምስክሮችን እና የሃይማኖት መሪዎችን አነጋግሯል። እንዲሁም 20 ሰዎች የተሳተፉበት የቡድን ውይይት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር አድርጓል።

በተጨማሪ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከአክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል፣ ከአክሱም ሪፈራል ሆስፒታል፣ ከሚመለከታቸው የቀበሌ መስተዳደር አካላት እንዲሁም ከሃይማኖት ተቋማት አገልጋዮች የተለያዩ የምስል፣ የድምጽ እና ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎችን አሰባስቧል።

ኢሰመኮ በዚህ ምርመራው ያሰባሰባቸው መረጃዎች በተለይ ከኅዳር 19 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በነበሩት ሁለት ቀናት ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንደተፈፀመ አረጋግጧል።

- የአክሱም ከተማና አከባቢው ነዋሪዎች፣
- ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ጦርነት ሸሽተው በከተማዋ የተጠለሉ ተፈናቃዮች እና
- የኅዳር ፅዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ለማክበር ከተለያየ ቦታዎች የመጡ ሰዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከአንድ መቶ በላይ ሲቪል ሰዎች በወቅቱ በአክሱም ከተማ በነበሩ #የኤርትራ_ወታደሮች መገደላቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል።

*ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ በPDF ፋይል ተያይዟል (በዝርዝር እንመለከተዋለን)

@tikvahethiopia