TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የታማሚዎች ሁኔታ ፦

- በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጠ ስምንቱ ሰዎች መካከል አምስቱ #ከዱባይ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።

- አንድ የዘጠኝ (9) ወር ህጻንና ወላጅ እናቱ ይገኙበታል።

- አንድ የ25 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ከታይላንድ መጥታ በለይቶ ማቆያ ክትትል ስታደርግ የነበረች በቫይረሱ መያዟ ተረጋግጧል።

- አንድ የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ጉዞ ታሪክ #የሌለው ሲሆን የንክኪ ሁኔታውም በመጣራት ላይ ይገኛል። ወጣቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።

- ሌላኛዋ የ30 ዓመት ሴት ኤርትራዊት ስትሆን ከእንግሊዝ ለንደን መጥታ በአዲስ አበባ በለይቶ ማቆያ ክትትል እያደረገች የምትገኝ ናት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AtoAknawKawza

ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የተሰጠ መረጃ ፦

በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት በ2 ዞኖች ማለትም ወላይታ /ቦዲቲ/ እና ጉራጌ/ቡታጅራ/ በለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በደቡብ ህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ በተደረገው 34 የላብራቶሪ ምርመራ 2 (ሁለት) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁለቱም ሰዎች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡

የዕለቱ ታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ20 ኢትዮጵያዊት ፣ ከቦዲቲ ወረዳ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላት ፤ ከሞያሌ የተመለሰችና በቦዲቲ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች።

ታማሚ 2 - የ50 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ ከቡታጅራ ወረዳ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የሌለው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ሲሆን ለሌላ ህክምና ሆስፒታል መጥቶ በነበረው ምልክት መነሻ ናሙና ተወስዶ የተረጋገጠ።

በደቡብ ክልል ቫይረሱ የተገኘባቸው አጠቃላይ ሰዎች ከጤና ሚኒስቴር በተገለጸው መሰረት 6 (ስድስት) መድረሱን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።

(ደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት ጤና ቢሮ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 14 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,271 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ አራት (14) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 365 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 11 ወንድ እና 3 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ9 እስከ 68 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 9 ሰዎች ከአዲስ አበባ (1 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ ፣ 7 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ፣ 1 ሰው የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌለው) ፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ ፣ መቐለ ለይቶ ማቆያ ያለ) ፣ 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ) ፣ እንዲሁም 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 6

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 7

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 1

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት 4 ሰዎች (3 ከሶማሌ ክልል 1 ከአፋር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ (120) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋገጠ!

መደበኛ 24 ሰአት ዕለታዊ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ ለ #MoHEthiopia በደረሰው አዲስ መረጃ መሰረት በሃረሪ ክልል በተደረገ 12 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ (1) ሰው የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል።

ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ የ37 ዓመት የሀረር ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌለው ነው።

#DrLiaTadesse

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሀረሪ ክልል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 175 የላቦራቶሪ ምርመራ ነው 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። በአጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 8 ደርሷል፡፡

የእለቱ ታማሚዎች ተጋላጭነት ሁኔታ ከታወቀ ታማሚ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው እና የውጪ ጉዞም የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ25 ዓመት ወንድ ፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው የታወቀ ግንኙነት #የሌለው

ታማሚ 2 - የ30 ዓመት ወንድ ፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው የታወቀ ግንኙነት #የሌለው

ታማሚ 3 - የ35 ዓመት ሴት ፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው የታወቀ ግንኙነት #የሌላት

የላቦራቶሪ ምርመራው የተደረገው በሀረማያ ዩኒቨርሲቲና በሀረሪ ክልል ላቦራቶሪ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያውያን እና የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ናቸው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Oromiyaa

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 293 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሆለታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የሌለው፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 2 - የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊት የሰበታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia