TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሲዳማ ዞን አስተዳደር⬇️

የዞናችን ሕዝቦች ከዚህ እንደቀደመው ሁሉ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ነቅቶ እንዲጠብቅና ለረጅም ዓመታት ያጎለበተውን እንግዳ ተቀባይነት ባህሉን እንዲያሳይ የሲዳማ ዞን አስተዳደር አሳሰበ።

እንደሚታወቀው ከፊታችን መስከረም 18-21/2011 ዓ.ም የዴኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ እና ከመስከረም 23-25/2011 ዓ.ም የኢህአዴግ ድርጅታዊ #ጉባዔ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል። በእነዚህ ጉባኤዎች የጉባኤ ተሳታፊ እንግዶች ፣ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ከሀገር ውስጥና ውጭ ታላላቅ ሚዲያዎች የሚታደሙበት ጉባዔ በመሆኑ እንግዶችን ለመቀበል የሲዳማ ዞንና #የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል በሀገራችን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ተስፋ ሰጪና የመላው ዞናችን ሕዝብ #ተስፋ ያለመለመ በመሆኑ ሕዝባችንን ከለውጡ ጎን እንዲሰለፍ አስችሏል። ይህ የለውጥ ህደት ያልተመቻቸው እየፈነጠቀ ያለውን የተስፋ ብርሃን ለማጨለም በተለያዩ ጊዜያት በዞናችንም ሆነ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በለውጥ #አደናቃፊ ኃይሎች የተቀነባበረው ትንኮሳና መሰሪ ዓላማቸው በፀጥታ ኃይሉና በሕዝባችን ብርታት
እየመከነ በዞናችን ውስጥ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር መቻሉ አንዱ ማሳያ ነው።

ጉባዔዎቹ #በሰላም መጠናቀቅ የሕዝባችንን ሰላም ወዳድነቱን፣ እንግዳ ተቀባይነቱን ከማጉላት ባሻገር የሲዳማ ሕዝብ ለጠየቀው ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲያገኝና በሀገራችንም የተጀመረው የለውጥ ጅማሮን ለማስቀጠል ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም አልፎ አልፎ የለውጥ አደናቃፊ ኃይሎች በኀብረተ ሰቡ ውስጥ ስጋት ለመፍጠር በሚያደርጉት ትንኮሳ ሳይደናበር መላው ሕዝባችን ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እኩይ ዓላማቸውን እንዲያመክንና ለጉባዔው በሰላም መጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የሲዳማ ዞን አስተዳደር ጥሪውን ያቀርባል።

መስከረም,16/2011 ዓ.ም
ሀዋሳ,ሲዳማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የቁልቢ ገብርዔል ዓመታዊ ንግሥ በሰላም ተጠናቋል፡፡ በተመሳሳይ #የሀዋሳ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ተጠናቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
(የካቲት 27/2011 ዓ.ም.)

#የሀዋሳ_ኢንዱስትሪ_ፓርክ ሠራተኞች ሥራ የማቆም አድማ መትተዋል። ሠራተኞች አድማ የመቱበት #ምክንያት በተደጋጋሚ ጊዜ አቅርበናል ያሉት #የደመወዝ ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ መሆኑን ተናግረዋል። ሠራተኞቹ #ደኅንነታቸው እንደማይጠበቅና ለፆታዊ ጥቃትና ለዝርፊያም እንደሚጋለጡ ገልፀዋል።

በኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ #በላይ_ኃይለሚካኤል “ችግሩ የአንዳንድ ኩባንያዎችና የአስተዳደር በደል ነው” ብለዋል።

ምንጭ፦ VOA አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እንገናኝ!
(ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ)

ውድ #የሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በፍቅር ሀገር እንገንባ #የጥላቻ_ንግግር በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ ይቁም በሚል ልዩ መድረክ ተዘጋጅቷል። በዝግጅቱ ከፍተኛ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ #አመራሮች ይገኛሉ። ወጣት ተማሪዎች መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ። ባለሞያዎች ስለማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ግንዛቤ ይሰጣሉ።

N.B በዝግጅቱ #ተሳታፊ የሚሆኑ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ #አባላት ለዲላ፣ መቀለ እና ቡሌሆራ ጉዞ ይመዘገባሉ!

ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንመጣለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰላም ደርሰዋል!

#ከሀዋሳ_ከተማ የተነሱት #የሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት አዲስ አበባ ከተማ/መስቀል አደባባይ/ በሰላም ደርሰዋል።

ኑ ፍቅርን እንዝራ!
ኑ ፍቅርን እንስበክ!
ኑ ፍቅርን እናቀንቅን!
#StopHateSpeech

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል የጎብኚ ቁጥር አሽቆልቁሏል!

በደቡብ ክልል #የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው #አለመረጋጋት የጎብኚዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የስራ ሃላፊ እንዳሉት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ክልሉን የጎበኙ የውጭ አገር ጉብኚዎች ቁጥር አምና ከነበረው በአራባ ዘጠኝ ሺህ ያህል ቀንሶል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ አየለ እንዳሉት በክልሉ የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው አለመረጋጋት በጎብኚዎች እንቅስቃሴ ላይ የራሱን ተፅህኖ አሳድሯል።

ለአብነትም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ወደ ክልሉ የመጡ የውጭ አገር ጎብኚዎች አምና ከነበረው በአራባ ዘጠኝ ሺህ ያህል ቀንሶ መገኘቱን ነው የቢሮ ሃላፊዋ ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ የጠቀሱት። የቱሪዝም ዘርፈ ጥንቃቄ የሚያሻው በትንሽ ስጋት ሊደናቀፍ የሚችል መሆኑን የጠቆሙት ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ በቀጣይ መስህቦችን መልሶ የማስተዋወቅ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል።

በደቡብ ክልል የሆቴሎች ህብረት ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደጀኔ ጌታቸው በከተማው ተፈጥሮ በነበረው ሁከት የጎብኚዎች ቁጥር አስከመቆም በመደረሱ በከተማው በሆቴል ዘርፍ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶች ላይ የገበያ መቀዛቀዝ ማጋመጠሙን ተናገረዋል። ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ መንግስት ባከናወናቸው የማረጋጋት ስራዎች ዘርፉ አንፃራዊ መሻሻል እያሳየ መምጣቱን ነው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደጀኔ የገለጹ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ገለቱ ገረመው በበኩላቸው የአስተዳደሩ የፀጥታ መዋቅር ከጊዚያዊ ኮማንድ ፖስትና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መስራት ከጀመረ ወዲህ ከተማዋ ወደ ነበረ ሰላሟ እየተመለሰች ትገኛለች ብለዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የሀዋሳ_ከተማ_ፖሊስ

ባዕድ ነገር ጨምረው እንጀራ በመጋገር በህገወጥ መንገድ የሚያከፋፈሉ ተጠርጣሪዎች በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።

በቀን 25/4/2013 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በታቦር ክ/ከተማ ከወልደ አማኑኤል ዱባለ አደባባይ አለፍ ብሎ በሚገኘው መንገድ 500 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ሙሉ ግቢ ተከራይተው ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የተገኙት ተጠርጣሪዎቹ ህብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን ደህንነት አደጋ ውስጥ የሚከት የትኛውንም አይነት ህገወጥ ተግባር እንደማይታገስ ገልጿል።

መሰል ተግባራት የሚፈፅሙ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከነዋሪው ጋር የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።

ለጤና ጠንቅ በሆነ መንገድ ንፅህናውን ባልጠበቀ መልኩ ባዕድ ነገር የተቀላቀለበት እንጀራ በመጋገር እና በማከፋፈል ህገወጥ ተግባር በሚፈፅሙ አካላት ለይ አስፈላጊውን ማጣራት አደርጎ በህግ አግባብ ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑንም የከተማው ፖሊስ አስታውቋል።

ዝርዝር ጉዳዮ በሚመለከተው አካል በተገቢው ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ተብላል።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT