TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጄነራሎቹ⁉️

የቀድሞው የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ዋና ሃላፊ ሜጀር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው መያዛቸው ተነገረ። ሃላፊው ከትግራይ የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው ጀነራሉ የተያዙት ትናንት ማምሻ ሁመራ ከተማ ውስጥ ነው።

#የትግራይ ልዩ ፖሊስ ጀነራሉን ከያዘ በኋላ ለፌደራል መንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች #ማስረከቡን ምንጮች አስታውቀዋል። ከጀነራል ክንፈ ዳኘው በተጨማሪ የቀድሞ ኢንሳ በሚል ምህጻረ ቃል የሚጠራው የመረጃ ቴክኖሎጂ መስሪያ ቤት የቀድሞ ሃላፊ ሜጀር ጀነራል #ተክለብርሃን_ወልደአረጋይም ከሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ጋር #መያዛቸውን የተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበው ነበር።

ይሁን እና ጀነራል ተክለብርሃን የፍርድ ቤት #የማሰሪያ ትዕዛዝ አልተሰጠባቸውም በሚል እንዳልተያዙ ምንጮቼ ገልጸዋል ብሏል የጀርመን ድምፅ ራድዮ የአማርኛው አገልግሎት ክፍል።

ጉዳዩን #ለማጣራት የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን እያነጋገረን ነው እንደደረሰን መረጃውን እናቀርባለን ብሏል የጀርመን ድምፅ።

ሁለቱን ጀነራሎች ጨምሮ በርካታ የቀድሞ ከፍተኛ የጦርና የመረጃ (ስለላ) ባለሥልጣናት እሥረኞችን በማሰቃየት እና በሙስና ወንጀል እንደሚጠረጠሩ የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ትንንት አስታውቆ ነበር።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተይዘው እየመጡ ነው‼️

የቀድሞ የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ ከድርጅቱ አሰራር ጋር በተያያዘ በወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑት የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በምዕራባዊ ትግራይ በኩል #ባታር በተሰኘው አካባቢ ነው በህብረተሰቡ እና በመከላከያ ኃይል ትብብር የተያዙት፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ወደ አዲስ አበባ ተይዘው እየመጡ ነው፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ብርጋዴር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው በቁጥጥር ስር የዋሉት #በትግራይ ክልል ልዩ ፖሊስ ነው።

via-etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጄነራሉ ተይዘው አዲስ አበባ መጥተዋል‼️

በዛሬው እለት በቁጥጠር ስር የዋሉት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው አዲስ አበባ ገብተዋል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ #እንዳረጋገጠው ተጠርጣሪው በሁመራ በኩል ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ በትግራይ ክልል ልዩ ሀይል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ #ደርሰዋል

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሌሎች የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው ትናንት ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወቃል።

በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይም ፍርድ ቤቱ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱም የሚታወቅ ነው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማረሚያ ገብተዋል‼️በቁጥጥር ስር የዋሉት ሜጀር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው አዲስ አበባ ገብተው ወደ ማረሚያ ቤት አቅንተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ሜጀር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው አቅም የለኝም መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ ብለው ያቀረቡት ጥያቄያቸውን ዛሬ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው‼️

የብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር በነበሩት ሜጀር ጀኔራል #ክንፈ_ዳኘው በራሳቸው ወይም ጠበቃ አቁመው ለመከራከር ከቤተሰብ ጋር መክረው ለሰኞ ህዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጠ።

ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ‘የ4ሺህ ብር ጡረተኛ በመሆኔ ጠበቃ ለማቆም አቅም የለኝምና መንግስት #ጠበቃ ያቁምልኝ’ ያሉትን ውድቅ በማድረግ በራሳቸው እንዲከራከሩ ውሳኔ ሰጥቷል።

በጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ከባንክ 100 ሺህ ብር ማውጣታቸውንና ይህንን ያህል ገንዘብ በዚሁ ጊዜ ሊጠፋ እንደማይችል፣ የመኖሪያ ቤት፣ 80 ሺህ ብር ዋጋ ያለው መኪናና በባንክ ውስጥ 5ሺህ300 ብር እንዳላቸው ፖሊስ ማስረጃ አቅርቧል።

የተጠርጣሪው ጠበቆች ‘ፖሊስ ያቀረበ ማስረጃ ጠበቃ ለማቆም አያስችልም’ ሲሉ ተከራክረዋል።

ተጠርጣሪው ‘በ2005 ዓ.ም ያስመዘገብኩት ሊወርድ ይችላል። ቤትና መኪና በስሜ የተመዘገበ ምንም የለኝም። ንብረት ካለኝ ይወረስ’ ብለዋል።

ተጠርጣሪው ይህን ቢሉም ፍርድ ቤቱ በራሳቸው ወይም ጠበቃ አቁመው እከራከራለሁ የሚለውን ከቤተሰብ ጋር ተማክረው እንዲቀርቡ ለሰኞ ህዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሩ ሰጥቷል።

ከ2002 እስከ 2010 ዓ.ም የብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር በነበሩት ወቅት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጠበቃ ለማቆም አቅም እንደሌላቸው ቃለ ምሃላ መፈጸማቸው አይዘነጋም።

ተከላካይ ጠበቃ እንዲመደብላቸው ትዕዛዝ የሰጠው ችሎቱ መንግስት በሚያቆምላቸው ተከላካይ ጠበቃ በኩል የተጠርጣሪውን ምላሽ ለመስማት ለህዳር ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።

የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ መርማሪ ቡድን እንዳስረዳው ተጠርጣሪው ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው 15 የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ያቀፈውን ሜቴክ ሲመሩ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ወደጎን በመተው በአገርና ህዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ምዝበራ እንዲደርስ አድርሰዋል በሚል መጠርጠራቸውንም አስረድቷል።

ከተጠቀሱ የወንጀል ድርጊቶች መካከልም ሕጉን ባልተከተለና የድርጅቱን መመሪያ በጣሰ መንገድ በቢሊየን የሚቆጠር የአገር ውስጥና የውጭ ግዥዎች ያለምንም ጨረታ እንዲፈጸም በማድረግ አገራዊ ኪሳራ እንዲደርስ ማድረጋቸውን ጠቅሷል።

ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ግዙፍ አገራዊ ፕሮጀክቶችን እሰራለሁ በሚል ‘ጨረታ ማወጣት ስራ ማጓተት ነው’ በሚል ፕሮጀክቶቹን ለስጋ ዘመድና በጥቅም ከሚጋሯቸው ሶስተኛ ወገን ለጨረታ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲባክን አድርገዋል በሚል መጠርጠራቸውን አስረድቷል።

በሌላ በኩል ደርጅቱ ከተቋቋመበት ተልዕኮ ውጭ ከኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት ሎጀስቲከስ አገልግሎት ደርጅት ከ28 ዓመታት በላይ ያገለገሉና ያረጁ ‘አባይ ወንዝና አንድነት’ የተሰኙ መርከቦችን ብረት ለመጠቀም ግዥ ፈጽሞ ጅቡቱ ወደብ ላይ ለግማሽ ዓመት እንዲቆሙ በማድረግ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንዲከፈል አድርጓል ተብሏል።

በኋላም ዱባይ ከሚገኝ የጋራዥ ድርጅት ከ3 ሺህ ዶላር በላይ ወጭ ለአንድ ዓመት በማስጠገን ህገ ወጥ በሆነ መንገድ በተለይም ቀይ መስመር ተብሎ በሚታወቀው ከኢራን እስከ በርበራ/ሶማሊያ/ ጭነት በማዘዋወር ሲሰሩ ቆይተው ነገር ግን በድርጂቱ ባንክ ሂሳብ አንድም ገንዘብ ገቢ አላደረጉም።

በመጨረሻም እጅግ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጭ የተደረጋበቻው መርከቦች አጅግ በወረደ መጠን ከ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ባልበለጠ ዋጋ አንዲጨሹ ተደርጓል ነው የተባለው።

በሌላ በኩል ከድርጅቱ ሃለፊነት ውጭ ለረጂም ጊዜ አገልግሎው የቆሙና ነዳጃቸውም አገር ውስጥ የሌላ ስድስት አውሮፕላኖችን ከእስራኤል በመግዛትና ደጀን አቬሽን የሚል በማቋቋም ካለምንም ጥቅም ከፍተኛ ብክነት አንዲደርስ አድርገዋል፣ አስራ ሁለት የሚሆኑ ደረጃቸው የወረዱ ሚግ-23 አውሮፓለኖችን ለአገልግሎት አበቃለሁ በሚል ግዥ በመፈጸምም ያለምንም ጥቅም እስካሁን ድርስ እንዲቀመጡ አድርጓል።

በሌላ በኩል በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ የወዳደቁ ብረቶችን አገልግሎት የሚሰጡትን አገልግሎት ላይ አንዳይውሉ፣ የሚወገዱትንም አንዳይወገዱ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ  ሃብት አላግባብ እንዲባክን አድርገዋልም ተብሏል።

እንደ ያዮ ማዳበሪያ ፋብሪከ አይነት ፕሮከጅቶችም ካለምንም አዋጭ ጥናትና የባለሙያ ያልታገዙ እቅዶችን እየተመራ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲባክን አድርጓል፣  ካለምንም አዋጭነት ጥናት በድርጅቱ የተመረቱ ቁሳቁሶችም ገዥ በማጣት ለዓመታት አላግባብ ተከማችተዋል ብሏል።

ከአስር ስኳርና የማደባሪያ ፍብሪካዎችን ለመገንባት የተረከበው ሜቴክ ማከናወን ባለመቻሉ አንዳንዶቹ ለሌላ ድርጅት እንዲሰጡ መደረጉን የገለጸው መረማሪ ፖሊስ፣ ድርጅቱ ለፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ የሚሆን በቢሊየን ከፍተኛ ገንዘብ ተረክቦ ነገር ግን ፕሮጀክቶቹ ሳይከናወኑ ገንዘቡም ከድርጅቱ የባንክ ሂሳብ አንደሌላ አስረድቷል።

በአጠቃለይ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በራሳቸው ትዕዛዝ ኮርፖሬሽኑ ከህግ ወጭ ግዥዎችን በመፈጸም፣ ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና የጥቅም ተጋሪ ሶስተኛ ወገንን ለመጥቀም ሲሉ ከፍተኛ ምዝበራ አድርሰዋል በሚል በከባድ የሙስና ወንጀል መጠርጠሩን ለችሎቱ አስተድቷል።

ከዚህም በተጨማሪ ተጠርጣሪው በህግ አንደሚፈለጉ እያወቁ ከአገር ለመውጣት ሲሞክሩ ጠረፍ ላይ ሁመራ አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስረድቷል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኛው‼️

በሜጀር ጀኔራል #ክንፈ_ዳኘው ላይ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ።በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት ቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤት ፈቀደ።

አመልካች መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ ተጨማሪ የሙስና ወንጀል ድርጊት ማግኘቱን ከትናንት በስቲያ ለችሎቱ አመልክቶ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር።

ድርጅቱ የሚያከናውናቸውን ስምምነቶች 90 በመቶ በተጠርጣሪ የሚፈጸሙ መሆኑን በመግለጽ፣ ተጠርጣሪው ቢወጡ አጠቃላይ የምርመራውን ሂደት ያደናቅፋሉ በሚል የተጠርጣሪ ጠበቆች ያቀረቡትን ዋስትናም ተቃውሞ ነበር።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አቃቤ ህግ በሜጀር ጄኔራል #ክንፈ_ዳኘው እና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መሠረተ። በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በመዝገብ ቁጥር 229396 ዛሬ በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ከእርሳቸው በተጨማሪ በተመሳሳይ ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ረመዳን ሙሳ፣ ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ፣ አቶ ቸርነት ዳና ላይ ክስ መመስረቱን አቃቤ ህግ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት አስታውቋል። በዚህም መሠረት ተጠርጣሪዎቹ በ10ኛ ወንጀል ችሎት የነበራቸው መዝገብ ተዘግቶ ጉዳያቸው በ15ኛ ወንጀል ችሎት እንዲታይ ተደርጓል።

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia