TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
#Tigray

" በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ ነው " - ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

ዛሬ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ክልል ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን አሳውቀዋል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ፤ የፌዴራል መንግስት ህወሓትን ከሽብርተኝነት ፍረጃ መሰረዙ በህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ፕሬዜዳንትነት የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ትግበራ ለመግባት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ስለመግለፃቸው ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ህወሓት ከሽብርተኝነት መዝገብ ስለመሰረዙ ምን አሉ ?

" በዛሬው ዕለት ህወሓት ከሽብር መዝገብ ተሰርዟል። ስለሆነም ጊዜያዊ አስተዳደራችን ስራው የሚጀምርበት ሁኔታ ተሟልቷል።

#በጀት የማዘጋጀትም ይሁን ሌሎች #ከእስረኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የወንጀል ክሶችን በማንሳት እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በሁለቱም ወገን በኩል ግኝኑነት ተጀምሯል።

በመሆኑም በበኩላችን በጓድ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደራችን ስራዎቹ እንዲሳኩ ለማድረግ ሁሉንም አቅማችንን በማቀናጀት ከፍተኛ ርብርብ እናደርጋለን።

የትግራይ ህዝብም በሁሉም አቅሙ የጊዜያዊ አስተዳደራችን ደግፎ እንዲሰማራ ጥሪ እናቀርባለን። "

ዶ/ር ደብረፅዮን ስለ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ምን አሉ ?

" የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማፋጠን አሸባሪነት የሚለው ሳይነሳ ቀድመን ነው እየሰራን የመጣነው። ጊዜያዊ መንግስቱን ለማቋቋም በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መምጣታቸውን ሁሉም ሲከታተለው የነበረ ጉዳይ ነው።

ኮሚቴ ከማቋቋም ጀምሮ ሁሉም ጊዜያዊ አስተዳደሩን በተመለከተ አጀንዳው አድርጎ እንዲሰራ በውስጥም በውጭም መድረኮችን በማዘጋጀት ተሰርቷል።

ኮንፈረንስ በማዘጋጀት እና ከኮንፈረስን በኃላ ምርጫዎችን በማካሄድ ሊያካትታቸው የሚገባ ፈፃሚ አካላት እንዲመረጡ ተደርጓል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ #ህወሓት እና #ባይቶና ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የትግራይ ሰራዊት ፣ የትግራይ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚሳተፉ አካላት ተሟልተን ለማዕከላዊ መንግስቱ አሳውቀናል። "

ዶ/ር ደብረፅዮን #ህወሓትን በተመለከተ ምን አሉ ?

" ድርጅታችን ህወሓት የትግራይ ግዛታዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ሰላም የሰፈነባትና ብሔራዊ ክብሯ የተጠበቀች ትግራይን ለመገንባት ሁሉንም አቅሙን በማቀናጀት የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚታገልበት ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት!! "

@tikvahethiopia