TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#OLF

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በቀጣዩ ምርጫ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚወዳደር አስታውቋል። በምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሂደቱን ገና ያልጨረሰው ኦነግ ፤ በመላ ሃገሪቱ ምርጫ መወዳደር የሚያስችል ቁመና አለኝ ብሏል። ከምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሰርተፍኬት የማግኘት ሂደቱን ከጨረሰ በኋላ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጀምርም አስታውቋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-08-27-5

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OLF

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና አገኘ። የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ፓርቲው ከህዳር 4 ቀን 2012 ዓ.ም በአገር አቀፍ ፓርቲነት መንቀሳቀስ የሚያስችለውን ህጋዊ እውቅና ማግኘቱን አስታውቋል።

(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OFC #OLF

ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በመቐለ ከተማ ፌደራል ስርዓቱንና ህገ-መንግሥቱን መጠበቅ በሚል በተካሄደው የውይይት መድረክ ጥቂት የማይባሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጥሪውን ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ከእነዚህ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ነው፡፡ የፓርቲው የወጣቶች ዘርፍ ተጠሪ አቶ አዲሱ ቡላላ ህውሐት ከዚህ በፊት የፌደራል ስርዓቱን በስርዓት ሲመራ ስላልነበር ዛሬ የፌደራል ስርዓቱ ተቆርቋሪ ነኝ ማለቱ የሚታመን አይደለም ይላሉ፡፡

በተመሳሳይ ጥሪውን ውድቅ ያደረገው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ነው፡፡ የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ ደግሞ ከዚህ በፊት እኛን ሲያሳድድ ከነበረ ሃይል ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሊኖረን አይችልም ብለው ከመድረኩ ቀርተዋል፡፡ በትግራይ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ጥሪው ስላልተደረገላቸው ቀርተዋል ተብሏል፡፡

በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የአረና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረስላሴ ጥሪ እንዳልተደረገላቸው ለቢቢሲ ሬድዮ አማርኛ ክፍል ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ከትግራይ ክልል የተገኙት ሁለት ፓርቲዎች ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡ ህውሐት የፌደራል ስርዓቱና የህገ-መንግሥቱ ጠባቂ ነኝ የሚለው ሌሎች ላይ ጫና ለማሳደር እንደሆነም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

(AHADURADIO)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OLF

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ምርጫ 2012 በሰላም እንዲጠናቀቅ እንደሚሰራ የግንባሩ ሊቀ-መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ ከትናንት በስቲያ በአምቦ ከተማ ስታድዮም ለአምቦ ነዋሪዎች ባደረጉት ንግግር ኦነግ ህብረ-ብሄራዊ ፌደሪሊዝም ወደኋላ እንዳይመለስ የበኩሉን አስተዋፆ እንደሚያደርግ ገልጿል።

PHOTO:VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OLF

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦ ነ ግ/ በሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ ትላንት ቅርንጫፍ ከፈተ። ድርጅቱ በመጪው ምርጫ በሰላማዊና ዴሞከራሲያዊ መንገድ ለመሳተፍ መዘጋጀቱን የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ገልጸዋል። ግንባሩ በከተማውና በዞኑ የሚንቀሳቀስበትን ጽህፈት ቤት የከፈተው አባላቱ፣ ደጋፊዎቹና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
#OLF

በደቡባዊ ኦሮሚያ ዞኖች እና በምዕራብና ቄለም ወለጋ አካባቢዎች የመንግስት ወታደሮች በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ እየፈጸሙ ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ከሷል።

ሰዎች በጅምላ ይታሰራሉ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣም እየደረሰ ነው የሚለው ግንባሩ ፣ ክስተቱ ሆን ተብሎ በመንግስት እየተፈጸመ ያለ ነውም ብሏል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች ይህን ድርጊት እየፈጸሙ ያሉት ወታደሮች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳያውጅ የተሰማሩ የኮማንድ ፓስት አባላት ሲሆኑ ለአንድ አመት ህዝቡን እያስጨነቁ በመሆኑ ወደ ካምፓቸው እንዲመለሱ መቸየቃቸውን የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።

በዜጎች ላይ ደርሷል ያለውን ጉዳትም ገለልተኛ እና ነጻ አካል እንዲመረምረው በማለት ግንባሩ ጠይቋል። 

[DW]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የበራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሰለሞን ባልታወቁ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል ሲሉ የቲክቫህ ቡራዩ ቤተሰቦች አሳውቀውናል። ከደቂቃዎች በፊት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰሙ እንደነበር የቤተሰባችን አባላት ሲገልፁ ነበር። በከተማው ከተፈጠረው አለመራጋጋት ጋር ተያይዞ ቁጥሩ በርከት ያለ የፀጥታ ኃይል ወደ ከተማይቱ [ቡራዩ] እየገባ እንደሆነ የቲክቫህ አባላት እየገለፁ…
#OLF

የሀገር ሰላምና የዜጎች ደህንነት ሊረጋገጥ የሚችለዉ ሁሉም ወገኖች ለሁለንተናዊ መፍትሄ ተግተዉ ስሰሩ ብቻ ነው!

(የኦነግ መግለጫ - የካቲት 14, 2012)

የክስተቱን መንስዔና አጠቃላይ ምንነቱን አስመልክቶ እስካሁን በቂ ግንዛቤና መረጃ ባይኖረንም እንኳ በትናንትናዉ ዕለት (የካቲት 13, 2012) በቡራዩ ከተማ የተፈጸመዉንና የኮሚሽኔር ሰለሞን ታደሰ ሕይወት የጠፋበትን ግድያና የአካል ጉዳት ያደረሰዉን ጥቃት በጽኑ እናወግዛለን።

በጠፋዉ ሕይወትና በደረሰዉ አካላዊ ጉዳት ለተጎዱትም የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለተጎጂ ቤተሰቦችና ጓደኞች ሁሉ መጽናናቱን እንመኛለን።

በእንዲህ መሰሉ ጥቃትም ይሁን በሌላ በምንም መልኩ የተወሰኑ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ዒላማ አድርጎ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና አላስፈላጊ ጫናዎች የሀገሪቱን ችግሮች ይበልጥ ያባብሱና ያወሳስቡ እንደሆነ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ያመጣሉ ብለንም አናምንም።

በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ መንገዶች እየታዩ ላሉት የፖለቲካና የደህንነት ችግሮች ሁሉ ሰላማዊና ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ መንግሥት ከፍተኛዉን ድርሻና ኃላፍነት እንዳለዉ ይታወቃል። የዚህች ሀገር የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉም ይህንን አስመልክቶ የድርሻቸዉን ለመወጣት ግዴታ አለባቸዉ።

ሰፊዉ ሕዝብም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ሕዝብ የተጋረጡብንን ችግሮች በተመለከተ የችግሮቹን መንስዔና መፍትሄያቸዉን ለይቶ ያሉብን ችግሮች ለዘለቄታዉ መፍትሄ በሚያገኙበት አቅጣጫ ላይ የበኩሉን እገዛ ለማድረግ በንቃት መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነዉ ብለን እናምናለን።

More https://telegra.ph/OLF-02-22

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OLF

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ-መንበር የሆኑት የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት በፌዴሬል ፖሊስ መከበቡን የፓርቲው ቢሮ ኃላፊ አቶ ገዳ ኦልጅራ ለቢቢሲ ተናገሩ።

አቶ ገዳ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት አካባቢ የሚገኘው የጸጥታ ኃይል የሊቀመንበሩን ደኅንነት ለመጠበቅ መሰማራቱን ከፖሊስ መስማታቸውንም ተናግረዋል።

የአቶ ዳውድ ቤት መከበቡን ያረጋገጡት አቶ ገዳ የታጠቁ ኃይሎች በመኖሪያ ቤቱ ዙሪያ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።

ኃላፊው፤ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖሪያ ቤታቸው መውጣትና መግባት እንዳልቻሉና ወደ ውጪ የሚወጡ ከሆነም በጸጥታ ኃይሎቹ በቁጥጥር ሥር ሊውሉ እንደሚችሉ ስጋተቸውን ተናግረዋል https://telegra.ph/OLF-07-26 #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#OLF

ትላንት የኦነግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ እሁድ የተደረገው ስብሰባ አቶ ዳውድ ሊገኙ የማይችሉበት ሁኔታ ስለተፈጠረ ስብሰባው በምክትል ሊቀመንበሩ መካሄዱን መናገራቸው አይዘነጋም።

ስብሰባው የተካሄደው ሊቀመንበሩን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ 'ከእውነት የራቀ' ሲሉ ማስተባበላቸውም ይታወቃል።

በተመሳሳይ አቶ አራርሶ ቢቂላ እሁድ በኦነግ ጽሕፈት ቤት የተካሄደው ስብሰባ የሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ እውቅና የነበረው መሆኑን በመናገር አሁንም የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አቶ አራርሶ የስብሰባው ዋና አጀንዳ የነበረው “ሕዝቡ ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል? ድርጅታችንስ ምን ድረጃ ላይ ነው? በተለይ ደግሞ ወደ አገር ከገባን በኋላ ምን አገኝን፣ ምን አጣን? የሚለውን ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

በተቃራኒው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ገዳ ኦልጅራ እሁድ በአቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ሰብሰባ የድርጅቱ እውቅና የለውም፤ በግንባሩ ሊቀ መንበርም የማይታወቅ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ አራርሶ ቢቂላ ፤ ከአቶ ዳውድ ስብሰባ ለማካሄድ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ተናግረው ስብሰባ ሲጠሩ ፤ ዶ/ር ገዳ ወደ አቶ ዳውድ እንደደወሉና ፤ አቶ ዳውድ ስለ ስብሰባው መረጃ እንዳልደረሳቸው እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።

ያለ ድርጅቱ ሊቀ መንበር እውቅና ስብሰባ ማካሄድ ተገቢ አይደለም ብለው ለስብሰባ የሄዱ ሰዎችን እንደከለከሉ ገልጸው ፤ ' ሲከለከሉም የታጠቁ የመንግሥት አካላትን ይዘው መጥተው ፣ በጉልበት ገብተው ነው ስብሰባቸውን ያካሄዱት። ስብሰባው ሕጋዊ አልነበረም' ብለዋል ዶ/ር ገዳ https://telegra.ph/OLF-07-28 (BBC,DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#OLF #BALDERAS

ዛሬ "በብሄራዊ መግባባት" ላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባካሄዱት ውይይት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጥሪ እንዳልተደረገለት አሳውቋል።

ፓርቲው ዛሬ በብሔራዊ መግባባት ላይ ውይይት ሊያደርጉ ነው መባሉ የሰማው ከሚዲያ እንደሆነና ከዚህ ባለፈ ለድርጅቱ የቀረበ ጥሪ የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በፌስቡክ ገጹ እንደገለጸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በብሄራዊ መግባባት ዙሪያ "በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ" እያካሄደ ያለው ውይይት ሁሉን አሳታፊ አይደለም ሲል ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

Via @tikvahethmagazine

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦነግ በምርጫ 2013 ይሳተፋል ?

ትላንት በተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የእጩዎች ምዝገባ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አንድም እጩ አላስመዘገበም።

የኦነግ ጊዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ፥ ኦነግ ምንም የእጩ ምዝገባ አለማድረጉ በምርጫው ላለመሳተፉ ጉልህ ማሳያ ነው ብለዋል።

አቶ በቴ፥ "... በእኛ በኩል በተደጋጋሚ ስንገልፅ እንደነበረው ቢሮዎቻችን ፣ ዋና ፅ/ቤቶቻችን ጨምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኑ ፣ ነፃ እንቅስቃሴ እንደድርጅት መታገዱ ፣ አመራርና አባሎቻችን ያለህግ አግባብ መታሰራቸው ምርጫ ላይ በምናደርገው ተሳትፎ ላይ ትልቅ ተፅእኖ አላቸውና እነዚህ ችግሮች ሳይፈቱ መሳተፍ እንደማንችል ስንገልፅ ነበር ፤ በዚህ ሁኔታ እጩ ማስመዝገብ አልቻልንም ስለዚህ በምርጫ ሂደቱ ተሳታፊ አይደለንም" ብለዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እስከ ቀጣዩ ጠቅላላ ጉባኤ ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ከዚህ ቀደም የተነገረላቸው አቶ ቀጄላ መርዳሳ (የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) በበኩላቸው ፓርቲው ለ7 እና 8 ወር ችግር ላይ ስለነበር እጩ ለማቅረብ አስቸጋሪ እንደበር ገልፀዋል።

አቶ ቀጄላ ፥ ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤ የውስጥ ችግሮቹን ፈቶ በወጥ አመራር በምርጫ 2013 ለመሳተፍ እጬዎችን ለማስመዝገብ በተለየ ሁኔታ ጊዜ እንዲራዘምለት ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑን አሳውቀዋል።

#EthiopiaElection2013 #DW #OLF
https://telegra.ph/Oromo-Liberation-FrontABO-03-05
#OLF

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር አባላት ያከናውኑትን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ሰጥቷል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኦነግ አመራር አባላት (በእነ አቶ አራርሶ ቢቂላ ቡድን) የተከናወነውን ጠቅላላ ጉባኤ ተቀባይነት የለውም ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

ውሳኔውን መሰረት በማድረግ በጉባኤው የተመረጡት አዲስ አመራሮች እንደ ኦነግ አመራሮች መቀበል እንደማይችል አሳውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ምርጫው ውስጥ ለመሳተፍና እጩዎች ለማቅረብ ያቀረቡትን ጥያቄ አሁን የተመረጠው አመራር ተቀባይነት ካለማግኘቱ ጋር በተያያዘም ቦርዱ ጥያቄውን ማየት እንዳላስፈለገው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

* ዝርዝር መግለጫውን ከላይ ያንብቡ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ በቴ ኡርጌሳ ታሰሩ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ቡራዩ ከተማ መታሰራቸውን ከኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አቶ በቴ የታሰሩት ቡራዩ ፖሊስ ጣቢያ ነው። ወደቡራዩ የሄዱት የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ ነበር ተብሏል። አብረዋቸው ወደ ቡራዩ የሄዱት ሹፌራቸውም ለእስር መዳረጋቸው ተገልጿል። @tikvahethiopia
#OLF

" ... በእጃችን ከሚሞት ብለው ነው የሰጡን " - ሚሎ ኡርጌሳ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ በቴ ኡርጌሳ ከ1 ዓመት እስር በኋላ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር ተለቀዋል።

ምንም እንኳን አሁን አቶ በቴ ከእስር ቢለቀቁም በከፋ ህመም ላይ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

በቅርቡ እስር ላይ እያሉ ከሌሎች የታሰሩ ባልደረቦቻቸው ጋር የርሀብ አድማ አድርገው እንደነበር ተነግሯል፤ ከዚህ በኃላ ነው የጤናቸው ሁኔታ የከፋው።

የአቶ በቴ ወንድም ሚሎ ኡርጌሳ " በእስር ቤቱ ህመሙ ሲጠናበት ነው የቡራዩ ፖሊስ መምሪያ ቤተሰብ መጥተው እንዲወስዱ ያለው፡፡ " ያሉ ሲሆን አቶ ባቴ ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ አዳራ በተባለ ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ በቴ ህመሙ የጠናባቸው አስቀድሞ ህክምና ባለማግኘታቸው እንደሆነ ወንድማቸው አስረድተዋል።

አቶ በቴ ከዚህ በፊት ታስረው ለፍርድ ቤት እንደቀረቡ በሁለተኛው ቀጠሮ የዋስትና መብት የተጠበቀላቸው ቢሆንም ፖሊስ ግን ከቤተሰብም ሰውሮ በተለያዩ እስር ቤትና ማዕከላት እንዳቆዩት ወንድማቸው ተናግረዋል።

ቡራዩ፣ አዋሽ እና ገላን የታሰሩባቸው ስፍራዎች ናቸው።

በዚህ ሁሉ ሂደት ላይ በመጨረሻ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር ሆነው የርሃብ አድማ በማድረጋቸው ለህመም መዳረጋቸውን የሚገልፁት ወንድማቸው ሚሎ የርሃብ አድማውን ተከትሎ ከገላን ወደ ቡራዩ ከተወሰዱ በኋላ ከቤተሰብ ጋር ተገናኝተው ምርመራ ሲያደርጉ ለከፋ ህመም የዳረጋቸው በሽታ እንደተገኘባቸው ገልፀዋል።

" ከዚህም በኋላም ቢሆን መልሰው አስረዋቸው ነበረ ቢሆንም በመጨረሻ በእጃችን ከሚሞት ብለው ነው የሰጡን " ሲሉ ወንድማቸው ሚሎ ኡርጌሳ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/DW-03-15

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዓመት በኋላ ከቤታቸው ውጪ መታየታቸው ተሰምቷል። አቶ ዳውድ ዛሬ ረፋድ ላይ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ስብሰባ ለመቀመጥ ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አምርተው እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል። ምርጫ ቦርድ ከቀናት በፊት የኦነግ የረጅም ጊዜ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ከቤታቸው እንዳይወጡ ተከልክለው በቁም…
#OLF

የኦነግ ከፍተኛ ከፍተኛ አመራር አባል እና የሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ሽጉጥ ገለታ ለዶቼ ቨለ የተናገሩት ፦

" ... የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከአንድ ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ በመኖሪያ ቤታቸው ታግተው ሰው ሄዶ ሊጠይቃቸው እንዲሁም እሳቸውም ወጥተው ሰው ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ነበሩ።

ከረጅም ጊዜ በኋላ ይህንኑን የተረዳው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማጣራት አድርጎ ነገሩ ትክክል አይደለም በማለት መንግስት እንዲፈታቸው መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡

ይህንኑን ሂደት ተከትሎ ይመስላል ከቀናት በፊት ሊቀመንበሩ የካቲት 30 ቀን 2014 ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚያ ከሚኖሩበት ጊቢው ወጥተው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመገኘት ከቦርዱ ሃላፊዎች ጋር የኦነግ ጽ/ቤት ስለመዘጋቱ፣ በእስር ላይ የሚገኙ የፓርቲው አመራሮች ለደህንነታቸው አስጊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በመሆኑም ከቀደመው ሁኔታ በተሻለ መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OLF የኦነግ ከፍተኛ ከፍተኛ አመራር አባል እና የሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ሽጉጥ ገለታ ለዶቼ ቨለ የተናገሩት ፦ " ... የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከአንድ ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ በመኖሪያ ቤታቸው ታግተው ሰው ሄዶ ሊጠይቃቸው እንዲሁም እሳቸውም ወጥተው ሰው ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ነበሩ። ከረጅም ጊዜ በኋላ ይህንኑን የተረዳው የኢትዮጵያ…
#OLF

አቶ ዳውድ ኢብሳ አሁን ላይ ያገኙት የመንቀሳቀስ ነጻነት ወደ ፈለጉበት መሄድ የሚያስችላቸው እና በስልክ የፈለጉትን ሰው ደውለው የሚገናኙበት ነው ?

የዶ/ር ሽጉጥ ገለታ (የአቶ ዳውድ ከፍተኛ አማካሪ) ለዶቼ ቨለ የሰጡት ምላሽ ፦

" .... እኔ የማውቀው መንቀሳቀሳቸውን እንጂ ከዚህ በፊት የሚጠቀሙበት ስልካቸውን በመቀማታቸው ለጊዜው አግኝተናቸው ማውራት አልቻልንም፡፡

ይሁንና አስፈላጊ የሆኑ አንዳንድ ቦታዎችን ለመድረስ እድሉን እንዳገኙ ነው ለጊዜው የምናውቀው፡፡

ይሄ ለውጥ ምርጫ ቦርዱ ደብዳቤውን ከፃፈ ወዲህ ያየነው መልካም የሚባል ለውጥ ነው፡፡

ከ7 ቀናት በፊት ጀምሮ የተሻለ የመንቀሳቀስ ሁኔታ ቢኖርም ሙሉ በሙሉ በነጻነት የመሄድ ነገር አለ የሚል መደምደሚያ ግን የለንም።

" ... ለውጡ መልካም ነው፡፡ ይህ ቀጥሎ ሊቀመንበሩ ሙሉ በሙሉ ነጻ እስኮሆኑ እና በተለያዩ ህመሞች በእስር ቤት እየተሰቃዩ ያሉት እንደነ ሚካኤል ቦረን፣ ከኔሳ አያና እንዲሁም ከ አቶ ባቴ ዑርጌሣ ጋር በአንድ ስፍራ የነበሩ እንዲሁም ስንቴ ፍርድ ቤት ያሰናበተው እና ከ2 ዓመት በላይ ታስሮ የሚገኘው አብዲ ረጋሳ እና ሁሉም የኦነግ አባላትና አመራሮች ተለቀው ቢሮው ቢንቀሳቀስ ለሁሉም ሰላም መልካም ነው፡፡

የፖለቲካ አውዱንም ያሰፋል፡፡

አሁን የተመለከትነው መነሻ ይመስለናል፡፡ መቀጠል ያለበት ነው ብለን እናምናለን፡፡ በዚህ ሂደት ድምጻችን ላያሰሙልን የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች እና ሚዲያዎች በህዝባችን ስም ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OLF የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር አባላት ያከናውኑትን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ሰጥቷል። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኦነግ አመራር አባላት (በእነ አቶ አራርሶ ቢቂላ ቡድን) የተከናወነውን ጠቅላላ ጉባኤ ተቀባይነት የለውም ሲል ውሳኔ አሳልፏል። ውሳኔውን መሰረት በማድረግ በጉባኤው የተመረጡት አዲስ አመራሮች እንደ ኦነግ አመራሮች መቀበል እንደማይችል አሳውቋል።…
#OLF

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኦነግን በተመለከተ ውሳኔ አስተላለፈ።

ምርጫ ቦርድ በኦነግ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ የቀረቡለትን አቤቱታዎች በማየት ውሳኔ መስጠቱን አስታውሷል።

በውሳኔው ቅር የተሰኙት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር እነ አራርሶ ቢቂላ ጉዳዮን ወደፍርድ ቤት በመውሰዳቸው ክርክር ሲደረግበት ቆይቶ የሰበር ሰሚ ችሎት የሁለቱንም ወገኖች የመሰማት መብት በመጠበቅ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲሰጥበት ወደቦርዱ መመለሱ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ምርመራዎችን በማድረግ የፍርድ ቤቱን ትእዛዝ ተከትሎ ውሳኔ አሳልፏል።

ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት እንደሚገባው ቦርዱ የገለፀ ሲሆን ፓርቲው እስካሁን ካለበት የአመራር ችግር አንጻር፣ ጉባኤ ከመደረጉ በፊት የጉባኤው አጠራር ደንብ እና የምርጫ ህጉን የተከተለ መሆኑን ማረጋገጥ ማስፈለጉን አስታውቋል።

በዚህም የጉባኤ አጠራር ዝርዝር ዕቅድ፣ የጉባኤውን አጠራር በተመለከተ በተገቢው የፓርቲው አካል የተሰጠ ውሳኔ እና የውሳኔው ቃለጉባኤዎች እስከ ሚያዚያ 16 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲቀርብ ወስኗል።

(የቦርዱ ውሳኔ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች በእስር ላይ ያሉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባሎች የእስር ሁኔታን በተመለከተ ለረጅም ጊዜ ክትትል ሲያደርግ ነበር። በተጨማሪ ከፓርቲውና ከእስረኞች ቤተሰቦች በቀረቡ አቤቱታዎች መነሻነት ከመጋቢት 1 እስከ 10 / 2014 ዓ/ም በቡራዩ ከተማ፣ በገላን ከተማ እና በሰበታ ፖሊስ መምሪያዎች በአካል በመገኘት ክትትል በማድረግ እስረኞችን፣…
#OLF

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፦

" የኦነግ ፓርቲ አመራሮች ለተራዘመ ጊዜ ከሕግ አግባብ ውጭ ታስረው የሚገኙ በመሆኑ በአፋጣኝ ከእስር ሊለቀቁ እና ለደረሰባችው ጉዳት ሊካሱ ይገባል።

በተጨማሪ የፍርድ ቤትና የዐቃቤ ሕግ ውሳኔዎች በተደጋጋሚ እየተጣሰ እስረኞቹ ከሕግ ውጪ ለተራዘመ እስር መዳረጋቸው ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ስለሆነ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አፋጣኝ ማጣራት አካሂዶ ተገቢውን እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል "

▪️

የኢሰመኮ የሲቪል፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጂብሪል ፦

" ታሳሪዎቹ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በመሆናቸው በሕዝባዊ አገልግሎት ስራቸው ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይጋለጡ ጥበቃ ሊደረግ ሲገባ፤ በተግባር የተገላቢጦሽ መሆኑ አሳዛኝ ነው ጉዳዩ አፋጣኝ እልባት ያስፈልገዋል "

@tikvahethiopia