TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥንቃቄ ይደረግ‼️

ከወለጋ #እንደተፈናቀሉ_በማስመሰል #በጅማ_ከተማ ህብረተሰቡን በማጭበርበር እርዳታ ሲያሰባስቡ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሁለት ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደገለጸው ግለሰቦቹ ከወለጋ እንደተፈናቀሉና ቤታቸው ንብረታቸው እንደተወሰደ በመናገር በሀሰት ከህብረተሰቡ ለአምስት ቀን #እርዳታ ሲያሰባስቡ ቆይተዋል።

ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በግለሰቦቹ ላይ ባደረገው ክትትል የካቲት 22/ 2011ዓ.ም. በጅማ ቢሺሼ የገበያ ማዕከል እንደያዛቸው የመምሪያው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ አውጋቸው ተናግረዋል።

“በወንጀል ድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉት ሁለቱ ግለሰቦች ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ መሆኑ በተደረገባቸው ምርመራ ተረጋግጧል” ብለዋል።

በሃሰት ካሰባሰቡት ገንዘብ ውስጥ አንደኛው መኪናውን እንድታሰራለት 5 ሺህ 300 ብር ለባለቤቱ መላኩንና ሌላኛው ደግሞ 3 ሺ 23 ብር ለዘመዶቹ መላኩን በሰጡት የእምነት ቃል አረጋግጠዋል።

ከዚህ ገንዘብ በተጨማሪም ፖሊስ በግለሰቦቹ እጅ አራት ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ በኢግዚቢትነት መያዙንም አመልክተዋል።

በወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን ሲከታተል የቆየው የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በዋለው ችሎች እያንዳንዳቸው በአንድ ዓመት ከስምንት ወራት ጽኑ እስራትና በ500 ብር እንዲቀጡ የወሰነባቸው መሆኑን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።

ግለሰቦች #ክስቸውን_እንዲከላከሉ እደሉ ቢሰጣቸውም #ባለመቻላቸው የቅጣት ውሳኔው ጸንቶባቸዋል፡፡

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia