TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዘንድሮ በመላ ሀገሪቱ የ " ኬጂ " ተማሪዎች እንግሊዝኛ ቋንቋ እየተማሩ አይደለም።

የመዋዕለ ህጻናት ተማሪዎች " ኤ፣ ቢ፣ ሲ፣ ዲ… " ን በዜማ መቁጠር፣ " ኤ ፎር አፕል፣ ቢ ፎር ቦል… " እያሉ ቃላት መመሥረትም አቁመዋል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ " ስፖክን ኢንግሊሽ " እና " ኢንግሊሽ ሊትሬቸር " ከ " ኬጂ " ተማሪዎች የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ ተሰርዘዋል።

እንደ ቀድሞው በአማርኛ ሂሳብ፤ በእንግሊዝኛ " ማትስ " እያሉ የቁጥሮችን አጠራር በሁለት ቋንቋ መሸምደድም ቀርቷል።

የዘንድሮ የ " ኬጂ " ተማሪዎች ለአካባቢ ሳይንስ እና ለ " ጄኔራል ሳይንስ " ሁለት ደብተር አይዙም።

በአራት ዓመታቸው " ነርሰሪ " የሚገቡት ህጻናት፣ በ6 ዓመታቸው ከ " ዩ ኬጂ " ሲመረቁ የሚያውቁት ብቸኛ የፊደል ገበታ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን እንዲሆን ተደርጓል።

ልጆችን እንግሊዝኛ በማስተማር ተመራጭ የሆኑት የግል መዋለ ህጻናት ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሁሉንም ትምህርት የሚሰጡት በአካባቢው የአፍ መፍቻ ቋንቋ ብቻ ነው።

በአዲሱ የትምህርት ሚኒስቴር አሠራር መሠረት ተማሪዎች እንግሊዝኛ ቋንቋን እንደ አንድ ትምህርት መማር የሚጀምሩት #አንደኛ_ክፍል ሲደርሱ ነው።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ መተግበር የጀመረው ሥርዓተ ትምህርት ህጻናት የሚማሩትን ትምህርት በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች (ሰብጀክት) አይከፋፍልም።

የኬጂ ተማሪዎች እንደ ቀድሞው ሂሳብ፣ አማርኛ ወይም አካባቢ ሳይንስ የሚባሉ የትምህርት ዓይነቶች አይኖሯቸውም። በትምህርት አይነቶች ፋንታ ህጻናቱ የሚማሩት " ጭብጦችን " ነው።

ለምሳሌ፤ የመጀመሪያ ዓመት የመዋለ ህጻናት ተማሪዎች ስድስት ጭብጦችን ይማራሉ። ከእነዚህ ጭብጦች ውስጥ፦
* ስለ እኔ፣ ስለ ቤቴ እና ስለ ቤተሰቦቼ
* ትምህርት ቤቴ እና አካባቢዬ የሚሉት ይገኙበታል።

የኬጂ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከሚማሯቸው ጭብጦች ውስጥ ደግሞ ፦
* ዋሊያ
* ህዋ
* ተክሎች እና መጓጓዣ ተጠቃሽ ናቸው።

በአዲሱ ካሪኩለም መሠረት ህጻናቱ እንደ ቀድሞው አብዛኛውን ጊዜያቸውን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብለው ከሰሌዳ እና ከደብተር ጋር እንዲፋጠጡ አይደረግም።

ዘንድሮ የኬጂ ተማሪዎች የሚማሩባቸው ዋነኛ መንገዶች ጨዋታ፣ መዝሙር እና ተረት ናቸው።

በአዲሱ ካሪኩለም የኬጂ ተማሪዎች እንግሊዝኛ እንዲማሩ አይደርግም። በእንግሊዝኛ ምንም ነገር የለም። ሁሉም ነገር በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል።

የኬጂ ትምህርት ይዘት መቀነስ ያላስደሰታቸው ወላጆችም ያሉ ሲሆን ተማሪዎች ከአቅማቸው በታች እንዲማሩ እያደረገ ነው ብለዋል።

በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶችም ከወላጆች ቅሬታ እየተቀበሉ መሆኑን የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች አሠሪዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ጣሰው አሳውቀዋል።

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ካሪኩለሙ በዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት የትምህርት ይዘቱ መቀነሱን እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መውጣቱን በተመለከተ ማኅበሩ ተቃውሞ አስተያየት መስጠቱንም አስታውሰዋል።

የቅድመ አንደኛ ሥርዓተ ትምህርትን ካዘጋጁ ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ጃለታ ፤ " ቤተሰብ ልጁ እንግሊዝኛ ከቻለ፣ ፊደል ከቆጠረ ወይም መደመር ከቻለ ተምሯል፣ አድጓል ብሎ ያስባል። በህጻናት ደረጃ ትምህርት እርሱ አይደለም " ብለዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/BBC-AMAHRIC-01-24

Credit - #BBCAMAHRIC

@tikvahethiopia