#GERD
በግድቡ ጉዳይ በኢትዮጵያ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመመከት ዝግጁ መሆኗን ግብጽ አስታወቀች!
የዓባይ ወንዝን በተመለከተ ሀገራቸው የትኛውንም አማራጭ እንደምትጠቀምና ታሪካዊ ተጠቃሚነቷን እንደምታስቀጥል የግብጽ ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ አስጠነቀቁ፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት አሜሪካ ላይ ሊካሄድ በነበረው የሦስትዮሽ ድርድር ኢትዮጵያ አለመገኘቷን ተከትሎ ግብጽ ጉዳዩን በአሉታ እየተመለከተችው ትገኛለች፡፡
ኢትዮጵያ ግድቡን በተመለከተ ሰፊ ምክክር ማድረግ እና ብሔራዊ ጥቅሟን በዘላቂነት የሚያስጠብቅ አቋም መያዝ በሚያስችላት ሐሳብ ላይ መምከርን ማስቀደም ስላለባት በድርድሩ እንደማትሳተፍ መግለጧ ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎም የግብጽ ፓርላማ ምክትል አፈ-ጉባኤ ሶሊማን ዋድሃን ዛቻ የተሞላበት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ምክትል አፈ-ጉባኤው ይህንን ያሉት የግብጽ ውጭ ጉዳይ እና የመስኖ ሚኒስትሮች ‘ኢትዮጵያ በድርድሩ ያልተገኘችው ድርድሩን ሆን ብላ ልታደናቅፍ ነው’ የሚል ሐሳብ ማሰራጨታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
More https://telegra.ph/GERD-03-03
#አልኣህራም #አብመድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia