TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
ሃላሌ!! #ይርጋለም!!

የአገር ሸማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና ወጣቶች የተገኙበት የሰላም ኮንፈረንስ #በይርጋለም ከተማ ተካሂዷል፡፡

ወጣቶች ጥያቄያቸው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ የሲዳማ "ሃላሌ" ባህላዊ ስርዓት ተከትለው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠይቁ የሲዳማ አገር ሸማግሌዎች አሳስበዋል፡፡

"ኤጄቶዎች" ወይም የሲዳማ ወጣቶችና አገር ሸማግሌዎች የጋራ የሰላም ኮንፈረንስ ማካሄድ ከጀመሩ በኋላ ለውጥ መታየቱን የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ #ሚሊዮን_ማቲዮስ አስታውቋል፡፡

"ኤጄቶዎች" የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ የሚረጋገጥበትን ህዝበ ውሣኔ እንዲያስፈፅም የክልሉ ምክር ቤት ለምርጫ ኮሚሽን ቢስታውቅም ዘግይቷል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 95 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,034 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠና አምስት (95) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,063 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ የተገኘባቸው 71 ወንድ እና 24 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ15 እስከ 80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 94 ሰዎች…
#AtoAknawKawza

በደቡብ ክልል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 8 መሆናቸው ተገልጿል!

ባለፉት 24 ሰዓት በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት 100 ያህል የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል። በአጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ስምንት (8) ነው።

አንድ ግለሰብ ከአዲስ አበባ ቤት ለቤት በተደረገው ምርመራ ፖዘቲቭ ሆኖ ወደ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ከገባ በኃላ ሲያዝ በዛሬው ዕለት የጤና ሚኒስቴር አዲስ በቫይረሱ መያዛቸውን ካረጋገጠው 95 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በንሳ ወረዳ ላይ ተይዞ በይርጋለም ለይቶ ማቆያ እንዲቆይ ተደርጓል።

ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው እና አብረውት ከአዲስ አበባ ወደ በንሳ የመጡ 14 እና 20 ሰዎች ደግሞ ከተጠርጣሪውና ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ተለይተው በድምሩ 34 ሰዎች ንክኪ ያላቸው #በይርጋለም ለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia